Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, May 18, 2015

አንድ በ20ዎቹ የእድሜ ክልል የሚገኝ ወጣት አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ በዝዋይ እስር ቤት ውስጥ ተገደለ

አንድ በ20ዎቹ የእድሜ ክልል የሚገኝ ወጣት አሰቃቂ በሆነ ሁኔታ በዝዋይ እስር ቤት ውስጥ ተገደለ

ሚያዝያ ፲ (አስር) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአዲስ አበባ 22 እየተባለ በሚጠራው አካባቢ የሚኖረው የ25 ዓመቱ ሲሳይ ተሾመ በቅጽል ስሙ ገብሬ ያለፉትን 8 ዓመታት በቃሊቲና በዝዋይ እስር ቤቶች እየተመላለሰ አሳልፏል።
በተለይ ወደ ዝዋይ እስር ቤት ከተላለፈ በሁዋላ ፣ ሃጎስ የተባለው የእስር ቤቱ ሃላፊ ” አንተ የነፍጠኛ ልጅ እንበቀለሃለን፣ በእኔ እጅ ነው የምትሞተው” እያሉ ይደበድቡትና ይዝቱበት ነበር። ባለፈው ቅዳሜ እናቱ ሊጠይቁት ሲሄዱ፣ ታሞ
ሚኒሊክ መወሰዱን ይነግሩዋቸዋል። ወደ ሚኒሊክ ሲሄዱ፣ በአንድ አምቡላንስ ውስጥ ጎንና ጎኑ በኤሌክትሪክ ተጠብሶ፣ ኩላሊቱ አካባቢ ተረጋግጦና በልዞ፣ አናቱ አካባቢ ያረፈበት ድብደባ ፊቱን ለማየት በማይቻል ሁኔታ በደም እንዲሸፈን
አድርጎታል።
የደረሰበትን ጉዳት ለመግለጽ ይዘገንናል የሚሉት ቤተሰቦቹ፣ ፖሊሶች አንዴ ታሟል፣ ሌላ ጊዜ ጉዳዩ በአቃቢህግ ተይዟል በማለት ለመደናገር እየሞከሩ ነው። የ22 አካባቢ ወጣቶች የሟቹ ቲሸርት ያለበትን ፎቶ እያሳተሙ ነው። ፖሊሶችና ደህንነቶች በድንካኑ አካባቢ እየተዘዋወሩ በመቆጣጠር ላይ ናቸው። የሟች የቤተሰብ አባላት የኢትዮጵያ ህዝብ ይፍረደን እያሉ ነው ። ከቤተሰብ አባላት ጋር አጭር ቆይታ አድርገናል

No comments:

Post a Comment

wanted officials