(ዘ-ሐበሻ) በካንጋሮው ፍርድ ፍትሃዊ ባልሆነ ፍርድ እስር ቤት የተወረወረው ጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ፤ ፍርድ ቤት በማያውቀው ሁኔታ በአንድ የህወሓት ኮማንደር በእስር ቤት ከፍተኛ ስቃይ እየደረሰበት እንደሚገኝ ከስፍራው ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ።
በጋዜጠኛ ተመስገን ደሳለኝ ላይ በዝዋይ እስር ቤት እየደረሰ ያለው ስቃይ ኮማንደር ቢኒያም በሚባል አዛዥ ሲሆን ተመስገንን በአንድ ምሽት ከ5 ጊዜ በላይ በድቅድቅ ለሊት በማስወጣት ብርድ ላይ እንደሚያስተኙት ከስፍራው የደረሰው መርጃ ያጋልጣል።
በተለይ ተመስገን ደሳለኝ “የመንግስት ገመና” በሚል ከእስር ቤት ከፃፈ በኋላ ደህነነቶች እና ይኸው ኮማንደር ቢኒያም የሚባል አዛዥ የእንግልሃለን ሬሳህን እዚህ ብንጠለው ዞር ብሎ የሚያይህ የለም በሚል እንደሚያስፈራሩት የጠቆሙት የዜና ምንጮቻችን ድብደባ እንደተፈጸመበትም ታውቋል።
ኢትዮጵያ ከወትሮው በተለየ ሁኔታ ግለሰቦች የሚያዙባት፤ በአንድ ግለሰብ ትዕዛዝም ሕይወት የሚጠፋባትና የሚበላሽባት ሃገር እየሆነች መምጣቱ የስርዓቱን ደጋፊዎች ሳይቀር እያስቆጣ እንደሚገኝ ከተለያዩ ስፍራዎች የሚገኙ መረጃዎች ይጠቁማሉ።
No comments:
Post a Comment