Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, May 14, 2015

በስልጤ ዞን የምሥራቅ አዘርነት በርበሬ ወረዳ ክርስቲያኖች የድረሱልን ጥሪ እያሰሙ ነው


*
.ክርስቲያን መምህራን እና የመንግሥት ሠራተኞችተመርረው እና ተሠቃይተው ወረዳውን እንዲለቁከሥራ ማባረርን ጨምሮ እስራት፣ያለበቂ ምክንያት የደመወዝ ቅጣት፣ ያልተገባ የሥራ ምደባ እና ዝውውር እንዲኹም ‹‹እናርዳችኋለን›› በሚል የግድያ ዛቻይደረግባቸዋል፤
*.የሚያስቀድሱበት እና የሚቀበሩበት ቤተ ክርስቲያን መሥሪያ ቦታ ያገኙት በብዙ ውጣ ውረድ ነው፤የቂልጦ ጎሞሮ ቅድስት ማርያም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያንንለመሥራት በኮሚቴ የተሰባሰቡ ምእመናን በአንድነት ባሉበት ቤትበምሽት ቤንዚን በማርከፍከፍ እሳት ተለቆባቸዋል፤
የወረዳው ቀናዒ ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን፣ የጽንፈኛ እና ዓምባገነን ባለሥልጣናትን በደል ተቋቁመው የሚያሠሯት የቂልጦ ጎሞሮ ቅድስት ማርያም ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን
*.እየተሠራ ባለው ሕንፃ ቤተ ክርስቲያን ላይ‹‹ጉልላት ለምን አስቀመጣችኹ››ሦስት ጊዜ የማቃጠል ሙከራ ተደርጓል በዞኑ ባለሥልጣናት በተደጋጋሚ የሚወቀሱት የወረዳው አስተዳደርና ልዩ ልዩ አደረጃጀቶች ጉዳዩን በውይይት ስም እያድበሰበሱ ክርስቲያኖችን በማይመለከታቸው ጉዳይበደመወዝ ከመቅጣት፣ ከሥራ ከማባረር እና ከመኖርያቸው ከማሳደድውጭ መፍትሔ ሰጭ የእርምት ርምጃ እየወሰዱ አይደለም፤
*.የሚደርስባቸውን በደል ለዞኑ ያሳወቁ እና በጠንካራ ሠራተኝነታቸው ከዐይን ያውጣችኹ የተባሉ የወረዳው ክርስቲያን መምህራን እና የመንግሥት ሠራተኞች‹‹አስወቅሳችኹን››ባሉ የወረዳው አስተዳደር እና የድርጅት ጉዳይ ሓላፊዎች፥ያለበቂ ምክንያት ከሥራ ተባርረዋል፤ የትምህርት ዝግጅታቸውን እና የሞያ ልምዳቸውን በማይመጥን ቦታ በማዛወር ሞራላዊ ጥቃት ተፈጽሞባቸዋል፤‹‹ሀገራችኹ ሥራ ቢኖር እዚኽ አትመጡም ነበር››በሚል ተዘብቶባቸዋል፤
*.በዛሬው ዕለት ለሦስተኛ ጊዜ ከቤቱ ተወስዶ የታሰረው የሕንፃ ቤተ ክርስቲያኑ አሠሪ ኮሚቴ ሰብሳቢ እና ምስጉኑ የቂልጦ ኹለተኛ ደረጃ መሰናዶ ት/ቤትመምህር የማርያም ወርቅ ተሻገር በፖሊስ ጣቢያ እንግልት እና ድብደባ እየተፈጸመበት እንዳለተዘግቧል፡፡የዋስ መብቱ ተጠብቆ ሊፈታ እንደማይችልምከወረዳው ኢንስፔክተር መገለጹን የዓይን እማኞች ተናግረዋል፡፡
*.ይህ መልእክት የደረሳችኹ ወገኖቻችን፤ የሃይማኖት አባቶች፣ የመንግሥት አመራሮች እና መሥሪያ ቤቶች፣ ጋዜጠኞች፣ለሊቢያ ወንድሞቻችን ብቻ አይደለም ለእኛም አልቅሱ፤ እነርሱ ከአገር ወጥተው ነው፤ እኛ ግን በአገራችን ከአዲስ አበባ 220 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ነው የምንገኘው፡፡ፍጹም መሮናል፤ ተሠቃይተናል፤ በጭንቀት እና በስጋት ላይ ነን፤ መቼ ምን እንደምንኾን አናውቅምና ድረሱልን! ! !
* * *
የወረዳው ኦርቶዶክሳውያን ምእመናን፥ ለወረዳ፣ ለዞን፣ ለክልል እና ለፌዴራል መንግሥት የአስተዳደር፣ የፍትሕ እና የጸጥታ አካላት እንዲኹም ለወረዳው ቤተ ክህነት እና ለሃዲያ እና ስልጤ ሀገረ ስብከት ጽ/ቤቶች ያሰራጩትየድረሱልን ጥሪ
Oche Fekadeab Z Ethiopia's photo.

No comments:

Post a Comment

wanted officials