Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, May 29, 2015

ሰማያዊ ፓርቲ የ2007 ዓ.ም ሀገራዊ ምርጫ ሂደቱንም ሆነ ውጤቱን እንደማይቀበለው አሳወቀ፡


• ‹‹የአፍሪካ ህብረት ራሱንም ሌላም ማዳን የማይችል
የእንጨት ድስት ነው›› አቶ ስለሽ
፡ ፓርቲው ዛሬ ግንቦት 21/2007 ዓ.ም በጽ/ቤቱ ‹‹ነጻነት በሌለባት ኢትዮጵያ ሕዝባዊ አስተዳደር መትከል ዘበት ነው!›› በሚል ለሀገር
ውስጥና ለውጭ ሀገር ጋዜጠኞች በሰጠው መግለጫ ምርጫው ‹‹ከዚህ ቀደም ከተካሔዱት ምርጫዎች ጋር እንኳ ሊወዳደር የማይችል እጅግ ኢ-ፍትኃዊ፣ ወገንተኛና ተዓማኒነት የሌለው በመሆኑ ሰማያዊ ፓርቲ ሂደቱንም ሆነ ውጤቱን አይቀበለውም፡፡›› ብሏል፡፡
በ2007 ዓ.ም ጠቅላላ ምርጫ ለመሳተፍ ሲወስን ገለልተኛና ብቃት ያላቸው ተቋማት እንደሌሉና ገዥው ፓርቲም እውነተኛ ምርጫ እንደማይፈቅድ እያወቀ መሆኑን የገለፀው ሰማያዊ በሂደቱ የተሳተፈው የስርዓቱን ችግሮች ለማጋለጥ እንደሆነ አስታውቋል፡፡ የፓርቲው ሊቀመንበር ኢ/ር ይልቃል ጌትነት ‹‹በሂደቱ ውስጥ በመቆየታችን እጩዎቻችን በህገ ወጥ መንገድ ሲታገዱ፣ ታዛቢዎች ሲከለከሉና ሲታሰሩ አሳይተናል፡፡
በሂደቱ በመቆየታችን የኢህአዴግን አውሬነት አሳይተናል፡፡
ከመጀመሪያው ጀምሮም ሆነ በምርጫው ወቅት የነበረውን
ማጭበርበር ለኢትዮጵያ ህዝብና ለዓለም አጋልጠንበታል፡፡››
ብለዋል፡፡ የፓርቲው ም/ሊቀመንበር እና የምርጫ ጉዳይ
ኃላፊው አቶ ስለሽ ፈይሳ በበኩላቸው ምርጫው መትረየስ
ተጠምዶ፣ ብረት ለበስ በየ መንገዱ ቆሞ፣ የአጋዚ ጦር አባላት
ከተማ ውስጥ ተሰማርተው ከመካሄዱም ባሻገር ከፍተኛ የድምጽ
ማጭበርበር የነበረበት ነው ብለዋል፡፡ የምርጫው ብቸኛ
የውጭ ታዛቢ የሆነውን የአፍሪካ ህብረት ታዛቢ ቡድንም
ራሱንም ሌላም ማዳን የማይችል ‹‹የእንጨት ድምጽ ነው!››
ሲሉ ተችተዋል፡፡
ምርጫው በህገ ወጥ አሰራሮች የታጀበ፣ በማንኛውም መመዘኛ
ፍትሃዊ፣ ነፃና ተአማኒ ሊሆን እንደማይችል ሒደቱ በግልፅ
አመላካች ነበር ያለው ሰማያዊ ፓርቲ ‹‹በውጤቱም በሐገራችን
የዲሞክራሲና የመድብለ ፓርቲ ስርዓት መኖርን ወደ መቃብር
የከተተና ኢትዮጵያ የአንድ ፓርቲ ስርዓት ሐገር መሆኗን
ያረጋገጠ ነው፡፡..ለኢትዮጵያ ዴሞክራሲ የጨለማ ዘመን
መምጣቱን ከማሳየቱ ባሻገር ኢህአዲግ በፍርሃት ተውጦ
ሁሉንም ለመቆጣጠር ባደረገው ሩጫ ለመግለፅ እስኪያፍር
ድረስ የሚያሸማቅቅ ውጤት እንዲከናነብ ሆኗል፡፡›› ብሏል፡፡
በኃይል በተቀማ ድምፅ የሚመሰረት መንግስትም በሕዝብ
ተቀባይነት እንደሌለውም ገልጾአል፡፡
ሰማያዊ ፓርቲ በአፈና እና ጭቆና ውስጥ ሆነው ድምጽ ለሰጡት
መራጮች ምስጋናውን አቅርቧል፡፡ በምርጫው ሂደት የተንገላቱ፣
የታሰሩትን፣ የተደበደቡና የተሰደዱትን አባላቱንም ፓርቲያቸው
በኢትዮጵያ ሕዝብ ተስፋ የተጣለበት እንዲሆን ለደረሰባቸው
መከራና በደል ክብር ይገባቸዋል ብሏል፡፡ የዜጎች ነፃነት
ሳይከበር ነጻና ፍትኃዊ ምርጫ ሊደረግ አይችልም ያለው
መግለጫው ሰብአዊና ዲሞክራሲያዊ መብቶቻችን እስከሚከበሩ
ድረስ ሰማያዊ ፓርቲ በሚያካሂደው የነጻነት ትግል
ኢትዮጵያውያን ከጎኑ እንዲቆሙ ጥሪ አድርጓል፡፡ ሰማያዊ ፓርቲ
ሰላማዊ ትግሉን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ገልጾአል፡፡


Like · Comm

No comments:

Post a Comment

wanted officials