Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, January 14, 2015

የኢሳት ባልደረባ የሆነው የጋዜጠኛ ወንድማገኝ ጋሹ ባለቤት ወይዘሮ አበባ መልሰው ከሶስት ህጻናት ልጆች ጋር ከኢትዮጰያ ተባረረች።

ኢሳት ዜና :-የሶስት ዓመት ህጻንን ጨምሮ ከሶስት ህጻናት ልጆች ጋር ለእህቷ ስርግ ወደ ኢትዮጰያ አቅንታ የነበረችውና ላለፉት 20 ቀናት በአዲስ አበባ የቆየችው ወይዘሮ አበባ፤ ከነ ልጆቿ ቦሌ አውሮፕላን ማረፊያ ታስራ እንድታድር ከተደረገች በሁዋላ ነው ከሀገር
የተባረረችው።
በእህቷ ሰርግ ላይ በርካታ ደህንነቶች ሲከታተሏት እንደነበረ የገለጸችው ወይዘሮ አበባ፤ በማግስቱ በቤተሰቦቿ ቤት ሳለች
ሁለት ደህንነቶችና አራት ፖሊሶች በመምጣት ከሶስት ዓመት ህጻን ልጇ ጋር እያዋከቡ ወደ አውሮፕላን ማረፊያ ይዘዋት
እንደሄዱና እዛ ባለ ቢሯቸው ውስጥ እንዳሰሯት ተናግራለች። ደህንነቶቹ አክለውም ፦<<ወንጀለኛ ነሽ፤ባለቤትሸ ኢሳት ላይ
መስራት እስካላቆመ ድረስ ኢትዮጰያ የመኖር መብት የለሽም እንዳሏት ተናግራለች::
የኢሳት ጋዜጠኛ የሆነው የወደማገኝ ጋሹ ባለቤት ወይዘሮ አበባ ለህታቸው ሰርግ ወደ አዲስ አበባ ባቀኑበት ወቅት በዘመዳቸው መኖርያ ቤት ውስጥ የደህንነት አባሎች መተው ከሶት ልጆቻቸው ጋር በመያዝ አዲስ አበባ ኤርፖርት ውስጥ ካሳደርዋት በሃላ በቀጥታ አገር ለቃ እድትወጣ አርገዋታል ወይዘሮ አበባ የሶስት አመት ልጅዋን ታቅፋ ነበር ከሌሎች ሁለት ልጅወችዋ ጋር ኤርፖርት ውስጥ ታስራ ያደረችው ባለቤትዋ ወደማገኝ ጋሹ ለኢሳት መስራቱን እስካላቆመ ድረስ ወደ ኢትዮጵያ መግባት እደማትችል በደህንነት ሃይሎቹ እደተነገራት ገልፃለች ወይዘሮ አበባ እደተናገሩት የስዋና የሶስት ልጅዎችዋ ፓስፖርት ላይ ወደ ኢትዮዽያ እንዳይገቡ እደተመታበት ገልፀዋል

No comments:

Post a Comment

wanted officials