Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, January 21, 2015

በመላ ትግራይ የምርጫ ኣስፈፃሚ ለተባሉ ሚሊሻዎች የተኩስ ልምምድ ስልጠና እየተሰጠ ነው


በመላ ትግራይ የምርጫ ኣስፈፃሚ ለተባሉ ሚሊሻዎች የተኩስ ልምምድ ስልጠና እየተሰጠ ነው ፤ በምስራቅ ጎጃም የምርጫ ካርድ ያልወሰዱ ዜጎች ስኳር እንዳይወስዱ ተከለከሉ


ጥር ፲፪(አስራ ሁለት ) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በመጪው ግንቦት ከሚካሄደው ምርጫ ጋር በተያያዘ በመላ ትግራይ ክልል <<ምርጫ አስፈጻሚ>>የተባሉ ተኳሽ ሚሊሻዎች ከፍተኛ የተኩስ ልምምድ እያደረጉ እንደሚገኙ በለክልሉ ያሉ ወኪሎቻችን ዘግበዋል።

ይህ የሚሊሻዎች ስልጠናው ፤ከኢትዮ-ኤርትራ ጦርነት በሗላ በዓይነቱም ሆነ በሰልጣኞቸ ብዛት ለየት ያለ ሲሆን፤ በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የህወሓት ኣባላት ብቻ የተሳተፉበት መሆኑ ታውቋል።

ሚሊሻዎቹ በኣፅቢ ወንበርታ ወረዳ ፣ሓየሎም ቀበሌ <ቓፀሎ >በተባለ ስፍራ ጥር 6 ቀን /2007 ዓ/ም ልምምድ ሲያደርጉ፤ ኣቶ ሕሸ ገብሩ የተባሉ የ8 ልጆች አባት ከሰልጣኞች በተተኮሰ ጥይት ተገድለዋል።

ኣቶ ሕሽ ገብሩን የገደላቸው ስልጣኝ ሚሊሻ ዓወት ድራሩ የሚባል ሲሆን፤ በፈጸመው ድርጊት ምንም ሳይጠየቅ ስልጠናውን እየቀጠለ ይገኛል።

በወረዳው እየሰለጠኑ የሚገኙ ሚሊሻዎች ከኣቶ ሕሸ በተጨማሪ በርካታ የቤትና የዱር እንስ ሳት እየገደሉ እንደሆነም ከስፍራው የደረሰን ዜና ያመለክታል። <<የምርጫ አስፈጻሚ>>ተብለው ከሚሰለጥኑት ከነኚህ ሚሊሻዎች በተጨማሪ በየምርጫ ጣቢያው ለሚመደቡ ሌሎች የህወሀት አባላትም ተጨማሪ ስልጠና እየተሰጠ መሆኑን ወኪሎቻችን አመልክተዋል።
ይህ በ እንዲህ እንዳለ በምስራቅ ጎጃም ዞን ጎዛመን እና አነደድ ወረዳ የቦቀል ቀበሌ ነዋሪዎች የምርጫ ካርድ ስልልወሰዳችሁ ስኳር አይሰጣችሁም መባላቸውን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
በቀበሌው መጥቷል የተባለውን ስኳር ለማግኘት ወደ ቀበሌው ሲያመሩ ‹‹የምርጫ ካርድ ወስዳችኋል?›› የሚል ጥያቄ እንደሚቀርብላቸው የተናገሩት ነዋሪዎቹ፤ የምርጫ ካርድ የሚያሳዩ ነዋሪዎች ስኳሩ ሲሰጣቸው፤ ያላወጡት በአስቸኳይ ምርጫ ካርድ አውጥተው እንዲመለሱና ስኳር እንዲወስዱ ተነግሯቸዋል ተብሏል፡፡
የምርጫ ካርድ ማውጣት የለብንም ያሉት ነዋሪዎች ስኳር እንደማያገኙ የተነገራቸው ከመሆኑም በላይ፤‹‹እንደዜጋ የምርጫ ካርድ ወሰድንም፤ አልወሰድንም ስኳር የማግኘት መብት አለን›› ያሉ ዜጎች በፖሊስ ተደብድበው እንደተባረሩ ከቦታው የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡
ምርጫ ካርድ ሳያወጣ ስኳር ለመውሰድ ወደ ቀበሌው ያመራ አንድ መምህር ማግኘት እንደማይችም መነገሩን ተከትሎ – የምርጫ ካርድ ቢያወጣም፣ባያወጣም ስኳር የማግኘት መብት እንዳለው ላቀረበው ጥያቄ፦<<‹‹እኛ ስኳር ስጡ የተባልነው ካርድ ለወሰደ ብቻ ነው፡፡ ካርድ ካልወሰድክ አይሰጥህም›› ተብሎ እንደተመለሰ ተናግሯል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials