Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, May 4, 2015

በኦሮሚያ ሰበታ አንድ የመድረክ አባል ተገደለ






በኦሮሚያ ክልል ሰበታ በተባለው ቦታ አንድ የመድረክ አባል ግለሰብ በጉጅሌው የኢህአዴግ ፀጥታ አካላት እንደተገደለ ተገለጸ።

የደህሚት ድምጽ ያገኘው መረጃ እንዳመለከተው በኦሮሚያ ክልል የሚገኙ የተቃዋሚ ድርጅት አባላት በስርአቱ የታጠቁ ሃይሎች እየደረሰባቸው ያለው የማስፈራራት ዛቻ አልበቃ ብሏቸው ከተማ ፋፎ የተባለውን የመድረክ አባል ሚያዚያ 12/ 2007 ዓ/ም 2:00 ሰአት አመሻሽ ወደ ስራው እየሄደ በነበረበት ጊዜ በኢህአዴግ የፀጥታ አካላት እንደተገደለ ለማወቅ ተችሏል።

የግለሰቡ መገደል ሁኔታ ገዢው የኢህአዴግ ስርአት እየተከተለው ያለውን የግብር አከፋፈል ሂደት በፅናት እየተቃወመው የነበረ በመሆኑ ብቻ እንደሆነና በጉጅሌው አይን እይታ በመውደቁ ሊገደል እንደቻለ የገለፀው ምረጃው እንደዚ አይነት በሰላማዊያን ድርጅት አባላቶች ላይ እየተወሰደ ያለው አሰቃቂ የግድያ ተግባርም ስርአቱ እየቀጠለበት መሆኑን መረጃው ጨምሮ አስረድቷል።

No comments:

Post a Comment

wanted officials