Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, May 11, 2015

በንጹሃን የሰማያዊ አባላት ላይ ለምስክርነት ያቀረባቸው ሰዎች የወያኔ ወጣቶች ማህበር አመራሮች መሆናቸው




የአዲስ አበባ የኢሕአዴግ ወጣቶች ማህበር አመራሮች በሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ ለሃስት ምስክርነት ቀረቡ


 በወያኔ ሚዲያዎች አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዋች የተባሉ የወያኔ አለቅላቂዎች በሃስት ምስክርነት ተዘጋጅተዋል::ሚያዝያ 14/2007 ዓ.ም ወያኔ ራሱ በጠራው ሰልፍ ላይ ‹‹ሁከትና ብጥብጥ በማስነሳትና በማስተባበር›› በሚል የሃስት ወንጀል ከየቤታቸው አፍሶ አስሯቸው የቆዩ የሰማያዊ ፓርቲ አባላት ላይ ክስ የመሰረተ ሲሆን ለምስክርነት ያቀረባቸው ሰዎች የወያኔ ወጣቶች ማህበር አመራሮች መሆናቸው ታውቋል::


ከነዚህም ምስክሮች መካከል አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪ እየተባሉ በወያኔ ሚዲያ ከሚቀርቡት አንዱ ወጣት ነፃነት ጣሰው ይባላል በፊት የጉለሌ ክ/ከተማ ነዋሪ ነው በጉለሌ በሚኖርበት ሰአት የኢህአዲግ ካድሬ በመሆን በ97 ብዙ ወጣቶች አስጨፍጭፎል ይህንን አልበቃ ያለው ወጣቱ ወደ ቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 3 የወጣቶች ማህበር አመራር ሆኖ በመመረጥ ውክልና በመያዝ ኵየቦሌ ክ/ ከተማ ወጣቶች ማህበር ምክትል ኘሬዘዳንት ሆነ በመቀጠል ደግሞ በክፍለ ከተማ ውስጥ እና በከተማ ደረጃ ያለውን እንቅስቃሴ በመጨመር በከተማ ስራ አስፈፃሜ ደረጃ ደርሶ የወንድሙ ዮሀንስ ጣሰውን ቦታ በመመኘት ለማግኘት ከፍተኛ ጥረት ያድርግ እንደነበር ሁሉም የሚያቀው የአደባባይ ሚስጥር ነው ይህን ሁሉ ሲፈፅም የህውሀት ኢህአዲግ አባል ወይም ብአዴንን በመወከል ነበር ይህን ሁሉ ታምር ያደረገው ። ዛሬ በአሁኑ ወቅት የአዲስ አበባ ወጣቶች ምክትል ፕሬዘዳንት በመሆን እያገለገለ ይገኛል ዛሬ ግን የአንዳንድ አዲስ አበባ ነዋሪዋችን ወክሎ ንግግር ebc ሲያረግ እውነት ህውሀት ኢህአዲግ በጣም አሰራሩ የጠፍበት ድርጅት መሆኑን ተረዳን ይህ ግለሰብ በተመሳሳይ በጣም ብዙ ግዜ አንዳንድ የአዲስ አበባ ነዋሪዋችን ወክሎ ሲያወራ ebC store ብንገባ ብዙ ማውጣት ይቻላል::

እነዚህ ሆዳም ካድሬዎች በንጹሃን የሰማያዊ አባላት ላይ ለመመስከር በሃሰት ምስክርነት በአቃቢ ሕግ ተዘጋጅተው ቢቀርቡን ከታሪክ ተጠያቂነት ነገን አያመልጡም በሌሎች ምስክሮች ላይ ያላችሁን ጥቆማ ብትሰጡን ለማቅረብ ዝግጁ ነን::መረጃውን የላካችሁልኝን አመሰግናለሁ::

No comments:

Post a Comment

wanted officials