« በጉልበት ወደ ዘመናዊነት »
የኢትዮጵያ ምርጫ እና የጀርመን የዘገባ ሽፋን
የኢትዮጵያ ምርጫ እና የጀርመን የዘገባ ሽፋን
እሁድ በመላው ኢትዮጵያ የተካሄደውን 5ኛ ሀገር አቀፍ ምርጫ ለመታዘብ የአውሮፓ ህብረት ልዑካን ወደ ኢትዮጵያ ባይሄዱም ፤ የዶይቸ ቬለን ሬዲዮ እና ቴሌቪዥንን ጨምሮ የጀርመን ጋዜጦች ስለምርጫው ዘግበዋል። የጥቂቱን የጀርመን ጋዜጦች ዘገባ እንደሚከተለው ነበር።
የጀርመን ታዋቂ ዕለታዊ ጋዜጣ « ዙድ ዶይቸ ሳይቱንግ» ስለ የኢትዮጵያ ሀገር አቀፋዊ ምርጫ ሲዘግብ ርዕሱን« በጉልበት ወደ ዘመናዊነት » ነው ያለው። የጠቅላይ ሚኒስትር አቶ ሀይለማሪያም ደሳለኝ ፓርቲ ኢሀዲግ እንደሚያሸንፍ ጥርጥር የለውም ሲል የዘገበው ይህ ጋዜጣ ፤ «ኢትዮጵያ ባለፉት ዓመታት በርግጥ ጥሩ የኢኮኖሚ እድገት ያስመዘገበች ሀገር ብትሆንም አሁንም ድረስ እንደ « ልማታዊ አምባገነን» ነው የምትታየው፣ መንግሥት የኤኮኖሚውን አቅጣጫ ብቻ ሳይሆን ህብረተሰቡንም ይቆጣጠራል ሲልም አትቷል ።ጋዜጣው የሰብዓዊ መብት ተማጋች ድርጅቶችን ዋቢ በማድረግ፤ ሂስ ሰንዛሪ ጋዜጠኞች በሀገሪቱ ቦታ እንደሌላቸው ወህኒ ቤት የሚገኙ ጋዜጠኞችን እና የኢንተርኔት ዘጋቢዎችን በምሳሌነት ጠቅሶ ያብራራል። ጋዜጣው ስለ ሃገሪቱ ልማትም ፅፏል። ምንም እንኳን ልማቱ ዝቅተኛ ደረጃ ላይ የሚገኘው ማህበረሰበብ ጋር ባይደርስም፤ በአዲስ አበባ ትላልቅ ፎቆች እየተሰሩ ስለመሆኑና በቅርቡ የቀላል ባቡር አገልግሎት ስራውን እንደሚጀምር ይጠቁማል።
« ዙድ ዶይቸሳይቱንግ»የኢትዮጵያ ምርጫ ሀተታውን ከማጠናቀቁ በፊትም፤ የተቃዋሚዎች እጣ ፋንታ ከባለፈው ምርጫ ጋር ሲነፃፀር አለመሻሻሉንም አንስቷል። እንደ ጋዜጣው ቀውስ ውስጥ ከሚገኙት ከሶማሊያ እና ከደቡብ ሱዳን ጋር ስትነፃፀር ምዕራባውያን ኢትዮጵያን የተረጋጋች ደሴት አድርገው ስለሚመለከቷት የዲሞክራሲ ርዕስ ሲነሳ ፤ ጆሮ ደባ ልበስ ብለው ያልፉታል።
ሌላው ስለ ኢትዮጵያ ምርጫ የዘገበው «ታገስሻው» የተባለው የጀርመን የዜና ማሰራጫ ነው። «ተቃዋሚ ድምፅ የለውም» በሚለው ርዕሱ፤ የምርጫው አሸናፊ ፓርቲ ኢሀአዲግ እንደሚሆን እንደማያጠራጥር ያትታል። ታገስሻው ከዚህም በተጨማሪ ፤ በቴሌቪዥን ሥርጭቱ እና በድረ ገጹ ከሀገር ሸሽቶ ናይሮቢ ውስጥ ጥገኝነት ስለጠየቀው ጋዜጠኛ የትነበርክ እና ደረሰብኝ ስለሚለው በደል ዘግቧል።
«ፍራንክፈርተር አልገማይነር » የተባለው የጀርመን ጋዜጣም ቢሆን እንደሌሎቹ ጋዜጦች ፤ማን ምርጫውን እንደሚያሸንፍ ግልፅ ነው ይላል፤
« እንደ ብረት የጠጠረ አገዛዝ ባላት ሀገር» በሚለው ርዕሱ ከ457 የምክር ቤት መቀመጫ 456ቱን ኢሀአዲግ ይዞ የመራው ሀገር እንደሆነ በመግለፅ፣ ጋዜጣው ፤ የተቃዋሚዎችን ነፃ አለመሆን እና ብሶት ያትታል። ከዚህም በተጨማሪ ጋዜጣው ፤ ምናልባትም ነፃ ምርጫ ታይቶበታል ያለውን የ97ቱን ምርጫ እና ከዛም በኋላ ስለተነሳው አመፅ እና በወቅቱም ከ200 በላይ ሰዎች ስለመሞታቸው አውስቷል። ከዚህም በተጨማሪ የኢትዮጵያ መንግሥት ፣ አሸባሪ ቡድናትን በመዋጋት የዩናይትድ ስቴትስ ስልታዊ አጋር መሆኑን ጋዜጣው ጠቅሷል ።
©ዶይቸ ቬለ
Wahl-Farce in Äthiopien
Rund 35 Millionen Äthiopier durften ein neues Parlament wählen, doch richtig frei waren die Wahlen nicht. Kritische Journalisten wurden im Vorfeld verhaftet. Die Opposition klagt über massive Schikanen.
In der Hauptstadt Addis Abeba war der Andrang vor den Wahllokalen trotz der aussichtslosen Lage schon am frühen Morgen groß. "Ich habe für die Opposition gestimmt, denn es ist wichtig, dass sie in Zukunft im Parlament besser vertreten ist," erklärte die Studentin Sisay. "Wir wissen alle, dass die Regierungspartei gewinnen wird, aber wir brauchen eine stärkere Opposition".
Die EPRDF von Premierminister Hailemariam Desalegn ist seit 1991 an der Macht. Bei den Wahlen vor fünf Jahren erhielten die Partei und mit ihr verbündete Gruppierungen 99,6 Prozent der Stimmen. Die Opposition bekam zwei Sitze. Und auch bei den aktuellen Wahlen gilt ein Wahlsieg als sicher.
Der Grund dafür ist die starke Unterdrückung von Opposition, Presse und Zivilgesellschaft. Eine Reihe von regierungskritischen Bloggern und Journalisten wurde verhaftet. Politischer Wettbewerb ist den Äthiopiern praktisch fremd. In punkto Meinungs- und Pressefreiheit belegt das Land im internationalen Vergleich einen der hinteren Plätze.
Premier will Markt liberalisieren
Dafür verantwortlich ist Hailemariam Desalegn. Seit drei Jahren regiert der 49-Jährige das Land und Beobachter gehen davon aus, dass er weiter im Amt bleiben wird. Allerdings muss er dafür noch vom neu gewählten Parlament bestätigt werden. Hailemariam wird einem Flügel zugerechnet, der die staatlich regulierte Wirtschaft liberalisieren will. Äthiopien erreicht zwar momentan Wachstumsraten von zehn Prozent, aber mit einem Pro-Kopf-Einkommen von 470 US-Dollar pro Jahr zählt das Land weiter zu den ärmsten der Welt.
Die Wahlbehörden wollen binnen fünf Tagen ein vorläufiges Endergebnis vorlegen. Die Spannung, welche Partei das Rennen gemacht hat, dürfte sich aber in Grenzen halten.
djo/se (afp, dpa, epd)
No comments:
Post a Comment