Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, May 5, 2015

በመተማ በተቃውሞ ላይ የተሳተፉ 2 ነዋሪዎች በፌደራል ፖሊሶች ሲገደሉ በርካቶች ቆሰሉ




ሚያዝያ ፳፯ (ሃያ ሰባት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-
ጎንደር ወገን ሲያንገላታ ውሎል የህውሀት ኢህአዲግ ፖሊስና ፌደራል አምስት ሰው ሲገሉ ስልሳ ሰው የቆሰለ እንዳለ የአይን እማኞች ገልፀዋሎ የአካባቢ ነዋሪዋች ጫካ መግባታቸውንና ምሽት ላይ ጦርነቱ አለመብረዱን ጨምሮ

ዛሬ ሚያዚያ 27 ቀን 2007 ዓም የመተማ ከተማ ነዋሪዎች በህገወጥ መንገድ ተሰርተዋል የተባሉ ቤቶችን ለማፍረስ በሄዱ ቤት አፍራሾችና የወረዳው ባለስልጣናት ላይ ተቃውሞዋቸውን ለማሰማት ቢሞክሩም፣ የፌደራል ፖሊሶች በወሰዱት ጭካኔ የተሞላበት እርምጃ 2 ነዋሪዎች በጥይት ተመትተው ሲገደሉ፣ 3 ደግሞ ለህይወት አስጊ በሆነ ሁኔታ ቆስለዋል። ከ50 ያላነሱ ሰዎች ደግሞ ቀላልና ከባድ ጉዳት ደርሶባቸዋል።

ባላስልጣናቱ ከሚያዚያ 26 ከቀኑ 10 ሰአት ጀምሮ ከ300 ያላነሱ ቤቶችን በማፍረስ ላይ የነበሩ ሲሆን፣ ዛሬ ንጋት ላይም ነዋሪዎች በተኙበት ቤታቸውን በዶዘር ማፍረስ በመጀመሩ፣ ቁጥራቸው በውል ያልታወቁ ነዋሪዎች ህይወታቸው ማለፉ በከተማው ውስጥ በመሰራጨቱ ተቃውሞው ተነስቷል።

የከተማው ነዋሪዎች በባለስልጣናቱ እርምጃ በመበሳጨት ቁጣቸውን የተለያዩ መፈክሮችን በማሰማት ሲገልጹ ከቆዩ በሁዋላ፣ ፖሊስ እርምጃ መውሰድ በመጀመሩ ብዙዎች ከፍተኛ የአካል ጉዳት ደርሶባቸዋል። አንዳንድ ወጣቶች ድንጋይ በመወርወር የሚደርሱባቸውን ጥቃቶች ለመከላከል ቢሞክሩም፣ ፖሊስ ጥይቶችን በቀጥታ ወደ ሰዎች በመተኮሱ ፣ ከአራት ሰአታት በላይ የቆየው ተቃውሞ ተበትኗል።

ፖሊስ ተቃውሞውን በሃይል ለመቆጣጠር ቢችልም የወረዳው ህዝብ በተወሰደው እርምጃ ቁጣውን በመግለጽ ላይ ነው፡፡ የወረዳው ባለስልጣናት የአገር ሽማግሌዎችን በመሰብሰብ ህዝቡን እንዲያረጋጉ ሊያግባቡዋቸው ሞክረዋል።

ነዋሪዎች እንደሚሉት ቤቶቹ ከመጀመሪያውም የተሰሩት በመንግስት ባለስልጣናት እውቅና ነው። ባለስልጣናቱ ጉቦ በመቀበል ከመጀመሪያው ጀምሮ ቤቶቹ ሲሰሩ ዝም ብለው ከቆዩ በሁዋላ፣ አሁን ቦታውን እንፈልገዋለን አፍረሱ ማለታቸው ተገቢ አለመሆኑን ነዋሪዎች ገልጸዋል።

የፌደራል ፖሊሶች በርካታ ወጣቶችን ይዘው አሰሩ ሲሆን ብዙዎች ወደ ሱዳንና ወደ ጫካ በመግባት አምልጠዋል።

በሌላ ዜና ደግሞ በሰሜን ጎንደር ዞን በታች አርማጭሆ ወረዳ ከሳምንት በፊት መቶ አለቃ ጥላሁን የተባለ ፖሊስ የዛብላ ቀበሌ ተወላጅ የሆነ አንድ ወጣት መግደሉን ተከትሎ ፣ 50 የሚሆኑ የዛብላ ቀበሌ አካባቢ አርሶአደሮች ማሰሮ ደንብ ከተማ ላይ የሚገኘውን የፖሊስ ጽህፈት ቤት በመክበብ በፖሊሶች ላይ እርምጃ ወስደዋል። አርሶአደሮቹ በወሰዱት እርምጃ አንድ ፖሊስ ሲገደል፣ በመስሪያ ቤቱ ውስጥ የነበሩት ፖሊሶች አምልጠዋል። አርሶአደሮቹ ገዳዩ ለህግ እንዲቀርብላቸው ጠይቀው መልስ በማጣታቸው ፣ በራሳቸው ተደራጅተው ወደ ከተማዋ ማቅናታቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ገልጸዋል። አርሶአደሮች ወደ አካባቢያቸው በሰላም ቢመለሱም፣ ፖሊሶች አጸፋ እርምጃ ለመውሰድ እንቅስቃሴ ጀምረዋል።

ከ10 ቀን በፊት ደግሞ በደዌ ከተማ የከተማ ወጣቶች 5 የቀበሌ እና የሚሊሺያ አባላትን የጦር መሳሪያዎች በመንጠቅ አምልጠዋል። ወጣቶቹ የወሰዱትን እርምጃ ተከትሎ የመንግስት ታጣቂዎች ፍለጋውን ማጠናከራቸው ታውቋል።

እንዳሁኑ አይነት በጎንደር ከመቶ ጊዜ በላይ ጸረ ወያኔ ጦርነት እየተነሳ ሌሎቻችን ለፍጻሜ ትግል የምናቀጣጥለው መቼ ነው

No comments:

Post a Comment

wanted officials