Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, May 22, 2015

በጊምቦ ጎኦታ ከምርጫ ጋር በተያያዘ አንድ ሰው ተገደለ፤ ምርጫው ተላለፈ

በጊምቦ ጎኦታ ከምርጫ ጋር በተያያዘ አንድ ሰው ተገደለ፤ ምርጫው ተላለፈ

71FA3110-8DE1-4347-9601-8D897AF1B4EC_w640_r1_sበደቡብ ኢትዮጵያ ከፋ ዞን በቦንጋ ከተማ ጊምቦ ጎአታ የምርጫ ክልል ከምርጫ ጋር በተያያዘ በተነሣ ግጭት የአንድ ሰው ሕይወት ማለፉና ብዙዎች መቁሰላቸው ተዘግቧል፡፡ ምርጫው ላልተወሰ ጊዜ ተላልፏል፡፡
በደቡብ ኢትዮጵያ ከፋ ዞን በቦንጋ ከተማ አካባቢ ማለት ጊምቦ ጎአታ የምርጫ ክልል ለፊታችን ዕሁድ – ግንቦት 16/2007 ዓ.ም ሊካሄድ ታቅዶ የነበረው የድምፅ መስጫ ቀን ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉን የዞኑ የምርጫ አስተባባሪ በተለይ ለአሜሪካ ድምዕ ራድዮ ተናግረዋል።
በዚህ ተሰናባች የምርጫ ክልል በህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ብቸኛው የግል የፓርላማ አባል ዶ/ር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የሚወዳደሩ ሲሆን በገጠር አካባቢዎች የምረጡኝ ዘመቻዎቸው ያካሄዷቸው ቅስቀሣዎች በፀጥታ ኃይሎችና በአካባቢው መስተዳድር ተባብረው ፈፀሙት በሚሉት ድብደባ አንድ ሰው ተገድሏል፡፡
ሌሎች ከአሥር በላይ መቁሰላቸው ታውቋል።
በዚህም ምክንያት ካሁን በፊት ያሸነፉት ዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ እና ደጋፊዎቻቸው የምርጫ ዘመቻቸውን አቋርጠዋል።
በጊምቦ ጎአታ የምርጫ ክልል ቦንጋ አካባቢ የዶክተር አሸብር ወልደጊዮርጊስ የምርጫ ምልክት ላም ስትሆን ገዥው ፓርቲ ደኢህዴግ/ኢህአዴግ ዕጩ ዶክተር መብራቱ ገብረማርያም በንብ ምልክት ተፋጠዋል።
ሰማያዊ ፓርቲ፥ ቅንጂት፥ ኢዴፓ፥ መኢአድ፤ መድረክና ሪፓ ፓርቲዎች በምርጫው በመሣተፍ ዝግጅት ላይ የነበሩ ሲሆን የምርጫው ቀን ላልተወሰነ ጊዜ መተላለፉን ተቃውመዋል።
ዝርዝሩን ከተያያዘው የድምፅ ፋይል ያዳምጡ፡፡፡፡http://amharic.voanews.com/

No comments:

Post a Comment

wanted officials