Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, January 3, 2015

ወያኔ የጉራጌ ማህበረሰብ ከሌላው የህብረተሠብ ክፍል ለማጋጨት በወልቂጤ ዩኒቨርሥቲ እየፈጸመው ያለው ደባ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊገነዘበው ይገባል

ወያኔ የጉራጌ ማህበረሰብ ከሌላው የህብረተሠብ ክፍል ለማጋጨት በወልቂጤ ዩኒቨርሥቲ እየፈጸመው ያለው ደባ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ሊገነዘበው ይገባል

  • By Seyoum Workneh
ከላይ በርዕሱ ላይ የጉራጌ ማህበረስብ ከሌላው የህብረተሰብ ክፍል ብዬ የተጠቀምኩት ወያኔ/ኢህአዴግ በጉራጌ ዞን በቸሃ ወረዳ ጉብሬ ከተማ ላይ በህዝብ ድጋፍና እርብርቦሽ የተመሠረተችው ወልቂጤ ዩኒቨርሥቲ ውሥጥ በተግባር እያደረገ ያለውን ጉዳይ ነጠል አድርጌ ለማሣየት እንጂ ወያኔ በሁሉም የሐገራችን ክፍል የተሠማራበት እኩይ ተግባር ጠፍቶኝ እንዳልሆነ ልትረዱልኝ እፈልጋለሁ። ባጠቃላይ ወያኔ ኢትዮጵያ ሐገራችን ለማጥፍት ግቡ አድርጎ የሚንቀሳቀሥ የትኛውንም ህዝብ ሊወክል የማይችል በጥቂት ማፍያ ወንበዴዎች የሚመራ የሆዳሞች ድርጅት ነው። የመጨረሻ የሆነውን ሐገር የማፍረሥ አላማቸው እውን እሥኪሆን ድረሥ ሀገሪቷን መምራት ሥለ ሚፈልጉ ህዝቡ አንድ እንዳይሆን የተቻላቸውን ሁሉ ከማድረግ ወደ ኻላ እንደሚያደርጉ ልንገነዘብ ይገባል።
welktie
ከፋፍለህ ግዛ (በዘር) መርህ የሚከተለው ወያኔ ላለፉት 23 ዓመታት ህዝቡን እርሥ ብርሥ እንዳይተማመን፤ እርሥ በርሥ እንዲተላለቅ፤ እርሥ በርሥ እንዲጥላላ አያሌ ሥራዎችን ሠርቷል። ህዝቡን በዘር፣ በሐይማኖት፣ በፖለቲካ አመለካከት፣ በእምነትና በሌሎችም ተመሣሣይ ጉዳዮች ለመከፍፈል በፖሊሢ ደረጃ ተቀርጾ ሢመሩበት የነበረና አሁንም ያለ ህዝብ ፍቃድ የገፉበት ጉዳይና ፖሊሢ ነው። የኢትዮጵያ ሕዝብ ከ3000 አመት በላይ ተከባብሮና ተቻችሎ፣ ያሉትን ልዩነቶች አጥብቦ የኖረባት ሐገር ዛሬ የዘር ፖለቲካን በማራመድ በህዝብ ዘንድ ጥላቻን በማሥፈንና ልዩነቶችን በማሥፍት የኢትዮጵያ ህዝብ ሆድና ጀርባ ለማድረግ ተግተው እየሠሩ ነው። ወያኔ በዚህም ተግባሩ ከልማት መንገድ ይልቅ የጥፍት መንገድ መምረጡን ያመለክታል።
ወያኔ በዚህም መሠሪ ተግባሩ ሙሉ በሙሉ ተሣክቶለታል ማለት ባይቻልም በተወሰነ ደረጃም ቢሆን ግን የዚህ ተግባር እርዝራዦች፣ አደር ባዮች፣ አጎብዳጆችና ሆዳሞች ግን አልጠፉም። አንዳንዶቻችን የወያኔ መሠሪ ተግባርና አላማ ጠንቅቀን የምናውቅ ብንሆንም ከወጥመዱ ማለፍ ያልቻልን ደካሞችም መኖራችን ግን አልቀረም። ወያኔ ሁላችንም ጠባብና ትምክተኛ እንድንሆን እንደሚፈልግ ሁሉም ኢትዮጵያዊ ጠንቅቆ የሚያውቀው ይመሥለኛል። ይህ ከሆነ ደግሞ ሁላችንም ወጥመዱ ውሥጥ እንዳንደናቀፍ አሥፈላጊ ጥንቃቄ መውሠድ ይጠበቅብናል። ያ ሳይሆን ሲቀር ግን እራሣችን ወያኔ ባዘጋጀው መረብ ውሥጥ ተጠልፈን ትክክለኛ መሥመር እየተከተሉ ያሉትን ማደናቀፋችን ወይም እየተከተሉት ላለው የለውጥ ጎዳና እንቅፍት መሆናችን አይቀሬ ነው። በዚህ ጊዜ በቀጥታም ሆነ በተዘዋዋሪ የወያኔ መሣሪያ ሆነናል ማለት ነው።
ወደ ዋናው ጽሁፌ ሥመለሥ ወያኔ በወልቂጤ ዩኒቨርሥቲ እያደረገ ያለውን ነገር አሣሣቢ ደረጃ ላይ በመድረሡ ምክንያት ነው። ይህም ዩኒቨርሥቲው ውሥጥ ወያኔ የራሡን ሠዎች በማዘጋጀት ፍራሽ ከተደረደረበት ክፍል እሥከ የተማሪ ማደሪያ የሆኑትን ዶርሚተሪዎችን በማቃጠል ከሌላ ክልል የመጡት ተማሪዎች ድርጊቱን እንደፈጸሙት በማድረግ የጉራጌ ማህበረሰብ ከሌላ ክልል ለመጡትን ተማሪዎችም ሆነ ሥለ ሌላው ማህበረሰብ የተሳሳተ አመለካከት እንዲኖረው ለማድረግና እርሥ በርሥ ለማጋጨት ነው። በመሠረቱ የጉራጌ ማህበረሠብ በሁሉም የሐገራችን ክፍል በተለያዩ የግልና የመንግሥት መሥሪያ ቤት በተለይ የንግድ ሥራ ላይ ተሠማርቶ የሚሠራ ህዝብ እንደመሆኑ መጠን ከሁሉም የሐገራችን ክፍል የሚመጡ ሠዎች ጋር በደንብ የመገናኘት አጋጣሚ ሥላለው የኢትዮጵያ ህዝብ ምን ያህል ጨዋ እንደሆነ ጠንቅቆ ያውቃል። በዚህም ምክንያት ወያኔ የሚፈጸማቸው ድርጊቴች ወይም የወያኔ ሴራዎች ጠንቅቆ የሚያውቅ ሕዝብ ነው።
ባሳለፍነው ሳምንት ታህሳስ 25, 2014 እኤአ ጠዋት በወልቂጤ ዩኒቨርስቲ ሁለት ተማሪዎች (አንደኛው ከአማራ ክልል የመጣ, ሁለተኛው ከኦሮምያ ክልል) መጣላታቸውን ተከትሎ ከኤሮምያ ክልል የመጡት ተማሪዎች የግቢው ህንጻዎች ላይ በሌሊት አደረሱት የተባለውን ጉዳት ተከትሎ የአካባቢው ማህበረሰብ ላይ የፈጠረው መጥፌ ሥሜት ነው። እዚህ ላይ ሁሉም የጉራጌ ማህበረሰብ ማወቅ ያለበት ነገር ቢኖር የዚህ ሁሉ ተጠያቂው ወያኔ መሆኑን ነው። ምክንያቱም የኦሮሞ ህዝብ ለብዙ አመታት ከጉራጌ ማህበረሰብ አብሮ የኖረና ተጋብቶ የተዋለደ እንደመሆኑ መጠን ምንም አይነት ችግር እንደሌለባቸው ነው። ሥለዚህ የተፈጠረው ድርጊት በማንም ይሁን በማን ወያኔ ህዝቡን ለማጋጨት ሆን ብሎ የፈጸመው እንጂ ከኦሮሞ ምህበረሰብም ሆነ ተማሪዎች ጋር ምንም አይነት ግንኙነት እንደሌለው ነው። ለወደፊትም ቢሆን ጥንቃቄ ልንወስድ ይገባል።
ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!

No comments:

Post a Comment

wanted officials