Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, May 26, 2015

ኢዴፓ የእሁዱን ምርጫ ውጤት ለመቀበል እንደሚቸገር ገለጸ




የኢትዮጵያውያን ዴሞክራሲያዊ ፓርቲ (ኢዴፓ) ፕሬዘዳንት ዶክተር ጫኔ ከበደ በትናንትናው ምርጫ ፓርቲያቸው ከሞላ ጎደል በሁሉም የአገሪቱ አካባቢዎች ባሉ አባላቱና ታዛቢዎቹ ላይ ጫና ሲደረግባቸው እንደነበር ገለጹ፡፡

አጠቃላይ የምርጫው ሂደት አሳፋሪ ነው ያሉት ፕሬዘዳንቱ በርካታ ምርጫ ታዛቢዎቻችን የታዛቢነት ካርዳቸው ተነጥቆ ከምርጫ ጣቢያዎች ተባረዋል ሲሉ ከሰዋል፡፡ “በዚህ ሁኔታ የሚካሄድ የድምጽ ቆጠራ በትክክል ይካሄዳል ብለን አናምንም፡፡ የዚህን ምርጫ ውጤት ለመቀበልም አስቸጋሪ ሆኖ ነው ያገኘነው” ሲሉ ነው ዶክተር ጫኔ ለድሬ ቲዩብ አስተያየታቸውን የሰጡት፡፡

ከዚሁ የፖለቲካ ዜና ሳንወጣ የሰማያዊ ፓርቲ የህዝብ ግንኙነት ሀላፊ አቶ ዮናታን ተስፋዬ ፓርቲያቸው ለወደፊቱ ከሌሎች ፓርቲዎች ጋር በጥምረት ለመስራት አልያም በርካታ ፓርቲዎችን ባስጠለለው መድረክ ስር ራሱን ለማዋቀር እያጤነበት እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ አቶ ዮናታን ፓርቲው ስለዚህ ሁኔታ ለመነጋገር ራሱን ዝግጁ እንዳደረገ የገለጹ ሲሆን በዚህ በኩል ራሱን ማጠናከር እንደሚፈልግም ጠቁመዋል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials