Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, May 19, 2015

የስኳር ፕሮጀክቶች በፋይናንስ ችግር ምክንያት ሳይሳኩ ቀሩ

የስኳር ፕሮጀክቶች በፋይናንስ ችግር ምክንያት ሳይሳኩ ቀሩ
ሚያዝያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- የህወሃት/ኢህአዴግ መራሹ መንግስት የአምስት ዓመት የዕድገትና የትራንስፎርሜሽን ዕቅዶች መካከል የስኳር ፕሮጀክቶች በዋነኛነት በፋይናንስ እጥረት ምክንያት እንዳልተሳኩ ከስኳር ኮርፖሬሽን
የተገኘ መረጃ ጠቆመ፡፡
በሰኔ ወር 2007 መጨረሻ የሚጠናቀቀው የአምስት ዓመት መርሃግብሩ ከተያዙት ፕሮጀክቶች አንዱ የስኳር ፕሮጀክቶች ሲሆኑ ለፕሮጀክቶቹ ተስፋ ተጥሎባቸው የነበሩት አበዳሪ ተቋማት ገንዘብ ሊሰጡ ፈቃደኛ ባለመሆናቸው ምክንያት ዕቅዱ
ሙሉ በሙሉ ማሳካት ሳይቻል መቅረቱን አመልክቷል፡፡
ከተያዙት ፕሮጀክቶች መካከል ኩራዝ፣ ተንዳሆ፣ በለስ፣ ወልቃይት፣ አርጆ ደዴሳ፣ አዳዲስ ፕሮጀክቶች ሲሆኑ የፊንጫአ፣ ወንጂ/ሸዋ እና መተሃራ የማስፋፊያ ፕሮጀክቶች እንደሚገኙበት የሚታወቅ ነው፡፡
ምንጮች እንደሚሉት ፕሮጀክቶቹ ብድር ባይገኝላቸውም በአብዛኛው በሀገር ውስጥ ከሚገኝ ባንኮች ብድር በጀት ስራቸው የተጀመረ ሲሆን አብዛኛውን የፕሮጀክቶቹን ሥራዎች ልምድ የሌለው በመከላከያ ወታደሮች የሚመራው የብረታብረት
ኢንጂነሪንግ ኮርፖሬሽን (ሜቴክ) ያለአንዳች ውድድር እንዲይዘው ከመደረጉ ጋር ተያይዞ ፕሮጀክቶቹ በወቅቱና በተያዘላቸው በጀት የመጠናቀቃቸው ጉዳይ በባለሙያዎች ጥያቄ ሲያስነሳ ቆይቷል።
በሜቴክ ስር እየተሰሩ ላሉ ፕሮጀክቶች የ2007 በጀት ዓመት ከስኳር ልማት ፈንድ እና ከሀገር ውስጥ ብድር ለበለስ አንድ እና ሁለት 4 ነጥብ 26 ቢሊየን ብር፣ ለኩራዝ አንድ 2 ነጥብ 34 ቢሊየን ብር በድምሩ 6 ነጥብ 56
ቢሊየን ብር እንዲሁም ለተንዳሆ ምዕራፍ ሁለት ስኳር ፋብሪካ ግንባታ 290 ነጥብ 76 ሚሊየን ብር፣ ለከሰም ብር 562 ነጥብ 5 ሚሊየን ብር ፣ ለወንጂ ማስፋፊ ፕሮጀክት ቀሪ ክፍያ 608 ነጥብ 33 ሚሊየን ብር በውለታ
የሚከፈል፣ ለመለዋወጫ የሚከፈል 175 ነጥብ 6 ሚሊየን ብር በጠቅላላው 7 ነጥብ 26 ቢሊየን ብር የተጠየቀ ሲሆን፣ በያዝነው በጀት ዓመት 1 ነጥብ 94 ቢሊየን ብር እንደተከፈላቸው መረጃው ያመለክታል።


No comments:

Post a Comment

wanted officials