በድሬዳዋ አየር ሃይል ውጥረት የበዛበት ግምገማ ተካሄደ
ኢሳት ዜና :-አራት ከፍተኛ ማእረግ ያላቸው የአየር ሃይል አብራሪዎች መጥፋታቸውን ተከትሎ በድሬዳዋ የአየር ሃይል ምድብ ሲካሄድ የነበረው የ3 ቀናት ግምገማ ሃሙስ እለት ተጠናቋል።
በግምገማው ላይ አብራሪዎች፣ አሰልጣኞች፣ ቴክኒሻኖችና ሰራተኞች የተገኙ ሲሆን፣ ሰራተኞቹ ስለጠፉት አብሪዎች የተሰማቸውን ስሜት እንዲናገሩ፣ የሚያውቁትን ሚስጢር እንዲያወጡ ሲገደዱ ሰንብተዋል። ብዙዎች ” ስለጠፉት አብራሪዎች ምን ትላላለችሁ?’ እየተባሉ ሃሳባቸውን እንዲናገሩ የተጠየቁ ሲሆን፣ በሚሰጡት ሃሳብ ተንተርሶ የደህንነት ሃይሎች ተጨማሪ ምርምራ እንደሚያካሂዱ በግምገማው ላይ የተሳተፉ ወገኖች ገልጸዋል።
በግመገማው ላይ የተገኙት አዛዦች በሙሉ እጅግ ተናደው መሰንበታቸውን የሚናገሩት ምንጮች፣ በግቢው ውስጥ ያለው ድባብ ውጥረት የበዛበት በመሆኑ ሰራተኞች ተረጋግተው ስራቸውን ለመስራት አልቻሉም። የእርስ በርስ ጥርጣሬውና አለመተማመኑ የከፋ ደረጃ ላይ መድረሱንም ሰራተኞች ገልጸዋል።
በዚህ ሳምንት ስርአቱን አናገለግልም ብለው ወደ ኬንያ የተሰደዱትን አብራሪዎች በተመለከተ ኢሳት ለወደፊቱ ዝርዝር መረጃዎችን እንደሚያቀርብ ለመግለጽ ይወዳል።
No comments:
Post a Comment