በአቶ አዲሱ ለገሰ ሰብሳቢነት በባህርዳር ከተማ ሊካሄድ የነበረው የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ስብሰባ ሳይካሄድ ቀረ
የአማራ ክልል መሬትን ሸንሽኖ ለትግራይ ክልል ነዋሪዎች በተለይም ለህወሀት አባላት እና ደጋፊዎች መሰጠቱን ተከትሎ በአርማጭሆ በተነሳው ተቃውሞ ዙሪያ ከሰኞ እለት ተቋርጦ ለዛሬ ቀነ ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው ስብሰባ መበተኑን ከስፍራው ያገኘሁት ማስረጃ ያስረዳለ።
ሰኞ እለት በ27/04/07 ዓ.ም ከፍተኛ የብአዴን አመራሮች እና የክልሉ ባለስልጣናት በጉዳዩ ላይ ለመወያየት ከቀኑ 4 ሰዓት ጀምሮ ባህር ዳር የክልሉ መስተዳደር የስብሰባ አዳራሽ ተገኝተው የነበረ ቢሆንም ስብሰባው ባለመስማማት እስከ 6፡30 ከተካሄደ በኋላ ተሰብሳቢው የተባለው መሬት የአማራ መሬት ነው የሚል አዝማሚያ በማሳየቱ ከፍተኛ ብስጭት ውስጥ የገቡት አቶ ገዱ አንዳርጋቸው ከምሳ በኋላ ስብሰባው ሲጀመር ከፌዴራል መንግስት መመሪያ መምጣቱን ተናግረው የሚቀጥለው ቅዳሜ ጥር 2 በአቶ አዲሱ ለገሰ እና በአቶ በረከት ስምኦን ሰብሳቢነት ስብሰባው ከእንደገና እንደሚካሄድ ተናግረው ስብሰባው ተበትኖ የነበረ ሲሆን በዛሬው እለት በአቶ አዲሱ ለገሰ ሰብሳቢነት ስብሰባው ይካሄዳል ተብሎ ቢጠበቅም ሳይካሄድ ቀርቷል። መረጃውን በስልክ የነገረኝ የብአዴን አባል እንደገለጸልኝ ከሆነ ስብሰባው መሰረዙን ለተወሰኑ የክልሉ አመራሮች በትላንትናው እለት የተገለጸ ሲሆን ቀሪው አባል ሰኞ እለት የሰማውን መረጃ ብቻ ይዞ ዛሬ ባህርዳር ላይ ቢገኝም ስብሰባው እንደተሰረዘ ተንግሮ እንዲመለሱ መደረጉን ገልጾ የተሰረዘበት ዋነኛ ምክንያት ስብሰባውን ተገን አድርጎ በሚነሳው ተቃውሞ የክልሉ አመራር አቅጣጫውን እንዳይቀይር በመስጋት በአቶ ገዱ አንዳርጋቸው እና በህወሀት አመርሮች የተዘየደ መላ መሆኑን አስታውቋል። በክልሉ የሚገኙ ካድሬዎች ሰሞነኛ ወሬ የአማራ ክልል መሬት ወደትግራይ ክልል መጠቃለል መሆኑን የገለጸው የመረጃ ምንጬ በክልሉ የአርበኞች ግንባር ጥቃት ይፈጽማል የሚል ከፍተኛ ስጋት እንዳለና ይህንንም ተከትሎ በመንግስት መስሪያ ቤቶች እና ባንኮች አካባቢ ከፍተኛ የመከላከያ ሀይል ሰፍሮ እንደሚገኝ አክሎ ገልጿል።

No comments:
Post a Comment