Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, May 5, 2015

በጤናተቋማትአገልግሎትአለመሟላትየእናቶችሞትበእጥፍጨምሯል፡፡

በጤናተቋማትአገልግሎትአለመሟላትየእናቶችሞትበእጥፍጨምሯል፡፡

ሚያዝያ ፳፮ (ሃያ ስድስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-በሀገሪቱካሉት 879 በላይ  የጤናተቋማትውስጥመሰረተልማቶችየተሟሉላቸው 105 ብቻሲሆኑ፣ ከእርግዝናና ከወሊድ ጋር በተያያዘ በየቀኑ 68 ሴቶች በየሰዓቱ ደግሞ 3 እናቶች ህይወታቸው እንደሚያልፍ መረጃዎች ያሳያሉ፡፡
የአብዛኛው እናቶች ሞት የሚከሰተው በደም መፍሰስ፣ በተራዘመ ምጥና በከፍተኛ የደም ግፊት ነው። በአዲስ አበባ ብቻ ከአንድ መቶ ሺ እናቶች መካከል 420ዎቹ ከወሊድ ጋር በተያያዘ ህይወታቸውን ያጣሉ።


በጤና ጥበቃ ሚኒስትር የእናቶችና ሕጻናት  ዳይሬክቶሬት  ዶ/ር ኢክራም መሃመድ  ለእናቶች ሞት ምክንያት ከሆኑት መካከል   85 በመቶ  በጤና ተቋማት አለመኖር የሚመጣ ነው ብለዋል።  የተሟላ የጤና ተቋማት መሰረተ ልማቶች አለመኖሩ ችግሩን እንዳባባሰው ተናግረዋል። ገዢው ፓርቲ የጤና ሽፋኑን በከፍተኛ ደረጃ ማሰደጉን ቢገልጽም፣ የእናቶች ሞት በተፈለገው ፍጥነት አለመቀነሱን መረጃዎች ያመለክታሉ።
የተባበሩት መንግስታት የልማት ድርጅት ሰሞኑን ባወጣው የ2014 ሪፖርት እናቶች በቂ የሆነ የጤና አግልግሎት እንደማያገኙ ገልጿል። ከዚሁ ጋር በተያያዘ ዩ ኤን ዲፒ  በኢትዮጵያ የድህነት ጥልቀቱ ባለፉት 10 አመታት መጨመሩን ይፋ አድርጓል። ኢትዮጵያ በሰው ልጅ ልማት ወይም በእንግሊዝኛው human development index ከ186 አገራት በ173 ኛ ደረጃ ላይ ትገኛለች። ገዢው ፓርቲ ድህነትን ለመቀነስ ባደረገው ትግል መልካም ውጤቶች ቢታዩም የድህነት ጥልቀቱ ግን በከፍተኛ ሁኔታ ጨምሯል ሲል ድርጅቱ ያወጣው ሪፖርት አመልክቷል። 25 ሚሊዮን ኢትዮጵያውያን በቀን ከአንድ ዶላር ባነሰ ወይም  0.60 ዶላር  ህይወታቸውን ይመራሉ።  ከዚህ ከፍ ባለ ሁኔታ የሚኖሩትም ቢሆኑ በምግብ ዋስትናና በባልተጠበቁ አደጋዎች ውስጥ መሆናቸውን ሪፖርቱ አምልክታል።
በአገሪቱ ውስጥ የኢኮኖሚ እድገት ቢመዘግብም፣ እድገቱ ሁሉንም ክልሎች በእኩል ያላደረሰ፣ ለወጣቶች በቂ ስራ ያልፈጠረ ነው ብሎታል።  የአገሪቱ የህዝብ ቁጥር በከፍተኛ ሁኔታ እየጨመረ ከመምጣቱ ጋር ተያይዞ ብዙ ችግሮች ሊከሰቱ እንደሚችሉም አስጠንቅቋል።
አፋር፣ ሶሚሊ፣ አማራና ኦሮምያ ክልሎች በሰው ልጆች ልማት ከመላ አገሪቱ ወደ ሁዋላ የቀሩ መሆናቸውን ዩ ኤን ዲ ፒ ሲገልጽ፣ በአንጻሩ የተሻለ ሁኔታ ውስጥ ይገኛሉ የተባሉት ትግራይ፣ ሃረሪና ድሬዳዋ ናቸው።

No comments:

Post a Comment

wanted officials