መኢዴፓና ኢብአፓ በፓርቲዎች ላይ የሚፈፀመው ደባና ዛቻ እንዲቆም ጠየቁ
• ‹‹ምርጫ ቦርድ የኢህአዴግ አምስተኛ አባል ፓርቲ ሆኗል››
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
የመላው ኢትዮጵያ ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (መኢዴፓ) እና የኢትዮጵያ ብሄራዊ አንድነት ፓርቲ (ኢብአፓ) በምርጫ ዋዜማ ገዥው ፓርቲና ምርጫ ቦርድ በተቃዋሚ ፓርቲዎች በተለይም በሰማያዊ፣ አንድነትና መኢአድ ላይ የሚፈፅሙትን ደባና ዛቻ እንዲያቆሙ ጠየቁ፡፡ ፓርቲዎቹ ህዳር 7/2007 ዓ.ም ‹‹በምርጫ ዋዜማ በፓርቲዎች ላይ የሚደርሰው ደባና ዛቻ በአስቸኳይ ይቁም›› በሚል በጋራ ባወጡት መግለጫ ኢህአዴግ ምርጫ ቦርድን በመሳሪያነት በመጠቀም ሰማያዊ፣ አንድነትና መኢአድ ላይ ወከባና ዛቻ እየፈፀመ ነው ሲሉ ወቅሰዋል፡፡ መግለጫው ምርጫ ቦርድ ጠቅላላ ጉባኤ አድርጉ እያለ ለማዋከብ ቢጥርም መኢአድና አንድነት የተዋጣለት ጠቅላላ ጉባኤ አድርገዋል ብሏል፡፡
ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው ሰማያዊ ፓርቲ አገራዊ ግዴታውን እየተወጣ በመሆኑ፣ እንዲሁም መኢአድና አንድነት ብቃት ያላቸው ልሂቃንን ማፍራት ስለቻሉ በተፈጠረበት ስጋት ፓርቲዎቹን ለማጥፋት እየጣረ መሆኑንና ምርጫ ቦርድም የኢህአዴግ አምስተኛ አባል ፓርቲ እስኪመስል ድርስ የገዥው ፓርቲ መጠቀሚያ ሆኗል ሲሉ ወቅሰዋል፡፡
የኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ከገዥው ፓርቲ መሳሪያነት ወጥቶ የተጣለበትን ኃላፊነት እንዲወጣም ፓርቲዎቹ በመግለጫቸው አሳስበዋል፡፡

No comments:
Post a Comment