የአንድነት ለፍትሕና ዴሞክራሲ ፓርቲ (አንድነት) ቢሮ በፖሊስና በደህንነት መከበቡን አቶ አስራት አብርሃ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ቢሮው በደህንነትና በፖሊስ በመከበቡ አባላት መውጣትና መግባት እንደማይችሉ የገለጹት አቶ አስራት ‹‹ውጭ ያለነው ወደ ውስጥ እንዳንገባ ተከልክለናል፡፡ ውስጥ ያሉትም መውጣት አይችሉም፡፡›› ብለዋል፡፡ የአንድነት አመራሮችና አባላት እንዳይወጡና እንዳይገቡ የከለከሉት ደህንነትና ፖሊሶች የከበባውን ምክንያት እንደማይናገሩ አቶ አስራት ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በተመሳሳይ የመላው ኢትዮጵያ አንድነት ድርጅት (መኢአድ) ቢሮው በፖሊስና በደህንነቶች በመከበቡ አመራሮችና አባላቱ ወደ ውስጥ መግባትም ሆነ ወደ ውጭ መውጣት እንደማይችሉ ተግልጾአል
ምርጫ ቦርድ ዕውቅና የነሣቸው የፓርቲው አመራር አባላትም ወደ ፅህፈት ቤቱ እንዳይገቡ መደረጋቸውን ይገልፃሉ። ፖሊስ ከፅህፈት ቤቱ ሲያግዳቸው የፍርድ ቤት ትዕዛዝ እንዳላሳየም ተናግረዋል። የየካ ክፍለ ከተማ ፖሊስ እርምጃውን የወሰደበትን ምክንያት ተጠይቆ መልስ ለመስጠት ፍቃደኛ አልሆነም። የአንድነት ፓርቲ ምክትል ፕሬዚዳንትና እንደራሴ አቶ ግርማ ሰይፉ ለቪኦኤ መግለጫ ሰጥተዋል፡፡ - See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/38622#sthash.uABK7UlZ.dpuf
No comments:
Post a Comment