አቶ ኃ/ማርያም ደሳለኝ ከምርጫ ጋር ተያይዞ ሁከትና ብጥብጥ ለመፍጠር ምልክት አሳይተዋል ያሉዋቸውን የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎችና ደጋፊዎች አስጠነቀቁ፡፡
ሚያዝያ ፲፫ (አስራ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-ጠ/ሚኒስትሩ በፓርላማ ተገኝተው ከኢህአዴግ የም/ቤቱ አባላት ለቀረቡላቸውን ጥያቄዎች ምላሽ የሰጡ ሲሆን በዚህ ምላሻቸውም በስም ያልጠቀሱዋቸውን ተቃዋሚዎች አስጠንቅቀዋል።
የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎች ወደምርጫው የገቡት በግማሽ ልብ መሆኑን ፣ የብጥብጥና የሁከት አማራጭ ከተገኘ ያንን ለማካሄድ የሚያስቡ ናቸው ሲሉ ፈርጀዋቸዋል።
” የተቃዋሚ ፓርቲ መሪዎቹ በአንዳንድ አካባቢዎች ከወዲሁ እኛ አሸንፈናል፣ ከተሸነፍን ደግሞ ምርጫው ተጭበርብሮአል፣ ይህንን አውቃችሁ ምላሽ መስጠት አለባችሁ ብለው ሕዝብን እየቀሰቀሱ ነው ” በማለት የተናገሩት አቶ ሃይለማርያም፣ ድርጊታቸው መሪዎችን ሊበላ ይችላል በማለት ከባድ እርምጃ እንደሚወስዱ አስጠንቅቀዋል። የጸጥታ ሃይሎች በቂ ዝግጅት ማድረጋቸውንም ጠ/ሚኒስትሩ ገልጸዋል።
ጠ/ሚኒስትሩ የሻእቢያ ተላላኪዎች የተለያዩ የሁከትና የጸረሰላም እንቅስቃሴ ለማድረግ 24 ሰአታት እንደሚሰሩ ተናግረው፣ እስካሁን ደረስ ህዝቡ ድጋፍ ስለነሳቸውና የመከላከያ ሰራዊት ክህሎት እያደገ በመምጣቱ ሊሳካላቸው እንዳልቻለ ገልጸዋል።
አቶ ሃይለማርያም በቅርቡ በኢህአዴግ ከፍተኛ አመራሮች ተገምግመው መካከለኛ ውጤት ማምጣታቸው መዘገቡ ይታወሳል።
ገዢው ፓርቲ በአገሪቱ ውስጥ በገጠርና በከተማ ያሰማራቸው የፌደራል ፖሊስ አባላት በህዝቡ ላይ የስነልቦና ጫና ከመፍጠራቸው በተጨማሪ ፣ በየአካባቢው በርካታ ወጣቶችና የመንግስት ሰራተኞችን እየያዙ በማስርና በመደብደብ እያሰቃዩ ነው ።

በመላው አዲስ አበባ ልዩ ትኩረት የሚሹ መንደሮች ተብለው በተለዩ ቦታዎች ውስጥ ነዋሪ የሆኑ ወጣቶች እየታፈሱ ነው፡፡ ሰብሰብ ብሎ በየመንደሩ ማውራትና መዝናኛ ቦታ መቀመጥ እጅግ አደገኛ ሆኗል። ከፖሊስ የተገኘ አስተማማኝ መረጃ እንደሚያመለክተው የታክሲ ሾፌሮችና ረዳቶች በከፍተኛ ሁኔታ በአፈናው መነጽር ውስጥ ገብተዋል፡፡ ስራው በትራፊክ ፖሊሶች በኩል የሚሰራ ሲሆን፣ ሾፌሮችን በሰበብ አስባብ ለማሰር ታቅዷል። ቀጨኔ፣ሳሪስ፣ቄራ፣አስኮ፣ፈረንሳይና ሌሎችም ቦታዎች ምሽት ላይ በየታክሲው ” ቶሎ ግባ ሰፈር እየታፈሱ ነው ” የሚሉ የስልክ ድምጾች እየተሰሙ ነው፡፡
በትግራይ ደግሞ በዓፅቢ ወንበርታ ወረዳ በቅስቀሳ የነበሩ የአረና ፓርቲ አባላት ላይ ድብደባ ተፈጽሟል።
ሕድሮም ሃይለስላሴ መቀሌ ሆስፒታል ፣ ወልደ አብራሃ ገብረመድህን ፣ ወልደገብርኤል ሃይሉ እና ነጋሲ ክንፋ በውቅሮ ሆስፒታል፣ ተኝተው በመታከም ላይ ናቸው። ሌሎችም በርካታ የፓርቲው አባላት በመደብደባቸው በህክምና ላይ ይገኛሉ፡፡

No comments:
Post a Comment