Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, January 16, 2015

ልዩ የኢትዮጵያ አፈር አንዳርጋቸው ጽጌ (ይናገራል ፎቶ)

አንዳርጋቸው ጽጌ (ይናገራል ፎቶ)


ይህ ታሪካዊ ፎቶ የተገኘው ከጋዜጠኛ መሳይ መኮንን ነው:: አንዳርጋቸው ጽጌን ከነወታደር ልብሱ በረሃ ላይ ያሳየናል:: ፎቶው ታሪካዊ ከመሆኑ አኳያ ሊቀመጥ የሚገባው ነው:: ለዚህም ነው ይናገራል ፎቶ ብለን ያቀረብነው:: ፎቶውን ካሳየን አይቀር ታዋቂው ጸሐፊ ጸጋዬ ገብረመድህን አረአያ ከፎቶው በታች “አንዳርጋቸው ጽጌ ልዩ የኢትዮጵያ አፈር” ሲል በአውስትራሊያ ለሚታተመው አሻራ መጽሔት ላይ የጻፉትን ታሪካዊ ትንታኔም ዘ-ሐበሻ አስተናግዳዋለች::
andargachew Tisge
አንዳርጋቸው ጽጌ ልዩ የኢትዮጵያ አፈር
ከጸጋዬ ገብረመድህን አረአያ
በ1950 ዓ.ም. ደብረብርሀን በሚገኘው የሀይለ ማርያም ማሞ ሁለተኛ ደረጃ ትም ህርት ቤት ስገባ የዓጼ ዘርአ ያዕቆብ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ዳይሬክተር የነበሩ ት አቶ ጽጌንና ባለቤታቸውን በየቀኑ አያቸው ነበር። ወይዘሮ አልታዬ ዘወትር በቀኝ እጃቸው እየደገፉት እሱ ድክ ድክ የሚልም ትንሽ ልጅ አይረሳኝም። የየዕለቱ ትርኢት ስለነበር . . . . ብዬ አልፌዋለሁ።
ከዘመናት በኋላ እኔም አድጌና በመንግስት ስራ ኃላፊነት ቆይቼ ይህቺን አገር የ ሚያናውጡ ሰዎች ወደ ፖለቲካው መድረክ ሲመጡ በመጥረጊያ ከተጠረጉት የጥን ት ጋዜጠኞችና የሚዲያው አመራር አባላት ጋር እዳሪ ስንጣል ያ ልጅ ይመስለኛል ከ ጦቢያ ቢሮ ያገኘኝ። አንዳርጋቸው ጽጌ ከመቼው በወያኔ መርከብ ተሳፍሮ ፣ ከመቼ ው ወርዶ፣ ከመቼው ወደ ተቃዋሚነት እንደተሸጋገረ የፖለቲካው ጉዞ ቅፅበት አልገ ባኝ አለ። የተቀላቀለው ቡድን አካሄድና ይልቁንም “አማራ” በተባለው የህብረተሰብ ክፍል ላይ ያለውን ግልጽ አቋም በመረዳት “የአማራው ህዝብ ከየት ወዴት?” የሚል መጽሀፍ ጽፎ ለህዝብ ሲያቀርብ እኔም ሆንሁ ብዕሩ እልፍ የሚጥለው ጓደኛዬ ሰውነ ት መልካሙ ጥርጣሬ ውስጥ ወድቀን ነበር። ስለዚህ ሰውነት (በብዕር ስምነት ይቆይ ና) “በኢትዮጵያዊነት ላይ የተወረወረ ቦምብ” በሚል ርዕስ የራሱን ቦምብ አፈነዳ። አ ንዳርጋቸው አስተያየት የመስጠት መብታችንን እየጠቀሰ በመሰረቱ ግን “አቶ ሰውነ ት ትክክለኛው ጉዳይ የገባቸው አይመስለኝም” ብሎ ከእኔ ጋር በጦብያ ቢሮ (አክፓ ክ ነው እንባል የነበረው) ደስ የሚልና ምሁራዊ ቅባት የነበረበት ሙግት ገጠምን። ድር። በእኔ በኩል ይህን ድርጅት ፋሽስት ለማለት የፈለግሁት ኢሰብዓዊ አቋሙን ፣ ደ ም የማፍሰስ ሱሱን፣ ለህይወት አንዳች ዋጋ ለመስጠት ያለመፈለግ ዝንባሌውን . . . ለ ማሳየት ነበር። አንዳርጋቸው ደግሞ የተማሪው ፖለቲካ ፍሬ እንደመሆኑ ወደ ክላሲ ካል ትርጉሙ ለመሄድ ነበር የፈለገው። በነገራችን ላይ አንዳርጋቸው በችኮላ ላይ ስለ ነበርና ጊዜም ስላልነበረው ስለፋሺዝም ብዙ ሳንወያይ ተለያየን። ጊዜ ቢኖረው ኖሮ “አብዮታዊ ዴሞክራሲ” ከቤኒቶ ሙሶሊኒ “አቫንቲ” እና ከፋሽዝም የተዳቀለ መሆኑን (ያው መጻህፍት በመጠቃቀስ) አስረዳው ነበር። የተማሪ ፖለቲካና የሶቭየት (ኢምፓ የር) ቀኖናውያን እንደሚሉት “ቀኝ ክንፍ ፍልስፍና” (ኢዲዮሎጂ) አለመሆኑን ለማብ ራራት እሞክር ነበር። በነገራችን ላይ ሙሶሊኒ ሮጦ ከሂትለር ክንፍ ሥር ሳይወድቅ የ ምዕራቡ ዓለም መሪዎች (እነ ሩዝቬልትና የውጪ ጉዳይ ሚኒስትሩ ሐል) ፋሺዝምን እንደ ታላቅ የዓለም ፖለቲካ የዕድገት ማስረጃ አድርገው ያዩት ነበር። ፋሺዝም የመ ጣው እንደ ሬቮሉሲዮን ስለሆነ የቀኝ ክንፍ ፍልስፍና አይደለም። ይህ ክርክር ያልተ ፈጸመና በአጭሩ የቀረ ጭንጋፍ ሙግት ነው። አንዳርጋቸውን በዚህ ዓይነት ሙግት የምዘርር አይደለሁም። እሱ ላቅ ያለ አመለካከትና ትንፋሹ ሳይቀር ሕይወት ያለው ነ ው። በዓለም አቀፍ የቅንጅት ኮሚቴ ውስጥ አብረውት የሠሩ ዘመዶችና ወዳጆች አሉ ኝ። ይሳሱለታል። “አንዱ . . .አንድዬ . . . አንዳርግ . . .” ይሉታል። የቅንጅት አመራር አባላት በወያኔ ወኅኒ ዓለም በተወረወሩ ጊዜ በሳምንት ውስጥ ለቢቢሲ ሰባት ቀናት መግለጫ ሲሰጥ ሰምቼዋለሁ። በበሰለ አሳብ ፣ በጠራ ቋንቋና በጨዋ አንደበት። ይህ ብቻም አልነበረም ፤ በወቅቱ የአፍሪካ ህብረት ዓመታዊ ስብሰባ በአክራ ሲካሄድ የጋ ናን ሚዲያ በተለይ፣ እና የአፍሪካ መገናኛ ብዙሀንን በአጠቃላይ በቁጥጥሩ ስር አው
ሎበኢትዮጵያላይእየተካሄደያለውን የፖለቲካ፣ የኢኮኖሚ፣ የማህበራዊ ሰዕ ልበሚያስደንቅአኳኋንሲያቀርብየነ በረጀግናነው።አንድመቶየፕሮፖጋን ዳ ሰራዊት የማይችለውን የአትላስ ሽክ ምብቻውንበአስገራሚሁኔታያከናወ ነልዩፍጥረትነው።እኔደግሞየዚህን ሥራአስቸጋሪነትበልዩልዩገጽታውአ ውቀዋለሁ ባይ ነኝ።
“ተራራ አንቀጠቀጥን . .” የሚሉ የ መሣርያ አምላኪዎችና ባሩድ ነካሾች ይ ህንታላቅነፍስ-የኢትዮጵያነፍስናከ ኢትዮጵያ ጎን የወጣ ልጅ -ከአስመራ እ ስከዱባይ…ከየመንእስከደቡብአ ፍሪካ….ከእንግሊዝአገርእስከአውስ ትራሊያናአሜሪካወዘተባሰማሯቸው የስለላናየአፈናጓዶችአማካኝነትዓለ ምን ሲያካልሉ ከርመዋል። ቁጥር ስፍ ርየሌለውገንዘብምአፍስሰዋል።በመ ጨረሻምዱባይ፣አስመራ፣ደቡብአፍ ሪካ ያሉት የቆስጤ ሴረኞች … የምስራ ች ተባብለዋል። እነሆ ውቡ ወፍ ተጠ ምዷል። የትግሉም ሆነ የዓለምም ፍጻ ሜግንአይደለም።አይሆንምም።አን ዳርግየከፈለውሰማዕትነትበሚቀጥሉ ትየኢትዮጵያትውልዶችበክብርይወ ሳል።ለአዲሱዘመንአውራጀግናበማ ግኘታችን ልንኮራ ይገባናል።
እግዚአብሄርይከበር-ስለአንዳርጋ ቸው!አገሮችበታሪካቸውትልልቅፈተ ና ያጋጥማቸዋል ። ሕዝብ በችግር ሰዓ
ትይጠራራል። እንደዚህ ላስቀምጠው። – በጭንቅ ሰዓት ፣ በፈተና ጊዜና ቀን የጎደለ በ ሚመስልበት ወቅት ከማዕበሉ ጋር የሚታገልና ድልን የሚያስገኝ ፤ ካልተሳካም በድፍ ረቱ ፣ በልበ ሙሉነቱ ይህን ያህል የማይባል ረቂቅ ድልን የሚያቀዳጅ ሰው ይሻል። በ ደሙና በማይነገር – በማይበገር ጥንካሬው አማካይነት ወጀቡን የዋኘ ፣ ማዕበሉን ጸጥ ያደረገና የሚያደርግ ፤ ለዛሬው ትውልድ የነጻነት ብልጭታ ያሳየ (የሚያሳይ) ፤ ለመ ጪው ከውስጡ ብርሀኑ ቦግ ያለ የትግልን ችቦየሚያቀብል (ያቀበለ) ሰው ይሻል።
የህንድ የመጀመሪያው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀዋህርላል ኔህሩ በታላቁ የዓለም ሰው በማህተመ ጋንዲ (በአክብሮት ጋንቲጂ) ሥርዓተ ቀብር (በሂንዱ ልማድ ቀብር ሳይሆ ን የማቃጠል ሥርዓት ነው ያለው) ላይ ሲናገሩ የተጠቀሙበትን አንድ ሐረግ ልሰርቅ አፈልጋለሁ። ለአንዳርጋቸው ጽጌ ለመስጠት! “ጋንዲ ልዩ አፈር ነው። ከእኛም ልዩ የ ሚያደርገው ልዩ አፈርነቱ ነው።” ብለዋል። እኔ ራሴ መንቀሳቀስ የማይሆንልኝና በማ ንኛውም የአገሪቱ ታሪክ ላይ ይህ ነው የሚባል አሻራ ለማሳየት የማይሆንልኝ ቧጋች ነ ኝ። ሰዎችን የማወቅ ዕድል ግን አለኝ። ጀግና ብቻ ሳይሆን ባንዳና ምንደኛም አውቃ ለሁ። ተጎልቼ ይህን የመሳሰለውን ወግ እጠርቃለሁ። አላጋንንም።
አንዳርጋቸው እንደማናችንም ከአፈር -ከኢትዮጵያ አፈር ተፈጥሯል። እእ! ከኢትዮጵያ ልዩ አፈር! ስለዚህ ‹ልዩ ሐረግ› የኔህሩን ሽንት ይባርክ! የአንዳርጋቸው ጠላፊዎችና አሳሪዎች የጀግና መንፈስ የላቸውም እንጂ በክብር የ ሚጠብቁት ልዩ እንቋቸው በሆነም ነበር። ሚኒልክ የጎጃሙን ንጉ ስ ምርኮኛቸውን የተንከባከቧቸው በክብር በመጠበቅ ነበር። ወያ ኔዎች ከፈሪ ልብ የተቆረጡ ፈሪዎች በመሆናቸው እንጂ አንዳርጋ ቸውን ያንን ያህል የስጋ ስቃይ ባላደረሱበት ነበር። ለትርዒት መ ላልሰው ባላቀረቡትና የደስታቸው ምንጭ ባላደረጉትም
ነበር። እነሱ ዛሬ የሥጋ ቁስልና የመንፈስ ስቃይ የሚግቱት ሰ ው ነገ የታሪካቸው ፈርጥ የሚሆን ልዩ አፈር ይሆናል። ሃሌሉያ! በአጠቃላይ አንዳርጋቸው የነጻነት ተጋድሎውን የተወጣ ፤ ምድ ራዊ መከራን፣ አካላዊና መንፈሳዊ ቅጣትን ሁሉ የተቀበለ፣ትግሉ ን ለሌሎቻቸን በአደራ ያስተላለፈ ታላቅ ነፍስ ነው። ታላቁ ህንዳ ዊ ጋንዲ “ማሀትማ” ይባላል። “የተከበረ ነፍስ” ማለት ነው። የዓለ ም ጌታ እንዳለው ነቢይ በአገሩና በዘመኑ አይከበርም ሆነና አንዳ ርጌ የሚገባውን አክብሮትና አድናቆትን ጠላት በተንጣለለበት አ ገሩ ለማግኘት ባይችልም በውጪው ዓለም የተበተኑና የውስጡ
ንም የሚወክሉ ወገኖች ሁሉ ህዝብ ለማንም ሰጥቶ የማያውቀው ን ክብር ሰጥተውታል። የኢትዮጵያ ጆን ኦፍ አርክ፣ የኢትዮጵያ ማንዴላና ጋንቲጂ ብለውታል። ጠላቶቹ የአገር አጥፊዎች እየተዘ ባበቱበት፣ እየሰደቡትና እንደ “ጊኒ ፒግ” መላልሰው በቴሌቪዥ ን እያቀረቡት ነው። ልዩ ወፋችንን—ናይቲንግኤላችንን ባሰቡ ቁ ጥር መንፈሳቸውን የሚያሸብር አንዳች ስሜት ተጣብቷቸው ቆይ ቶ መያዙንና በእጃቸውመግባቱን ያለማመን ችግር ደርሶባቸዋል። “ሶባጅ – ሳቬጅ!” ፍሬደሪክ ኤንግልስ ወዳጁና ጓዱ ስለነበረው ካ ርል ማርክስ በቀብሩ ሥነ ሥርዓት ላይ የተናገረው ምስክርነት ት ዝ ይለኛል። The best hated man ይለዋል። (ከሁሉ የበለጠ የ ተጠላ ሰው እንደማለት ነው።) በወቅቱ በተፈጠሩም ሆነ በኋላ በተነሱ ትውልዶች ዘንድ ግን ካርል ማርክስ The best hated man ብቻ ሳይሆንThe best loved man ሆኗል። አንዳርጋቸው ጽጌ በእጃቸው በገባ ሰዓት ማራኪዎቹ ወያኔዎች የተሰማቸውን ደ ስታ ጣኦታቸውና የሴረኞች ሁሉ አባት የሆነው አምባገነን ከሞተ በት ዕለት ኅዘን ጋር ማስተያየት ይቻላል። አዎን አንዳርጋቸው በ ወያኔዎች ለወያኔዎች የቀትር ጋኔን ነበር። የሚያስፈራ ነፍስ – እ ንኪያስ The most hated man ለኢትዮጵያ ሰፊ ህዝብ ደግሞ The most loved man! ይታደለዋል እንጅ …በዚህም መሰረት ይቀጥላል።
አበበ አረጋይ …በላይ ዘለቀና አሞራው ውብነህ፣ ጅማ ሰንበቶ፣ በቀለ ወያ፣ አብዲሳ አጋ ሲደመር ሲደማመር ቅዱስ ያሬድ፣ ዮፍታሄንጉሴ፣ ዶክተር ዓለመወርቅ . . . ነው። አ ላበዛሁበትም። ክብር ሁሉ አልከመርኩ በትም። ቢሆንልኝ ከነጋ ድራስ ተሰማ እሸቴ ጋር “እንደምን አድርጌ ከፍቼ ላውጣው” እያ ልኩ አቀነቅን ነበር።
ጀግኖች የኢትዮጵያ ወጣቶችና ጸጥ ወዳለው ዓለም የምትሸ ጋገሩ አእሩግ! ናፖሊዮንም ተማርኳል።ታላቁ ጄነራልና ጦረኛ መ ሪ። ያንን ታላቅ የጦር መሪና ገናና የዓለም ገዢ የማረከው እንግሊ ዝ ደግሞ ጀግንነትን የማድነቅ፣ ሰብዐዊ መብትን የማክበር ባህል -ድንቅ ባህል ባለቤት ስለሆነ አክብሮ ነበር የያዘው። ናፖሊዮን ከ ሴንት አልባ አምልጦ እንደገና ለመቶ ቀናት ፈረንሳይን መርቷል። ማን ያውቃል የዴስቲኒን አድራሻ! ማን ያውቃል የዴስቲኒን የፍጻ ሜ ምዕራፍ? የዚህን ወጣት ታሪክ ከሥር መሰረቱ የሚያወጉ ወዳ ጆቹና የትግል ተካፋዮች እንዳሉ አያጠራጥርም። በመድረክና እን ደኔም በመስኮቱ ንግግር ፣ ራቅ ብሎም በመሄድ የከፈለውን መስ ዋዕትነት በጨረፍታ ለምናውቀው አንድ መደምደሚያ ላይ እንደ ርሳለን። አንዳርጌ የሚከበር ፣ የሚወደድና በአእምሮው ትልቅነት ፣ በሰብአዊነቱና በአርቆ አሳቢነቱ – ማናቸውንም የነጻነት መስዋዕ ትነት ለመክፈል ባሳየው ቆራጥነቱ የሚደነቅ ነፍስ ነው። እንደሱ ያሉ ሰዎች ከጊዜያቸው በፊት መጥተው ፈተናን ሁሉ ይቀበላሉ። መንፈሱንና ስጋውን ለአምላክ እንዳስረከበ ደካማ ሰው እግዚአብ ሄርን የምለምነው አንድ ነገር አለኝ። ሲድራቅ ፣ ሚሻቅና አብድና ጎን ከሚንቀለቀለው እሳት አራት ሰው አድርጎ በፍጹም አቸናፊነ ት ያወጣቸው አምላክ ምን ይሳነዋል? በወያኔ እስር ቤት የሚንገዋ ለል አንበሳ በሕልሜም በውኔም ይታየኛል። እናንተስ ጎበዝ! በክ ርስቶስ ላይ ያሾፉ፣ የሾህ አክሊል በራሱ ላይ የደፉበት ፣ እስኪደ ክማቸው የገረፉት፣ ጎኑን የወጉት የሰው አራዊትና አራዊት ሰዎች ሥዕል አይመጣባችሁም? “ሶባጅ! ሳቬጅ!” “አኒማሌ” አል ጣልያ ን! ለወያኔዎች አንድ ምስጢር ልተውላቸው እወዳለሁ። “አንዳር ጋቸው ጽጌ መንፈስ ነው።”
ይህን ትንቢት ተቀበሉኝ። አምላካችን ለዚች ሀገር እንደማ ዕዘን ድንጋይ ሆነው ሕዝቡን የሚያገለግሉ መሪዎች ይሰጠናል። የሰራዊት ጌታ የምህረት ተስፋ ነው። እንደ ድንኳን ካስማ የሆኑ አስተዳዳሪዎችና እንደ ጦር ሜዳ ቀስት የሆኑ የጦር አዛዦችን ይ ሰጠናል። ብርቱ የሆኑ ጀግኖችን እንጠብቃለን። ከላይ ከጸባዖት! ከመሬቲቱ ከኢትዮጵያ ማኀጸን።እነዚህ ደግሞ የኢትዮጵያን ጠላ ቶች ረግጠው ከመንገድ ጭቃ ጋር እንደሚለውሱ ያደርጋል – ማ ን? የኃያላን ኃያል! የጌቶች ጌታ! ትዕቢተኞች ይዋረዳሉ። ዕብሪተ ኞች ይንኮታኮታሉ። (ከነቢዩ ኢሳያስ የትንቢት ቃል ያዳቀልሁት ነው።)
የአንዳርግ “ሌጋሲ” – ኑዛዜና ቅርስ ነው። የትውልድ ቅርስ፣ የትግል ቅርስ … የመስዋዕትነት ቅርስ! በአንዳርጋቸው ላይ የሚፈ ጸ መውን ኢሰብዓዊ ድርጊት ሁሉ ሳስበው ከጥንት ጀምረው ኢ ትዮጵያን ከሰለጠነው ዓለም ጋር ለማሰለፍ ብዙ መስዋዕትነትን የ ከፈሉ ሰዎች እነ ሎሬንዞ ታዕዛዝ፣ ተስፋዬ ተገኝ፣ ተክለ ሃዋርያት ዋየህ፣ ሐኪም ወርቅነህ እሸቴ ቢሞቱ፤ እነ ሐዲስ ዓለማየሁ፣ ቢ ትወደድ ዘውዴ ገብረ ሕይወት፣ እነ አማኑኤል አብርሀም… በህይ ወት ቆይተው ኢትዮጵያ የገባችበትን የኋሊት ጉዞና ቅድመ መሳፍ ንት ዘመን አገዛዝ አይተውታል። የተጓዙበትን ርቀት ሜዳ ስለሚ ያስታውሱ (ለምሳሌ የባርያ አስተዳዳሪነትን ለማስቀረት የተደረገ ውን ያነሧል) በኢትዮጵያ አዲስ የባርያ ስርዓት የገባ ይመስላል። እንደቀድሞው በዓለም አቀፉ አካል ቁጥጥር ቢደረግ እኮ ከድርጅ ቱ ከሚባረሩ አገሮች ግንባር ቀደም የምትሆነው የእነ ኃይለማርያ ም ኢትዮጵያ በሆነች ነበር። ኢትዮጵያ ዛሬ የእነ ኃይለማርያም ናት። ነገ ነው የደቂቀ አንዳርጋቸው የምትሆነው።
አንዳርጋቸው ጽጌ በወያኔ ዓለም አቀፍ ሴራ ከተያዘበት ዕለት ጀምሮ በተለይ በውጪ ያለው ኢትዮጵያዊ በነቂስ ወጥቶ የት ግል ቃል ኪዳን ሲያደርግ ይታያል። ይኽ ደግሞ የሚቀጥል ነው። ሕዝብ በራሱ አነሳሽነት ተንቀሳቅሶ በራሱ መፈክር አቋሙን ሲገ ልጥ ለማየት የታደልንበት አንድ አጋጣሚ የአንዳርጋቸው ሌጋሲ ይመስለኛል። “እኔ አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ” የሚለውን ከኢትዮጵያ ጋር የተካሄደ መሐላ በግንቦት ሰባቶች በድርጅታዊ አሰራር የመጣ መስሎ ይታይ ይሆናል። አይደለም። ሕዝቡ ጀግንነቱ፣ ወኔው፣ ወ ንድነቱ፣ የተሟሟቀበትና የተነሳበት ነበር ለማለት ይቻላል። በእ ኔ በኩል ምርኮ ተብሎ የተጠራውን “ክተት” ለማለት እወዳለሁ። …. ያገሬ ሕዝብ ጆሮ ይሰጠኝ ይሆን?
http://www.zehabesha.com/amharic/archives/38097

No comments:

Post a Comment

wanted officials