Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, May 27, 2015

መድረክ የእሁዱን ምርጫ ውጤት አልቀበልም አለ ‪






መድረክ የእሁዱን ምርጫ ውጤት አልቀበልም አለ ‪

የኢትዮጵያ ፌዴራሊያዊ አንድነት መድረክ ባለፈው እሁድ የተካሄደውን አምስተኛው አገር አቀፍ አጠቃላይ ምርጫ ውጤትን እንደማይቀበል ገለፀ።

የመደረክ ከፍተኛ አመራሮች ዛሬ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ፥ በምርጫው ሂደት ላይ ችግሮች የነበሩ በመሆኑ ውጤቱን አንቀበልም ብለዋል።


መድረክ በምርጫው አጋጥመውኛል ያላቸውን ችግሮች ለኢትዮጵያ ብሄራዊ ምርጫ ቦርድ ማሳወቁን ነው ያመለከቱት።

ማምሻውን አዲስ አበባ አፍንጮ በር አከባቢ በሚገኘው የመድረክ ዋና ፅህፈት ቤት መግለጫ የሰጡት የመድረክ የወቅቱ ሊቀመንበር ፕሮፌሰር በየነ ጴጥሮስ እና ሌሎች የመድረኩ አመራሮች ናቸው።

ወያኔ/ኢሕአዴግ በምርጫ ተሸንፎ እያለ አጭበርብሮ በሥልጣን ለመቀጠል በሚያደርገዉ መፍጨርጨር ለሚከተለዉ ማንኛዉም ሕዝባዊ ተቃዉሞ ተጠያቂ ነዉ።በሚል የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ አለም አቀፍ ድጋፍ ሰጪ ቡድንም  መግለጫ  ማውጣቱ የሚታወስ ነው ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials