Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, May 26, 2015

የ2007 ምርጫ ውሎ (ዝርዝር የታዛቢዎች ትዝብት)


የ ምርጫ ውሎ (ዝርዝር የታዛቢዎች ትዝብት)

 የዛሬውን 2007 ምርጫ አስመልክቶ ከተለያዩ የአገራችን ክፍሎች እየተዘገቡ ያሉ ዘገባዎች እናስተላልፋለን። አብዛኞቹ ትዝብቶች በነገረ ኢትዮጵያ የተዘገቡ ሲሆን፤ ሌሎቹ ደግሞ የግል ትዝብት እና እይታዎችን ያካተቱ ናቸው።

———————-

በጉደር አምቦ ጸጥታው ደፍርሷል::ምርጫው ቆሟል::

በአቦ በባድዮ ጉደር አምቦ ምርጫ ጣቢያዎች ምርጫውን ከቁጥጥር ውጪ ያደረጉ ችግሮች የተፈጠሩ ሲሆን በየምርጫ ጣቢያዎቹ የኢሕአዴግ የቅስቀሳ ፖስተሮች ተለጥፈዋል::ይህን ተከትሎ በጉደር ከፍተኛ የሆነ የጸጥታ መደፍረስ ተፈጥሯል::በታዛቢዎች እና በምርጫ ባለስልጣናት መካከል ከፍተኛ አለመግባባቶች ተፈጥረው እስከ ድብድብ ተደርስል::‹‹ከንብ ውጭ ምልክት የለም፡፡ ከዛም ካርድ ይቀዳሉ፡፡ ሶስት ቀበሌዎች ተዘዋውሬ አይቻለሁ፡፡ መምህራን ስለሚጠይቁ ችግር እየደረሰባቸው ነው፡፡ ይህ ምርጫ ይበላል?›› ኦሮሚያ ክልል አደሬ ጮሌ ቀበሌ

——————-

‹‹ከ8 ሰዓት በኋላ ካርዱን ራሳቸው ነው እያጠፉ እያስገቡ ያሉት፡፡ ማንን ነው የምትመርጡ ሲባል የምንመርጠውን እኛ እናውቃለን ያሉት ተደብድበዋል፡፡ በተለይ አንዱ ይህን የሞተ መንግስት አልመርጥም ብሎ በመናገሩ ክፉኛ ተደብድቧል፡፡ ህዝብ በዱላ ሊያልቅ ነው፡፡›› ከስናን ወረዳ

——————-



ገዳም ሰፈር ምርጫ ጣቢያ 1 እና ምርጫ ጣቢያ 9 ሰማያዊ ፓርቲ በዕጣ ምክንያት ዕጩ ባለማቅረቡ ሰማያዊ የለም የተባሉ 10 ወጣቶች ‹‹ሰማያዊ ከሌለማ ማንንም አንመርጥም›› ብለው ሲወጡ ታፍነው ታስረዋል፡፡ ከደጀን ‹‹ትናንት ቤቴ ተከቦ አደረ፡፡ እንደምንም ምርጫ ጣቢያ ልመርጥ ስሄድ መምረጥ አትችልም ተብዬ ተመለስኩ፡፡ የቀበሌ አመሮች ናቸው የሚመርጡት›› ቄስ ዋልተንጉስ አባተ የሰማያዊ ፓርቲ የክልል ምክር ቤት ዕጩ

——————-

‹‹ጋሞ ጎፋ አርባ ምንጭ ከተማ ብርብር ምርጫ ክልል የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎችን አዋክበው እንዳይታዘቡ አድርገዋል፡፡ ካቢኔ ኮሮጆው ክፍል ድረስ ገብተው ኢህአዴግ ላይ ምልክት እንዲያደርግ ጫና አድርገዋል፡፡ በተለይ ሴቶችንና ሽማግሌዎችን በግዳጅ ነው ያስመረጧቸው፡፡ በአጠቃላይ በጋሞጎፋ የህዝብ ታዛቢዎች የተመረጡት በኢህአዴግ ነው፡፡ ይህን ቀድመንም ተናግረናል፡፡›› አቶ ወንድሙ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ

——————-

በደቡብ ወሎ ደጋን ከተማ በሚደረገው ምርጫ መራጩን ተከትለው በመግባት ንብን እንዲመርጡ እያስገደዱ መሆኑን እና አንዳንድ በተለይም ሴቶች በፍርሀት እንዳሏቸው ሲያደርጉ አብዛኛው ግን የቻለ የፈለገው ሲመርጥ ግማሹም ካርዱን አበላሽቶ እየወጣ ነው የሚል መረጃ ከስፍራው ደርሶናል።

——————-

በወረባቦ ወረዳ በቢስቲማ ከተማ በሚካሄደው ምርጫ ህዝቡ እየተስፈራራ ኢህአደግን እንድመርጡ እየተደረገ ነው የሴቶችን ካርድ አቶ መሀመድ አደም የተባለው የወንዶችን ደግሞ የሱፍ የተባለው ሚስጥር ቤት ተከትለው እየገቡ ንብ ላይ ምልክት አድርጉ በማለት እያስገደዱ ነው::

——————-

ገዳም ሰፈር ምርጫ ጣቢያ 1 እና ምርጫ ጣቢያ 9 ሰማያዊ ፓርቲ በዕጣ ምክንያት ዕጩ ባለማቅረቡ ሰማያዊ የለም የተባሉ 10 ወጣቶች ‹‹ሰማያዊ ከሌለማ ማንንም አንመርጥም›› ብለው ሲወጡ ታፍነው ታስረዋል::

——————-

እኔ ያለሁት ቦረና/ያቤሎ ነው። እኔ በመረጥኩበት ጣቢያ ደስ የሚል ምርጫ የሚያሰኝ ነገር ነበር። በዚያው ከተማ በሌላ ጣብያ የመረጡ ሁለት የምቀርባቸው ሰዎች የነገሩኝ ነገር ግን እጅግ የሞደብር ነው። 1ኛው “ንብ ላይ x አድርግ ሲሉኝ እምቢ ብዬ የምፈልገው ላይ ምልክት አደረኩ” ሲለኝ ሌላው ግን “ፈርቼ ንብ ላይ ምልክት አደረኩ” አለኝ። በዚያ ጣቢያ የተቋሚ ፓርቲዎች ታዛቢ የሌለ ሲሆን፣ አንዱ ካድሬ በቋሚነት ከድምፅ መስጫ ሚስጥራዊ ቦታ ሳይወጣ መራጮችን “ንብ ላይ ምልክት አድርጉ” እያለ በመርዳት መንፈስና በማስፈራራት ሰው የማይፈልገውን ኢህአዴግ እያስመረጠ እንደሆነ ነግረውኛል። አንድ መራጭ ከቦረና

——————-

ከሚሴ አማራ ክልል ኦሮሚያ ልዩ ዞን ለምርጫ ውድድር የቀረቡት ኢህ አዲግና መድረክ ሲሆኑ:: ሁሉም ሰው ኢህ አዲግን እንዲመርጥ ከፍተኛ ጫና በመደረግ ላይ ይገኛል :: የድምጽ መስጫ ሚስጥራዊ ቦታዎች በታዛቢዎች በኩል ያለው ክፍት በመሆኑ ማን እንደሚመርጡ በቀላሉ ማየት ይችላሉ :: የኢህአዲግ ካድሬዎች በ እድሜ የገፉ አባቶችና እናቶች ቆይ ላግዘሽ ወይም ላግዝህ በማለት ኢህ አዲግን ይመርጣሉ :: እኔ እመርጣለሁ ብለህ እምቢ እንዳትል የምታውቃቸው ሰዎች ናቸው:: ነገ መጥተው ሊሳስሩህና ሊስገርፉህ ይችላሉ:: መድረክን ለመምረጥ ብንሄድም የመምረጥ እድሉን አልሰጡንም::

——————-

”….ከሚስጥራዊ ቦታዎች በፊት ወንበሮች አሉ ተረኛው ምልክት አድርጎ እስኪወጣ አረፍ ብለህ የምትጠባበቅበት ወንበሮች አሉ። በዛ ግልፅ ወንበሮች ላይ አረፍ ብዬ እያለሁ አንዱ የወረዳው ካድሬ መጥቶ እስክፕሪቶ ሰጠኝ እዛ ውስጥ ስለሌለ ይሆን ብዬ አሰብኩና ተቀበለኩት ። አፍጥጦ እያየኝ “ግዜ ለመቆጠብ እዚሁ ምልክት ማድረግ ትችላለህ” አለኝ። “ችግር የለውም መጠበቅ እችላለሁ” አልኩት በትህትና። ” ጉዱ ካሣ ዘመቀሌ

——————-

የህዝብ አስተያየት ‹‹አንድ ቦታ ሰብስበው ንብን ብቻ እንድንመርጥ እየነገሩን ነው›› ከጀሞ ኮምዶሚኒየም ‹‹ካድሬዎች የድምጽ መስጫ ቦታው ድረስ በመግባት ንብ ላይ ምልክት እንድናደርግ እያስገደዱን ነው፡፡›› ሰሜን ወሎ ወቄት ወረዳ ‹‹መሳሪያ ይዘው እያስፈራሩን ነው፡፡›› ጎዛመን ወረዳ ‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ነው የምንመርጠው ስንል እነሱ በግድ ንብ ላይ ምልክት እያስደረጉን ነው፡፡ ኮረጆው ብቻውን መቀመጥ ሲገባው አንድ ካድሬ አጠገብ ነው ያስቀመጡት፡፡ በተለይ የምንጠይቀው ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠሩብን ነው፡፡›› ምስረቅ ጎጃም ስናን ወረዳ ‹‹ወረቀቱ በቀበሌው ሊቀመንበር በኩል ነው እየተፈረመ የሚገባው፡፡ ምርጫው የተጭበረበረ ነው፡፡›› ሰሜን ወሎ ቆቦ ወረዳ ‹‹በጣም የሚያሳዝን ነው፡፡ ምርጫውን ሌሊት ነው የጨረሱት፡፡›› ምስራቅ ጎጃም ቢቡን ወረዳ ‹‹ህዝቡ በፌደራል ተከቦ ከመረጥክ ንብን ምረጥ ተብሎ በግድ ነው የመረጠው፡፡ ምርጫ የሚያሰኝ አንድም ነገር አላየሁበትም›› ከዱር ቤቴ ከተማ

——————-

በባሌ ከተማ አስመራጮች ሁሉም ኢህአዴጎች ናቸው። የመድረክ ታዛቢዎች እስር ቤት ይገኛሉ። ፓሊስ ጣቢያ ሄደን አረጋግጠናል።ይህ አካባቢ በብዛት ሙስሊሙ ስለሚገኝበት መድረክ ያሸንፋል ብለው ስለፈሩ፣ ኢህአዴጎች ህዝቡን እያስፈራሩ ይገኛለ። ከአካባቢው ነዋሪ።



——————-

በወረባቦ ወረዳ በቢስቲማ ከተማ በሚካሄደው ምርጫ ህዝቡ እየተስፈራራ ኢህአደግን እንድመርጡ እየተደረገ ነው የሴቶችን ካርድ አቶ መሀመድ አደም የተባለው የወንዶችን ደግሞ የሱፍ የተባለው ሚስጥር ቤት ተከትለው እየገቡ ንብ ላይ ምልክት አድርጉ በማለት እያስገደዱ ነው::

——————-

ምርጫው ሳይጀመር በምስራቅ ጎጃም ተጠናቆዋል።

በምስራቅ ጎጃም በግንደወይን ከተማ ባሉ የምርጫ ጣቢያዎች የገጠር ቀበሌዎች ላይ ምርጫው እየተካሄደ ያለው በብአዲን ካድሬዎችና በምርጫ አስፈፃሚዎች መምረጫው ወረቀት ላይ እየተሞላ ኮሮጆ ውስጥ ብቻ መክተት ሆኖዋል የመራጩ ድርሻ ለማስመሰል እንኳን ያልተሞከረበት የምርጫው ሂደት ነው።

——————-

በገርባ ከተማ አንድ መራጭ መታሰሩ ተገለጽ :: ንብ እንዲመርጥ ሲገደድ አልመርጥም በማለቱ ምርጫ በማደፈርስ ተከሶ መታሰሩ ተገለጸ::

——————-

መታወቂያ የሌላቸው ነዋሪዎች እየመረጡ ነው ወረዳ 20 ምርጫ ጣቢያ መታወቂያና የምርጫ ካርድ የሌላቸው ነዋሪዎች እየመረጡ ነው ተብሏል፡፡ ነዋሪዎች በዚህ አካባቢ ነዋሪ ከሆኑ ስድስት ወር ሆኗቸዋል በሚል ያለ ቀበሌ መታወቂያ እየመረጡ እንደሆነ ተገልጾአል፡፡ ንፋስ ስልክ ላፍቶ 5ና 8 ምርጫ ጣቢያ ላይ መታወቂያና የምርጫ ካርድ ያልያዙ ነዋሪዎች እየመረጡ እንደሆነ የአካባቢው የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ የሆነው አቶ እስክንድር ጥላሁን ገልጾአል፡፡ በዚሁ ምርጫ ጣቢያ ፖሊስ ምርጫ ጣቢያው ውስጥ እየገባ መረጃ እየወሰደ እንደሆነ ተገልጾአል፡፡ ‹‹ፖሊስ ህግ ከማስከበር ውጭ ምርጫ ጣቢያ ውስጥ ሊገባ አይችልም፡፡ መታወቂያ ስጠይቀው ግን ያሳየኝ የፖሊስ መታወቂያ ነው፡፡ ትክክል እንዳልሆነ ስንነግራቸው ሊሰሙን አልቻሉም፡፡›› ሲሉ ተዘዋዋሪ ታዛቢው ገልጸዋል፡፡ በዚሁ ወረዳ በሌላ ምርጫ ጣቢያ ላይ የተመደቡ ታዛቢም ብዙ መታወቂያችን ጠፍቶብናል ከሚሉት በተጨማሪ መታወቂያ እንደሌላቸው የሚያምኑ ሰዎች እየመረጡ ነው ብለዋል፡፡ ‹‹እኔ መታወቂያ የሌላቸው መምረጥ እንደሌለባቸው ስከራከር በብሎክ ነው የተሰጠን፡፡ መታወቂያ እንደሌለን እያወቁ በብሎክ ከፍለው ምርጫ ካርድ ሰጥተውናል፡፡ ስለሆነም ቀድመውም ያውቁታል›› በሚል መምረጥ እንዳለባቸው ገልጸውልኛል ብለዋል፡፡ በተመሳሳይ ወረዳ 14 ምርጫ ጣቢያ 9 አንድ ግለሰብ ምርጫ ጣቢያው ውስጥ በመግባት ‹‹ንብን ምረጡ›› እያለ መራጩን ሲያስገድድ ተደርሶበታል ተብሏል፡፡

——————-

በደቡብ ወሎ ደጋን ከተማ በሚደረገው ምርጫ መራጩን ተከትለው በመግባት ንብን እንዲመርጡ እያስገደዱ መሆኑን እና አንዳንድ በተለይም ሴቶች በፍርሀት እንዳሏቸው ሲያደርጉ አብዛኛው ግን የቻለ የፈለገው ሲመርጥ ግማሹም ካርዱን አበላሽቶ እየወጣ ነው የሚል መረጃ ከስፍራው ደርሶናል።

———————-

የህዝብ አስተያየት

‹‹አንድ ቦታ ሰብስበው ንብን ብቻ እንድንመርጥ እየነገሩን ነው›› ከጀሞ ኮምዶሚኒየም

‹‹ካድሬዎች የድምጽ መስጫ ቦታው ድረስ በመግባት ንብ ላይ ምልክት እንድናደርግ እያስገደዱን ነው፡፡›› ሰሜን ወሎ ወቄት ወረዳ


‹‹መሳሪያ ይዘው እያስፈራሩን ነው፡፡›› ጎዛመን ወረዳ

‹‹ሰማያዊ ፓርቲ ነው የምንመርጠው ስንል እነሱ በግድ ንብ ላይ ምልክት እያስደረጉን ነው፡፡ ኮረጆው ብቻውን መቀመጥ ሲገባው አንድ ካድሬ አጠገብ ነው ያስቀመጡት፡፡ በተለይ የምንጠይቀው ላይ ከፍተኛ ጫና እየፈጠሩብን ነው፡፡›› ምስረቅ ጎጃም ስናን ወረዳ



‹‹ወረቀቱ በቀበሌው ሊቀመንበር በኩል ነው እየተፈረመ የሚገባው፡፡ ምርጫው የተጭበረበረ ነው፡፡›› ሰሜን ወሎ ቆቦ ወረዳ
‹‹በጣም የሚያሳዝን ነው፡፡ ምርጫውን ሌሊት ነው የጨረሱት፡፡›› ምስራቅ ጎጃም ቢቡን ወረዳ
‹‹ህዝቡ በፌደራል ተከቦ ከመረጥክ ንብን ምረጥ ተብሎ በግድ ነው የመረጠው፡፡ ምርጫ የሚያሰኝ አንድም ነገር አላየሁበትም›› ከዱር ቤቴ ከተማ

———————–

ባህርዳር ላይ የድምፅ አሰጣጡ ሚስጥራዊ አይደለም ተባለ

ባህርዳር ከተማ ላይ ድምጽ አሰጣጡ ሚስጥራዊ አለመሆኑን መገንዘባቸውን የሰማያዊ ፓርቲ ተዘዋዋሪ ታዛቢዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በአንድ የምርጫ መስጫ ሳጥን ላይ ሶስት ሰዎች በአንድ ላይ ድምጽ ሲሰጡ እንዳገኟቸው የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ አቶ አዲሱ ጌታነህ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ በአንድ ምርጫ ሳጥን ላይ አንድ ጊዜ የሚመርጡትም በካድሬዎች 1ለ5 የተጠረነፉት ነዋሪዎች መሆናቸውን ለማወቅ እንደቻሉ ገልጾአል፡፡
መራጩን በምን መልኩ መምረጥ እንዳለበት የሚያስተምሩት ሰዎችም ኢህአዴግ ላይ ‹‹ኤክስ›› እንዲሁም ሰማያዊ ላይ ‹‹ራይት›› ምልክት እንዲያደርጉ በማስተማር ለሰማያዊ የሚሰጠው ድምጽ ዋጋ እንዳይኖረው እያደረጉ እንደሚገኙ፤ አቶ አዲሱ ገልጾአል፡፡ እጩዎችና ታዛቢዎችም ወከባ እየደረሰባቸው ነው ተብሏል፡፡ ዕጩዎችን ‹‹ትፈለጋላችሁ›› እየተባሉ እንደሚያዋክቡ የገለጸው አቶ አዲሱ፤ እሱን ከነጋ ሶስት ጊዜ ያህል ‹‹ትፈለጋለህ›› እያሉ እንደገና እንደተውት ገልጾአል፡፡
በሌላ በኩል ምርጫ ቦርድ በአንድ ምርጫ ጣቢያ የሚመርጠውን ህዝብ ቁጥር 795 ነው በሚል የገለጸ ቢሆንም በአሁኑ ወቅት በአንድ ምርጫ ጣቢያ ይመርጣሉ ተብለው የተመዘገቡት 1300 መሆናቸውን፤ አቶ አዲሱ ገልጾአል፡፡

——————————-

‹‹የደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ ተማሪ ነኝ፡፡ ካለ ንብ ሌላ የሚመረጥ ምልክት አያሳዩንም፡፡ ሌላ ምልክት አሳዩን ስንል ከፈለክ ይህን ምረጥ ከዚህ ውጭ የሚመረጥ የለም ነው የሚሉን፡፡ ይህ ምኑ ምርጫ ይባላል?›› ከደብረታቦር ዩኒቨርሲቲ

———————

ኢትዮጵያ – የምርጫ ቀጣና ሳይሆን የጦርነት ቀጠና እየመሰለች ነው

የኢትዮጵያ ሕዝብ ለዉጥ ይፈልጋል። የነገዉን ምርጫ እንደ መሳሪያ በመጠቀም፣ ለዚህ ግፈኛ መንግስት ተቃዉሞዉን ይገልጻል ተብሎ ይጠበቃል። ህወሃት/ኢህአዴግ ህዝብ እንደተፋው ያውቃል። ከዚህም የተነሳ በብዙ ቦታዎች ፣ የምርጫ ጣቢያዎች ሁሉ ተዘግተዋል። እንደ አዲስ አበባ፣ ባህር ዳር ያሉ ከተሞች የጦርነት ቀጠናዎች ይምስሉ። ቁጥሩ እጅግ በጣም ብዙ የሆነው የታጠቃ ኃይል ተሰማርቷል። ቁጥራቸው እጅግ በጣም ብዙ የሆነ ኢትዮጵያዉይን እየታፈሱ ነው።

————————–

ይሄ በአገዛዙ ላይ የደረሰው ዉጥረትና ውርደት ፣ የሕዝብ ትግል ያመጣው ነው። ይሄ የሕዝብ የትግል መነሳሳት ደግሞ በአገራችን የነጻነት ጮራ የሚፈነጥቅበት ጊዜ ቅርብ መሆኑ የሚያሳይ ነው። በርግጥም የሕዝብ ጉልበት ያሸንፋለ። እነርሱ ጥቂቶች ናቸው። እነርሱ እስከ አሁንም የኖሩት እየከፋፈሉ ነው። እኛ ግን ሚሊዮኖች ነን። እኛ ግን ዘር፣ ኃይይማኖት ሳንለይ አንድ ሆነናል።

—————————-

ከወደ ባህር ዳር አሁን በደረሰን መረጃ መሰረት የምርጫው አየር ፌደራል ፖሊሳማ ሆኗል ፌደራል ፖሊሶች በየ ቀበሌዎች ጉራንጉሩ ተሰግስገው ሕብረተሰቡን የማሸበር ስራቸውን ጀምረዋል። ፍጥጫው አይሏል። በተለይ ወጣቶች እየታደኑ ለእስር እየተዳረጉ መሆኑንም ሰምቻለሁ። ትላንት ለሐጫም ተብሎ በጸያፍ ስድብ የተዘለፈ ሕዝብ ነገ ማንን ሊመርጥ እንደሚችል ይታወቃል። ለዛም ይመስላል የሕወሓት ግልምጫ ቀድሞ ባህር ዳር ላይ መክተሙ። ህዝቡም “እንግዲህ ሕወሓት ሆይ ብአዴን ያስጥልሽ ከሆነ እስኪ እናያለን!” እያለ ነው።

——————-

በደቡብ ጎንደር ዞን ደብረታቦር ከተማ የሰማያዊ ፓርቲ የክልል ምክር ቤት ዕጩ የሆኑት አቶ መለሰ ተሸመ ትናንት ማታ በደህንነቶች ታፍነው የተወሰዱ ሲሆን በአሁኑ ወቅት የት እንዳሉ አልታወቀም፡፡ በተመሳሳይ በደቡብ ጎንደር ስቴ ወረዳ ሁለት የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች ከፍተኛ ድብደባ እንደደረሰባቸው ታውቋል፡፡ ሁለቱም ታዛቢዎች እግርና እጃቸው ላይ ከፍተኛ ስብራት አጋጥሟቸው ሆስፒታል መግባታቸው ታውቋል፡፡

—————————–

ወሎ ውስጥ ብአዴን መራጮቹን እያስገደደ ነው

ወሎ መርሳ ውስጥ የኢህአዴግ ካድሬዎች 1ለ5 ለጠረነፏቸው መራጮች እየመረጡ ነው ተብሏል፡፡ በቦታው ሌሎች መራጮችንም እያስገደዱ መሆኑ ተገልጾአል፡፡ ዋድላ ወረዳ በሚገኙ ምርጫ ጣቢያዎችም የብአዴን ካድሬዎች በግዴታ እያስመረጡ መሆኑን ከታዛቢዎች የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በተመሳሳይ ሰሜን ቆቦ 09 ቀበሌ የቀበሌው ሊቀመንበር መራጮች ብአዴንን መምረጥ እንዳለባቸው እያስገደደ መሆኑን መራጮቹ ገልጸዋል፡፡

——————————

ከፍተኛ የደህንነቶች እና የፖሊስ ወከባ ሲደርስበት የሰነበተው የወረዳ 17 የሰማያዊ ፖርቲ ታዛቢ የነበረው ወጣት ኤፍሬም ሰለሞን ለመታዘብ ወደ ምርጫ ጣቢያ በመሄድ ላይ ሳለ በፖሊስ ታፍኖ መታዘብ አትችልም በፖሊስ የምትፈለግ ነህ በማለት ወረዳ 17 ቦሌ በሚገኘው በቁም እስረኝነት ፖሊስ ጣቢያ ታስሮ ከአንድ የመድረክ ታዛቢ ጋር ቃል ለመስጠት እየጠበቁ መሆኑን ምንጮች ገልፀዋል።

——————————–

ስልጤ ዞን ላንፎሮ ወረዳ ሱልጣን ኤገኑ የተባሉ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ ታስረዋል፡፡
ታዛቢዎች ቤታቸው ተከቦ ወደ ምርጫው እንዳይሄዱ ተደርገዋል፡፡ ካድሬዎች በር ላይ ቆመው መራጩ ማንን መምረጥ እንዳለበት እንደሚናገሩ ተገልጾአል፡፡

——————————

አዲስ አበባ ወረዳ 11 የምርጫ አስፈፃሚዎች መራጮች ኢህአዴግን እንዲመርጡ ግፊት እያደረጉ መሆኑን የሰማያዊ ፓርቲ ተዘዋዋሪ ታዛቢዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በዚሁ ምርጫ ጣቢያ አምህ ደስታ ት/ቤት ምርጫው ከመጀመሩ በፊት የምርጫው ወረቀት የአስፈጻሚው ፊርማና ማህተም ሊደረግበት ሲገባ ማህተምም ፊርማም እንዳልተደረገበት ተዘዋዋሪ ታዛቢዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ የምርጫ አስፈፃሚዎች ለምን እንዳልተፈረመበትና ማህተም እንዳልተደረገበት በተጠየቁበት ወቅት ‹‹ስራ ስለበዛብን ነው›› የሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡

—————————–

በወልቂጤ በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች መራጮች ጣት ላይ የሚቀባው ቀለም በሶፍት የሚለቅ መሆኑን ማረጋገጥ ተችሏል።በበርካታ ምርጫ ጣቢያዎች ለእናቶች የንብ ምልክት የተደረገበትን ወረቀት እየተሰጣቸው ነው።ወያኔ በከተማው ቀደም ብሎ ያጣውን ድምፅ የተለያዩ የማጭበርበሪያ ስልቶችን በመጠቀም ለማሸነፍ እየሞከረ ነው።

—————————–

ኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች እንዳይገቡ ተደርገዋል
ኦሮሚያ ክልል አርሲ ዞን በቆጅ አንድና በቆጅ ሁለት ምርጫ ክልሎች የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች እንዳይገቡ መከልከላቸውን አቶ ማንደፍሮ ጥላዬ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ በቆጅ አንድ ምርጫ ጣቢያ ላይ 17 የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩዎች እንዳይገቡ ተከልክለዋል አቶ ማንደፍሮ ገልጾአል፡፡ የምርጫ አስፈጻሚው ጋር በመሆን ታዛቢዎች እንዳይገቡ እንዳፈረገም ተገልጾአል፡፡ ታዛዎቹ ማሟላት ያለባቸውን ነገሮች ሁሉ አሟልተው የተገኙ ሲሆን ‹‹አትገቡም›› ከማለት ውጭ ምንም አይነት ምክንያት አልተሰጠም ተብሏል፡፡ በተመሳሳይ በቆጅ ሁለት ምርጫ ጣቢያ በታዛቢነት የተመደቡ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች ከቤታቸውም እንዳይወጡ በሚልሻ በመከበባቸው ምርጫውን መታዘብ ሳይችሉ መቅረታቸውን አቶ ማንደፍሮ ገልጾአል፡፡

———————————

48 የሰማያዊ ታዛቢዎች በቁም እስር ላይ ናቸው::26 ታዛቢዎች ታስረው የታዛቢነት መታወቂያቸውን መለሱ
ዛሬ 12 ሰዓት የጀመረው ምርጫ በወከባ ተጀምሯል፡፡ ኢህአዴግ ካድሬዎች መራጮቹን በመጠርነፍ እንዲመርጡ እያስገደዱ እንደሆነ አዲስ አበባ ውስጥ ከምርጫ ጣቢያ 03 የደረሰን መረጃ ያመለክታል፡፡ በዚሁ ምርጫ ጣቢያ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች እንዳይገቡ ታግደው በማርፈዳቸው ወረቀት ሳይቆጠር ምርጫው ተጀምሯል፡፡ በተመሳሳይ በወረዳ 15 ምርጫ ጣቢያ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች ‹‹አትገቡም!›› ተብለው ወከባ እንደደረሰባቸው የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ የሆኑት አቶ ተገኔ ጌታነህ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡

———————–

በወረዳ 6 ምርጫ ጣቢያ 20 መራጮች ጣት ላይ የሚደረገው መርገጫ ቀለም የሚለቅ እንደሆነ ታውቋል፡፡ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች ቀለሙ የሚለቅ መሆኑን ገልጸው ቃለ ጉባኤ እንዲያዝላቸው ቢጠይቁም የምርጫ አስፈጻሚዎቹ ፈቃደኛ ሊሆኑ አልቻሉም፡፡ ይህ በእንዲህ እንዳለ በሁሉም ምርጫ ጣቢያዎች የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች በገዥው ፓርቲ ካድሬዎችና ደህንነቶች ወከባ እየደረሰባቸው እንደሚገኝና አንዳንዶቹ በወከባው ምክንያት በቦታው አለመገኘታቸውን ዕጩዎቹ ገልጸውልናል፡፡

———————-

ሲዳማ ቦርቻ ወረዳ ደግሞ 26 የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች ታስረው የታዛቢነት መታወቂያቸውን እየመለሱ ሲለቀቁ፣ ሶስቱ መታወቂያን አልመልስም በማለታቸው አሁንም እንደታሰሩ ናቸው፡፡ በጉራጌ ዞን የም ልዩ ወረዳ ደግሞ 48 የሰማያዊ ታዛቢዎች በቁም እስር ላይ መሆናቸው ታውቋል፡፡

———————-

የወረዳ 20 የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ አቶ እስክንድር ጥላሁን ታዘን ነው ያሉ የፖሊስ አባልና አንድ ሲቪል ‹‹መኪናህ ይፈለጋል፡፡ መንጃ ፈቃድህን ስጠን›› በሚል ከቦታ ቦታ እንይነቀሳቀስ መደረጉን ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጾአል፡፡ የአቶ እስክንድር ታዛቢዎች ወደ ምርጫ ጣቢያው ከሌሊቱ 10ና 11 ሰዓት አካባቢ በሚሄዱበት ወቅት ‹‹ከፓርውና ከምርጫ ቦርድ ደብዳቤ ካላመጣችሁ›› በሚል እንዳይገቡ መደረጋቸውን ገልጾአል፡፡ የሌሎች ፓርቲዎች ታዛቢዎች ደብዳቤ እንዲያመጡ ያልተጠየቁ ሲሆን አቶ እስክንድር ምርጫ ቦርድ ደውለሎ በጠየቀበት ወቅትም ‹‹የሰጠናቸው መታወቂያ ብቻ በቂ ነው፡፡ ደብዳቤ አያስፈልግም›› እንደተባለ ገልጸዋል፡፡ ‹‹ደብዳቤ ካላመጣችሁ›› ተብለው የተጉላሉት የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች አብዛኛውን ሂደቶችን መታዘብ አልቻሉም ተብሏል፡፡

——————————-

አዲስ አበባ ወረዳ 11 የምርጫ አስፈፃሚዎች መራጮች ኢህአዴግን እንዲመርጡ ግፊት እያደረጉ መሆኑን የሰማያዊ ፓርቲ ተዘዋዋሪ ታዛቢዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ በዚሁ ምርጫ ጣቢያ አምህ ደስታ ት/ቤት ምርጫው ከመጀመሩ በፊት የምርጫው ወረቀት የአስፈጻሚው ፊርማና ማህተም ሊደረግበት ሲገባ ማህተምም ፊርማም እንዳልተደረገበት ተዘዋዋሪ ታዛቢዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ የምርጫ አስፈፃሚዎች ለምን እንዳልተፈረመበትና ማህተም እንዳልተደረገበት በተጠየቁበት ወቅት ‹‹ስራ ስለበዛብን ነው›› የሚል መልስ ሰጥተዋል፡፡

—————————-

በምስራቅ ጎጃም ዞን ደብረ ማርቆስ ከተማ ለሰማያዊ ፓርቲ ሊታዘቡ የነበሩ የዩኒቨርሲቲ ተማሪዎች የግቢ የኢህአዴግ ድርጅት ጉዳይ ኃላፊዎች ‹‹የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢ ከሆናችሁ ከትምህርት ትባረራላችሁ›› ብለው ስላስፈራሯቸው በቦታው እንዳልተገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ ሌሎች ታዛቢዎችም በትናንትናው ዕለት የታዛቢነት መታወቂያ ከተሰጣቸው በኋላ በደረሰባቸው መከባ ምክንያት በቦታው እንዳይገኙ ተደርገዋል ተብሏል፡፡ በምስራቅ ጎጃም ዞን አብዛኛው የምርጫ ጣቢያዎች አንድ ለአምስት የጠረነፉት የኢህአዴግ ካድሬዎች ለሌላው ሰው እየመረጡ እንደሆነ የሰማያዊ ፓርቲ ም/ የድርጅት ጉዳይ ኃላፊ አቶ በቃሉ አደነ ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡ ጉዳዩን ለምርጫ ቦርድ አሳውቀው ‹‹አሁን እንፈታዋለን!›› ቢሉም እስካሁን አልተፈታም ብለዋል፡፡

No comments:

Post a Comment

wanted officials