ከኢትዮጵያ ሳተላይት ቴሌቪዥንና ራዲዮ የተሰጠ መግለጫ
ባለፉት ጥቂት ቀናት ኢሳት በአሞስ ሳተላይት ወደ አየር መመለሱን መግለጻችን ይታወሳል። ይሁን እንጅ በስልጣን ላይ ያለው አገዛዝ ከደሃው ኢትዮጵያዊ የሚሰበስበውን ገንዘብ በመጠቀም በሚያደርገው ተደጋጋሚ የአፈና ሙከራ የኢሳት የአሞስ ስርጭት እንደገና እንዲቋረጥ ተደርጓል። ባለፉት 5 ዓመታት ሲደረግ የነበረው የአፈና ሙከራና የዲፕሎማሲ ዘመቻ ፣ አገዛዙ ኢሳትን ከምንም በላይ የሚፈራው ሃይል መሆኑን የሚያረጋግጥ ነው።
ምንም እንኳ በኢሳት ላይ በሚደርሰው ተደጋጋሚ አፈና የተነሳ ኢትዮጵያውያን ከፍተኛ የገንዘብ ወጪ እንዲያወጡ መገደዳቸው ቢያሳዝነንም፣ የገዢው ፓርቲ ድርጊት ለነጻነታችንና መብታችን መከበር የምናደርገውን ትግል ይበልጥ አጠናክረን እንድንቀጥል የሚያደርገን ነው።
የህዝብ ሃብት የሆነውን ኢሳት በአፈና እስከመጨረሻው ማስቆም አይቻልም፤ ደጋግመን እንደተናገርነው ኢሳትን ለማፈን የሚወጣውን ወጪ የሚመገቡት አጥተው በየጎዳናው ለወደቁት ዜጎች ዳቦ መግዣ ወይም ስራ አጥተው ስደትን እንደመፍትሄ እየወሰዱ በየበረሃው በአሳዛኝ ሁኔታ ህይወታቸውን ለሚያጡ ወጣቶች ስራ መፍጠሪያ በዋለ ነበር። ባለፉት5 አመታት ኢሳትን ለማፈን የወጣው በብዙ ሚሊዮን የሚቆጠር ገንዘብ፣ ብዙ ትምህርት ቤቶችን ፣ ብዙ የጤና ተቋማትን ፣ ብዙ መንገዶችን በመገንባት የዜጎቻችንን ህይወት በመጠኑም ቢሆን ለመለወጥ ያስችል ነበር፤ ሌላው ቢቀር ቢያንስ የመንግስት ሰራተኛው ለአባይ ግድብ በሚል ተገዶ የሚያወጣውን ገንዘብ መሸፈን ይቻል ነበር። ይህን በማድረግም የህዝባችንን ኑሮ ሲኦል ያደረገውን የኑሮ ውድነት በተወሰነ መጠን መቅረፍ ይቻል ነበር።
አገዛዙ ከደሃው ህዝብ የሚሰበስበውን ገንዘብ ለአፈና ማዋሉ አንድቀን በህግ ፊት እንደሚያስጠይቀው ሊያውቀው ይገባል።
ኢሳት የአሞስ ስርጭቱ ቢቋረጥም በሌሎች ሳተላይቶች ተመልሶ ለመውጣት አሁንም ጥረቱን አጠናክሮ ቀጥሎአል፤ ጥረቱ እንደተሳካ መረጃውን ለኢትዮጵያ ህዝብ የሚገልጽ ሲሆን፣ የኢሳት መረጃዎችን አሁንም በናይል ሳት ላይ በሚሰራጨው ሬዲዮ እንዲሁም በፌስቡክና በኢሳት ዌብሳት ላይ መከታተል የምትችሉ መሆኑን ለማስታወስ እንወዳለን።

ኢሳት
No comments:
Post a Comment