Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, May 5, 2015

ጠ/ሚኒስትር ናታኒያሁ ደማስ ፈቃደን አነጋገሩ



ጠ/ሚኒስትር ናታኒያሁ ደማስ ፈቃደን አነጋገሩ

ሚያዝያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሺዎች የሚቆጠሩ ቤተእስራኤላውያን ዘረኝነትን በመቃወም ካለፈው ሃሙስ ጀምሮ የጀመሩት የተቃውሞ ሰልፍ እሁድ ተጠናክሮ ከቀጠለ በሁዋላ፣ የአገሪቱ ጠ/ሚኒስትር ቤንጃሚን ናታኒያሁ ፣ የተቃውሞው
መነሻ የሆነውን ወታደር ደማስ ፈቃደን አነጋግረውታል።
ወታደር ደማስ በእስራኤል ፖሊሶች መደብደቡ በአገሪቱ የሚኖሩትን በተእስረኤላውያንን በእጅጉ አበሳጭቶ ለተቃውሞ አደባባይ አስወጥቶአቸዋል። ቤተእስረኤላውያኑ በአገሪቱ ውስጥ ያለውን ዘረኝነት እጥብቀው የተቃወሙ ሲሆን፣ ቁጣቸውንም የተለያዩ ጠርሙሶችና
ፕላስቲኮችን በፖሊሶች ላይ በመወርወር ገልጸዋል። በፖሊሶችም በቤተእስረኤላውያን ላይ ጉዳት መደርሱን መገናኛ ብዙሃን ገልጸዋል።
እሁድ የተካሄደው የተቃውሞ ሰልፍ በቅርብ የእስራኤል ታሪክ ያልታየ ነው ተብሎአል። ተቃውሞውን ተከትሎ የአገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢትዮጵያውያኑ በአግባቡ አለመያዛቸውን፣ ቁጣውም ለአመታት የተጠራቀመ መሆኑን በመግልጽ ይቀርታ ጠይቀዋል።
ጠ/ሚኒስትሩም ችግሩን እንደሚፈቱ ቃል በመግባት ሁኔታውን ለማረጋጋት እየሞከሩ ነው።

No comments:

Post a Comment

wanted officials