4 የሰማያዊ ፓርቲ የምርጫ ታዛቢዎች ተደበደቡ * በክፍለሃገራት ኢሕአዴግ ራሱን በራሱ እየመረጠ ነው
ሰማያዊ ፓርቲ የመደባቸው 4 የምርጫ ታዛቢዎች በገዢው ፓርቲ ተላላኪዎች መደብደባቸው ተዘገበ::
ምስራቅ ስቴ የተመደቡ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎች
1. ታደለ ግዛው (ዳጉት ቀበሌ)
2. እሱ ያውቃል በላይ (ለዋዬ ቀበሌ)
3. ገብሬ ተፈራ (ደንጎልት ቀበሌ)
4. መልካሙ ነጋ (አበርጉት ቀበሌ)
በተጨማሪም ይስማው ወንድሙ የተባለ የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢ በጥይት መሳቱን የሰማያዊ ፓርቲ አስተባባሪዎች ለነገረ ኢትዮጵያ ገልጸዋል፡፡
‹‹ጋሞ ጎፋ አርባ ምንጭ ከተማ ብርብር ምርጫ ክልል የሰማያዊ ፓርቲ ታዛቢዎችን አዋክበው እንዳይታዘቡ አድርገዋል፡፡ ካቢኔ ኮሮጆው ክፍል ድረስ ገብተው ኢህአዴግ ላይ ምልክት እንዲያደርግ ጫና አድርገዋል፡፡ በተለይ ሴቶችንና ሽማግሌዎችን በግዳጅ ነው ያስመረጧቸው፡፡ በአጠቃላይ በጋሞጎፋ የህዝብ ታዛቢዎች የተመረጡት በኢህአዴግ ነው፡፡ ይህን ቀድመንም ተናግረናል፡፡›› አቶ ወንድሙ የሰማያዊ ፓርቲ ዕጩ
‹‹ከ8 ሰዓት በኋላ ካርዱን ራሳቸው ነው እያጠፉ እያስገቡ ያሉት፡፡ ማንን ነው የምትመርጡ ሲባል የምንመርጠውን እኛ እናውቃለን ያሉት ተደብድበዋል፡፡ በተለይ አንዱ ይህን የሞተ መንግስት አልመርጥም ብሎ በመናገሩ ክፉኛ ተደብድቧል፡፡ ህዝብ በዱላ ሊያልቅ ነው፡፡›› ከስናን ወረዳ
‹‹ትናንት ቤቴ ተከቦ አደረ፡፡ እንደምንም ምርጫ ጣቢያ ልመርጥ ስሄድ መምረጥ አትችልም ተብዬ ተመለስኩ፡፡ የቀበሌ አመራሮች ናቸው የሚመርጡት›› ቄስ ዋልተንጉስ አባተ የሰማያዊ ፓርቲ የክልል ምክር ቤት ዕጩ/ከደጀን
ገዳም ሰፈር ምርጫ ጣቢያ አንድ እና ምርጫ ጣቢያ ዘጠኝ ሰማያዊ ፓርቲ በዕጣ ምክንያት ዕጩ ባለማቅረቡ ምክንያት ሰማያዊ የለም የተባሉ 10 ወጣቶች ‹‹ሰማያዊ ከሌለማ ማንንም አንመርጥም›› ብለው ሲወጡ ታፍነው ታስረዋል፡፡
‹‹የኢህአዴግ አባላት ናቸው የምርጫ ወረቀቱን እየተቀበሉ ምልክት የሚያደርጉት፡፡ ታዛቢ የሚባሉት ራሳቸው የኢህአዴግ አባላት ናቸው፡፡›› ከዱር ቤቴ
‹‹ባለስልጣናት ምርጫ ጣቢያው በር ላይ ቁጭ ብለው እጅ ይዘው እያስፈረሙ ነው፡፡ ከኢህአዴግ ውጭ እንመርጣለን ያሉ ወጣቶች ከአካበቢው ተባረዋል፡፡ ችግሩን ለሌሎች ይገልጻል የተባሉ ወጣቶች ስልካቸውን ተነጥቀናል፡፡ እኛ ከአካባቢው ርቀናል፡፡›› ስልጤ ዞን ላንፎሮ ወረዳ አርጢማ ቡላ ቀበሌ
(ነገረ ኢትዮጵያ እንደዘገበው)
No comments:
Post a Comment