የመንግስት ኮሚኒኬሽን ምክር ቤት የኢሳትን የመረጃ ጥንካሬ ገመገመ
ሚያዝያ ፳፫ (ሃያ ሦስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :- በአቶ ሬድዋን ሁሴን የሚመራው የኮምኒኬሽን ምክር ቤት የኢሳት አባሎችን እና ቁልፍ የግንቦት ሰባት አመራሮችን የግል ላፕቶፓቸውን እና ለመረጃ መሰብሰብ የሚጠቀሙባቸውን ስልኮች ለማግኘት የሚያስችል እቅድ ማውጣቱ ታውቋል።
በግምገማው ወቅት ኢሳት ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጠነከረ መሆኑ ተገልጿል። ኢሳት በመንግስት ላይ እየሰነዘረ ያለው ጥቃት ጉልህ ለውጥ የማምጣት አቅም ፈጥሯል ሲል በውይይቱን ላይ ተነስቷል፡ የኢሳት የማህበራዊ ሚዲያ እና የቴሌቪዥን ስርጭት ሀገሪቱን በማወኩ ሂደት በፕሮፓጋንዳ ስራው መንግስትን ቀድሟል የሚለው ግምገማ፣ ይህም በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት በማግኝት ተፅኖ እየፈጠረ ነው ብሎአል።
የኢሳትን እና የግንቦት ሰባት አመራሮች የአባላቱን የግል ስልክ ፤ ላፕቶፕ ፤ የሚስጢር ኢሜል አድራሻ ማግኝትን ተቀዳሚ አላማው ያደረገው ወይይት ፤ በኢንባሲ በኩል ያሉ ወኪሎች ቀጣይ ስራቸው የኢሳትን ጋዜጠኞች ላፕቶፖችና ስልኮች ማግኘት እንዲሆን ማሳሰቢያ ተሰጥቷል።
ውይይቱን ለመተግበር የተዘረጋውን እቅድ ኢሳት በአጽኖት የሚከታተለው ይሆናል። መረጃዎችን ለኢሳት የሚልኩ ኢትዮጵያውያን ደህንነታቸውን በተመለከተ በኢሳት በኩል አስፈላጊው ጥንቃቄ የሚደረግ በመሆኑ ምንም ስጋት እንዳይገባቸው ድርጅቱ አስታውቋል። መንግስት ኢሳትን ለማፈን ተደጋጋሚ ሙከራዎችን ቢያደርግም እስካሁን ሊያስቆመው አልቻለም። ኢሳት ካለፉት ሶስት ሳምንታት ጀምሮ በተጠናከ ሁኔታና አብዛኛው ህዝብ ሊያየው በሚችለው በናይል ሳት ስርጭቱን በማስተላለፍ ላይ ነው።
No comments:
Post a Comment