Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, May 19, 2015

የግንቦት 7 ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ የሆኑት የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እህት ወ/ሮ ብዙአየሁ ፅጌ ለኢትዮጵያ ህዝብ መልዕክት አስተላለፉ!









የግንቦት 7 ንቅናቄ ዋና ፀሐፊ የሆኑት የአቶ አንዳርጋቸው ፅጌ እህት ወ/ሮ ብዙአየሁ ፅጌ ለኢትዮጵያ ህዝብ መልዕክት አስተላለፉ!

እነሆ መልዕክቱን ያንብቡ፤ ሼር በማድረግም ለሁሉም ኢትዮጵያዊ ይደርስ ዘንድ የበኩላችሁን አስተዋጽኦ ታደርጉ ዘንድ በአክብሮት ተጠይቃችኋል!


“ለውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ” ከአንዳርጋቸው ጽጌ እህት (ወ/ሮ ብዙአየሁ ፅጌ)

ይድረስ ለኢትዮጵያ ሕዝብ በኢትዮጵያ ውስጥም ሆነ ከኢትዮጵያ ውጭ እንዳሸዋ ተበትናችሁ የምትገኙ ወገኖቼ እኔ የተጎዳሁትን ያህል እናንተም የተጎዳችሁ መሆናችሁን በተለያዩ ሀገሮች በተደረጉ ሰልፎች ፤ የዉይይት መድረኮች ላይ በንዴት፤ በቁጭት እና በእልኸኝነት በእንባ ስትራጩ በመሃላችሁ ተገኝቼ ያየኻችሁ ሲሆን ይህም በጣም በኢትዮጵያዊነቴ እንድኮራ አድርጎኛል። አንዳርጋቸውም በወያኔ የጨለማ እስር ቤት እየከፈለ ያለውን መከራና መስዋትነት የትም እንዳልወደቀና እንዳልቀረ በማሰብ እጽናናለው።

ዛሬ አንዳርጋቸው ፅጌ በመላው ኢትዮጵያዊያን ዘንድ “የኢትዮጵያ የቁርጥ ቀን ልጅ“፤ “የኢትዮጵያ ልዩ አፈር“፤ “የኢትዮጵያ የበኩር ልጅ ” ወዘተ…. የሚሉ መገለጫዎችን እና መጠሪያዎችን የተጎናፅፈው ታናሽ ወንድሜ አንዳርጋቸው ፅጌ በእኔ እይታ ደግሞ የቤተሰባችን ልዩ ልጅ ነው።

አንዳርጋቸው የቤተሰባችን የመጀመረያ ወንድ ልጅ ስለነበረ ብርቅዬ መሆን የጀመረው የካቲት 1 ቀን 1947 ዓ.ም አዲስ አበባ በሚገኘው ቀዳማዊ ኃይለ ስላሴ ሆስፒታል ከእናታችን ከወ/ሮ አልታዬ ተሰማ ሮቢ እና ከአባታችን ከአቶ ፅጌ ሀብተማርያም ጨሜሳ ከተወለደ ቀን ጀምሮ ነው።

አንዳርጋቸው ለወላጅ አባታችን እና እናታችን፤ ለአያቶቻችን እና ለቅድመ አያቶቶቻችን ፤ ለእህቶቻን እና ለወንድሞቻችን ፤ ለዘመድ አዝማድ፤ ለአብሮ አደግ ጓደኞቹ በአጠቃላይ በአካባቢው ለነበሩት ዘመድ እና ወዳጅ ሁሉ ትልቅ እና ትንሽ ፤ ሐብታም እና ደሃ ፤ ወንድ እና ሴት ሳይል እንዲሁም በትምህርት ቤት አክብሮት እና ትህትና ሲያሳይ የኖረ ነው። የአንዳርጋቸው ሌላው ትልቁ እና አስገራሚው ስጦታዉ ወደር የማይገኝለት ትግስቱ ነው።

በቅርበት ከነበርው አካባቢው ሰፋ ባለው ክልል ወስጥም ቢሆን አንዳርጋቸው ስለ ሀገሩ እና ስለኢትዮጵያ ህዝብ ክብር እና ደህንነት የነበርው የተቆርቋሪነት ስሜት ገና የአንደኛ ደርጃ ትምህርት ቤት ተማሪ ከነበረበት ዘመን የጀመረ ነበር። ለዚህም ነው ዛሬ “ለአንቺነው ነው ሀገሬ ” የሚል ግጥም ለገጠመላት የልጅነት ፍቅረኛው “ኢትዮጵያ” ሲል ልጆቹን ቤተሰቡን እና ጓደኞቹን ጥሎ የሀገርን ጥቅም እየነገደ የቡድን ምቾትን እና ሀብትን በማካበት ላይ የሚገኘውን የዘረኛ ባንዳ ወያኔ መንግስት በቁርጠኝነት ለመታገል የተነሳው።

አንዳርጋቸው አገሩን በበጎውም በክፉም ዘመን የሚያውቃት የ1960ቹ ትውልድ አካል በመሆኑ ነው፡ በዚህም በዚያም የተነሳ ይችን አገር ለማዳን የመጨርሻው ትውልድ እንደመሆኑ ይህንን አደራ ለመሸከም ታረክ የጣለበትን ሀላፌነት ከዚህ የመነጨ ነው ብዬ አስባለው ስለሆነም አንዳርጋቸው ቁጭ ብሎ ከመፅፅት በላይ እራሱን ለዚች አገር የመስዋት ጠቦት አድርጎ ማቅረቡና ታፍኖ ያለው ነጻነት ናፋቂው የኢትዮጵያ ህዝብም ይህንን ተረድቶ በልቡ መሀደር ላይ በክብር የጻፈው በመሆኑ ማንም ምድራዊ ሀይል ምንም አይነት ጥላሸት በመቀባት ሊቀይርው እንደማይችል ባለፉት 10 ወራት የታየው አብሮነት ትልቅ ምስክር ነው።

እነሆ! ይህ ጉዞው ዛሬ በወረበላው የየመን መንግስት ሹማምንት ተባባሪነት በጠላቶቹ እጅ እንዲወድቅ አድርጎታል። አንዳርጋቸው በጠላቶቹ እጅ ከወደቀ አስርኛ ወራቶች በላይ ቢቆጠሩም እስከ ዛሬ ድርስ ከአረመኔዉ ወያኔ አፋኞች ውጭ እና ከፈጣረው በስተቀር የት ስፍራ በምን ሁኔታ እንደሚገኝ የሚያውቅ ሰው የለም።

አንዳርጋቸው በዚህ አይነት አሰቃቂ ሁኔታ ውስጥ መዉደቁ ልቤ ውስጥ የተቀመጠ የእሳት ረመጥ ሆኖ በየቀኑ እያቃጠለኝ ቢገኝም በሀገሬ ኢትዮጵያ ፤ ከአሜረካ እስከ ካንዳ ፤ከጃፓን እስክ ደቡብ ኮረያ፤ ከአዎሮፓ እስከ ደቡብ አፍረካ፤ ከአውስትራሊያ እሰከ እስራኤል እንዲሁም በተለያዩ የአርብ አገራት ባለው የአለማችን ስፋት ውስጥ የሚገኙ ኢትዮጵያን ወገኖቼ ” እኔም አንዳርጋቸው ፅጌ ነኝ !” ፡ “ሁላችንም አንዳርጋቸው ፅጌ ነን” ብለው በመነሳት የወያኔን እና የተባባሪዎቹን እብሪት፤ትዕቢት እና ህገወጥነትን ለማጋለጥ እያደረጉ ያለው ትግል ታላቅ መፅናናትን ይሰጠኛል።

አንዳርጋቸው የትናንሽ ልጆች አባት ከመሆኑ በላይ በተጨማሪ የ 85 ዓመት እድሜ ባለፅጋ የሆኑ አባታችን እዚያው ታፍኖ በተቀመጠበት ኢትዮጵያ ውስጥ ይኖራል። ከዚህ በተረፈ በጣም ከሚወዱት እና ከሚያፈቅሩት ከቅርብ ቤተሰቦቹ አልፎ አሁን ግን በአንዳርጋቸው የሀገር ፍቅር ፤ ለነጻነት ፤ ለፍትህ ፤ ለእኩልነት እና ለዴሞክራሲ የሚታገሉ በሚሊዮን የሚቆጠሩ አባት እና እናቶች ፤ ወድም እና እህቶች ፤ ልጆች አፍርቶ ይገኛል።

ይችን አጭር ፅሁፍ ለመፃፍ ያነሳሳኝ ዋናው ምክንያት ለዚህ በሚሊዮን ለሚቆጠሩ ቤተሰቤ ልባዊ ምስጋናዬን በአንዳርጋቸው ስም ለማቅረብ ነው። በዚህ ክፉ ጊዜ የታየው ቆራጥነት በወያኔ ታፍኖ የተወሰደው ወንድማችንን ሙሉ ነጻነቱን እንዲሁም በወያኔ እስር ቤት እየማቀቁ ላሉት የነጻነት ታጋዮች እንዲሁም መብትና ነጻነቱን ተገፎ በሰፊዉ እስርቤት እየማቀቀ ላለው መላው የኢትዮጵያ ሕዝብ ትግሉን እንደሚቀጥል እና ከግቡ እንደሚያደርስ ባለ ሙሉ ተስፋ ነኝ።

በመጨርሻም ውድ ኢትዮጵያን ወገኖቼ አንዳርጋቸው እና እሱን የመሰሉ የነጻነት ታጋዮች እና የፖለቲካ መሬዎች ካለፍርድ በየስር ቤቱ በግፍ ታጉረው ላሉ ሁሉ እና ለቤተሰቦቻቸው ጭምር ፍጣሪ አምላካችን ብርታቱን ይስጥልኝ። የመጨርሻውም ፍርድ የሚመጣው ከሱ ከእግዛብሄር ስለሆነ ይችን የምንወዳትን የጋራ ሀገራችንን ለመታደግ በጋራ የጀመርነውን በጋራ እንውጣው ስል በወያኔ ጭለማ እስር ቤት ውስጥ በሚሰቃዩት ወገኖች ስም እማፅናለው።

ኢትዮጵያ ለዘላለም ትኑር!!!

ወ/ሮ ብዙአየሁ ፅጌ

No comments:

Post a Comment

wanted officials