Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, January 23, 2015

አንዳርጋቸው ጽጌ ከሆንን እስከ ምን? ከAbraham Z,Taye

አንዳርጋቸው ጽጌ ከሆንን እስከ ምን? ከAbraham Taye
የግንቦት 7 ዋና ጸሃፊ የነበረው ጀግናው አቶ አንዳርጋቸው  ጽጌ በፋሺስት ወያኔ እጅ ከወደቀ  ወዲህእኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ”ሁላችንም አንዳርጋቸው ነን” የሚሉ ተተኪ ሰዎች ተበራክተዋል። አንዳንዶች እንደፌስቡክ ባሉ ድረገጾች ሳይቀር ስማቸውን አንዳርጋቸው ጽጌ ብለው  ስሙንም ፎቶውንም በመጠቀም አንዳርጋቸው ነን ሲሉ ይታያሉ።
አንዳርጋቸው ጽጌ ነን ስንል ስሙን ይዘን በማህበራዊ ድረገጾች በመጥራት ሲቀጥልም ፎቶውን በትልቅ ፍሬም አስርተን በየአደባባዩ ሰልፍ በመውጣት ባለፈ መሆን እንዳለበን ለማሳሰብ ከወጣትነቱና ከ አረጋዊነቱ ሁለት ጉልህ ክስተቶቹን በመምረጥ እንድንማርበት  ይሄ ጽሁፍ ተዘጋጅቷል።
በወጣትነቱ
የነጻነት ትግልን የጀመረው ገና በአፍላ ዕድሜው ነው። የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቱን ከቀሰመበት ከተፈሪ መኮንን ት/ቤት የኢንጅነሪንግ ትምሀርቱን ከተከታተለበት የሃይለስላሴ/ አዲስ አበባ ዩኒቨርሲቲ ተማሪ እያለ ንጉሱን ለመገለበጥ ከተወጠነው ታዋቂው የተማሪዎች ንቅናቄ አቀንቃኞች  አንዱ ነበር።
የዘመኑ ወጣቶችስ አንዳርጋቸው ጽጌ ነን ካልን አምባገነኑን የወንበዴ ስርዓት ለመናድ ይህ ነው ተብሎ የሚጠቀስ እንቅስቃሴ እያደረግን ነን ወይ? የሚል ጥያቄ አዕምሮዬ  ዘወትር  ይመጣል።
1960ዎቹ በነበረው አብዮት የባሌና የጎጃም ገበሬዎች ንጉሱ ላይ ካደረጉት አመጽ በተጨማሪ በመሃል ሃገር አብዮቱን ካቀጣጠሉት መስዋዕትም ከሆኑት ከተማሪዎቹ እንደ ጥላሁን እንደ አለልኝ ወዘተ ቆራጦች ላለመሆን ምን ያዘን?
ያኔመሬት ላራሹ” ይሁን ማለት አንገብጋቢ አጀንዳ ነበር። አሁንም የባሰበት ሁኔታ ነው ያለው። መሬታችን ለህንድ ለፓኪስታን ኢንቨስተሮች እየተሰጠ ከመኖሪያም እያፈናቀሉን ነው። ከከተማም ከገጠርም ዕትብታችን ከተቀበረበት ሲያፈናቅሉን ተመጣጣኝ ካሳ አይሰጠንም።
የዘውድ ስርዓታቸው ሲገረሰስባቸው  ያኔ የነበሩት  ነገስታቱም መኳንንቱም ኢትዮጵያዊ ስሜት የነበራቸው ቅንጣትም መሬት ለውጭ ያልሰጡ በቅኝ ያልተገዛች ኢትዮጵያን ዳርድንበሯን ያስከበሩ መሆናቸው የማይካድ ሃቅ ነው።ዘመነኞቹ ቅኝ ገዢዎቻችን ግን ዳር ድንበሯን ያስረከቡ ኢትዮጵያችንን እያፈርሱ ያሉ  ዘረኛ ፋሺስት ባንዳዎች ናቸው።
ይህንን ጸረ ኢትዮጵያ ኣቋም ያለውን አገዛዝ  ወያኔን ብቻ ሳይሆን የደርግንም ስርኣት በመቃወም ኢ ህ አ ፓን የተቀላቀለ ጀግና አርበኛ ነበር አቶ አንዳርጋቸው በወጣትነቱ። በቀይሽብር ታናሽ ወንድሙን አምሃ ጽጌን ያጣው አንዳርጋቸው በስደት ምድረ አውሮፓ እንግሊዝ በውርዝውናው ተጠልሏል። እኛም አንዳርጋቸው ጸጌ ነን ስንል አሱን የሆንነው እንደ አንዳርጋቸው ለስደት የተዳረግን በመሆናችን ብቻ እንዳልሆነ ማሳየት አለብን።
ምክንያቱም እሱ  በዘመነ ደርግም በዘመነ ኢህአዴግም ስለ ኢትዮጵያ ነጻነት ስለ ሰባዊ መብት ስለ ሃገር አንድነት ከማሰብ ፤ከመስራት የማይቦዝን ትልቅ ስብዕና ያለው ነው።
በራሱ አንደበት ከተናገረው ውስጥ ወያኔዎች በጣም የሚፈሩት እሱ የነሱን ደካማ ጎን በጣም ያውቃል ብለው ስለሚሰጉ ነው። የወያኔን ጠንካራና ደካማ ጎን አጥንተን ጨርሰናልን? ደርግ እንደተወገደ ሃገር አለኝ ብሎ ከጉያቸው ገብቶ ለሁለት አመት ያልበለጠ በአዲስ አበባ መስተዳድር አባላቸው ሳይሆን ሰርቷል። ዳካማነታቸውን አይቶ ዘረኝነታቸውን ነቅፎ መውጣቱ ለሆዳም የወያኔ ካድሬዎችም የሚያስተላልፈው ትልቅ መልዕክት አለ። እስከመቼ ባንዳ ባንዳ ሆናችሁ ትኖራላችሁ ይላቸዋል መልዕክቱ።ከተራ የወያኔ ካድሬ እስከ መከላከያው ሰራዊት ወንድሞቹ ሲገደሉ ዝም ብሎ ከማየት ጥይት ከማቀበል አምባገነኑን ስርዓት ነቅፎ እንደ አንዳርጋቸው መውጣት እኔም አንዳርጋቸው ጽጌ ነኝ ስንል የሚሰማንን  ቢያንስ የህሊና ነጻነትን ያጎናጽፋል።
በ አረጋዊነቱ
1997 ምርጫ ዋዜማ ባወጣው  “ነጻነትን የማያውቅ ነጻ ኣውጪ” መጽሃፍ የቅንጅት አንድነትና ለዴሞክራሲ ፓርቲ ሲመሰረት የተጋበዘ ከዚያም ዝዋይ ታስሮ ከተፈታ በኋላ የቅንጅት ታሳሪዎች እንዲፈቱ የተባበሩት መንግስታትን የኣውሮፓ ህብረትን ሳይታክት የጎተጎተ ከዚያም የግንቦት 7  የፍትህ የነጻነትና የዴሞክራሲ ንቅናቄ መስራችና ዋና ጸሃፊ መሆኑን ስናይ ምሁራን ተሰኝተው ለሃገራቸው በይፋ ከመስራት የሰነፉ አዛውንቶች በምንም መስፈርት የማይደርሱበት ዕንቁ ሰው ነው። እነዚህ ሰዎች እንኳን አንዳርጋቸው ጽጌ ነን ሊሉ ራሳቸውን ነጻ ለማውጣት ይቅርና ስለነጻነት ሰለዲሞክራሲ ቢያንስ በብዕር ስም  ለመጻፍ ካልሞከሩ የታሪክ ተወቃሾች ናቸው። አንዳርጋቸው ሸምግሎ እንኳ ጉልበቱን እያሳየ ነው።
እኛም ብንሆን አንዳርጋቸው ጽጌ ነን ከማለታችን ባለፈ የታሰሩት ይፈቱ የመሬት ቅርምቱ ይቁም ሰብዓዊ መብት ይከበር ብለን በሰላማዊ ሰልፍ መላ አለምን ከማጨናነቃችን በዘለለ ኢትዮጵያ ሆነ ኤርትራ መሬት ላይ ወርደን ብረት እስከማንሳትና ወያኔን  በአካል እስከመጋፈጥ ድረስ ልንታመን ይገባል።



በንጽጽር ለማጠቃለል ያህል  አቶ አንዳርጋቸው ከሞቀው የኣውሮፓው ኑሮ ቤተሰቡን ልጆቹን ትቶ በረሃ ለበረሃ ሲንከራተት በየመኖች ለወያኔ ተላልፎ የተሰጠው ኢየሱስ ክርስቶስ የሰውን ልጆች ለማዳን ከሰማይ ወደምድር ወርዶ በይሁዳ ለሰቃዮቹ ተላልፎ በመሰጠቱ ለሰው ልጆች ሁሉ ያጎናጸፈውን ነገረ ድህነት ያንጸባርቃል። አንድርጋቸው ጽጌ ነን ስንል ተደላድሎ በምዕራቡ አለም መኖር ሳይሆን ዝቅ ብሎ ለኢትዮጵያ ሲሉ ኢትዮጵያ ውስጥ መገኘት ነው። እንደሱ ከንግስናቸን ዝቅ ብለን  በጫካ ፋቲክ የምንለብሰው፥እንጨት የምንፈልጠው፥ዉሃ የምንቀዳው አንዳርጋቸውን ነጻ ለማውጣት ሳይሆን ራሳችንን ነጻ ለማውጣትና በሃገራቸንም ሆነ በሌላው ሃገር እንደፈለገን ሳንታፈን  የመውጣት የመግባት መብት እንድናገኝ መሆኑ የሚሰመርበት ጉዳይ ነው።
አንድርጋቸው ጽጌ ነን ስንል እሱ ከሰላሳ አመት በላይ እንደተሰደደው እኛም ሰደትህን ቀምሰናል ወይም እሱ ነጻነት የማያውቅ ነጻ አውጪን መጽሃፍ እንደጻፈ ሁሉ እኛም የድረ ገጽ አርበኛ ሆነናል በማለት ብቻ ሳይሆን እሱ አሳዳጆቹን ምሳቸውን ለማቅመስ ወደመሬት እንደሄደ ሁሉ እኛም በመሬታችን ኢትዮጵያ የሚጨበጥ ስራ መስራት ይጠበቅብናል።
አቶ አንዳርጋቸው ከውርዝውና እስከ አረጋዊነቱ መላ ህይወቱን ስለ ኢትዮጵያ የሚያስብ፥ ሰለኢትዮጵያ የሚናገር ሰለ ኢትዮጵያ የሰራ እንደመሆኑ መጠን አንዳርጋቸው ነን ስንል ከሱ አልፈን ውያኔን አስወግደን ለሃገራችን ነጻነት ዲሞክራሲ ፍት ህ እስኪሰፍን ድረስ መሆን አለበት።


                                                 I am Abraham Not Andy ,but Want to do like Andargachew Tsigea!

No comments:

Post a Comment

wanted officials