Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, May 31, 2015

የድርጅት ጋጋት ይብቃ፣ ተባበሩ ወይም አርፋችሁ ተቀመጡ - ግርማ ካሳ

የድርጅት ጋጋት ይብቃ፣ ተባበሩ ወይም አርፋችሁ ተቀመጡ - ግርማ ካሳ
ትላንትና አዲስ ድምጽ ራዲዮ ላይ ቀርቤ ነበር። አዲስ ድምጽ ራዲዮ በዲሲና አካባቢዋ እንዲሁም በኢንተርኔት በአለም ዙሪያ ሁሉ ታዋቂ የሆነች ራዲዮ ጣቢያ ናት። በራዲዮም ከሰጠኋቸው አስተያየት መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል፡
1) የሰላማዊ ትግል አይሰራም የሚባለው አባባል የሚጠቅመው ወያኔን ብቻ ነው። ጥያቄው የሰላማዊ ትግል ወይስ የትጥቅ ትግል ይሻላል የሚል መሆን የለበትም።ጥያቄው የትጥቅ ትግል የሚሉት በትጥቅ ትግላቸው፣ የሰላማዊ ትግል የሚሉትብደግሞ በሰላማዊ ትግላቸው ውጤት በሚያመጣ መልኩ እየተንቀሳቀሱ ነው ወይ ? የሚለው ነው መሆን ያለበት።
አንዳንድ ድርጅቶች እነርሱ ድጋፍ እንዲያገኙ ከመፈለግ የተነሳ፣ የሰላም ትግል አይሰራም የሚል አፍራሽና ጎጂ ፕሮፓጋንዳዎችን ሲረጩ እናያለን። የሰላማዊ ታጋዮች የትጥቅ ትግሉን በተመለከተ እንጻፍና እንናገር ቢሉ ብዙ ሊጻፍና ሊነገር እንደሚችል ግን መረሳት የለበትም። ይህ አይነቱ ክርክር ደግሞ ምንም ጥቅም አያመጣም። የትጥቅ ትግል የሚያደረጉት ትግላቸውን ይቀጥሉ። የሰላማዊ ትግል መደረጉ በምንም መስፈርት የነርሱን ትግል የሚጎዳበትም ሆነ የሚይዘበት ሁኔታ የለም። የኢትዮጵያ ሕዝብ ከ90 ሚሊዮን በላይ ነው። ያ ሁሉ ህዝብ ኤርትራ ገብቶ ነፍጥ አንስቶ ሊዋጋ አይችልም። ስለዚህ ያንን ህዝብ የሚያሰባሰብና የሚያንቀሳቅስ ስትራቴጂክ በሆነ መልኩ የሰላማዊ ትግል መጠናከር አለበት። የሰላማዊ ትግል ሰራዊት ራሱ ሕዝቡ ነውና።
2) ትግሉ የጥቂቶች አይደለም። ዶር መራራ፣ እነ ዮናታን ተስፋዬ፣እነ አቶ በላይ ፍቃደ፣ እነ ዶር ብርሃኑ ነጋ፣ እነ አቶ ታማኝ፣ እነ አቶ አበበ በለዉና፣ አቶ አበበ ገላው ፣ እነ አቶ ኦባንግ...በተናጥል ወይንም፣ ከጥቂት ጓደኞቻቸው ጋር ሆነው በሚያደርጉት ሥራ ለዉጥ ሊመጣ አይችልም። በጥቂት አክቲቪስቶች ድካም ብቻ ለዉጥ አይኖርም። የግዴታ የእያንዳንዱ ኢትዮጵያዊ ተሳትፎ ያስፈልጋል። ኢትዮጵያዊያኖችን በሙሉ ማሰባሰብና ማነቃነቅ ያስፈልጋል። ያንን ለማድረግ ደግሞ ኢትዮጵያዉያን እንዳይሰባሰቡ፣ ሁሉን ትተው ቤታቸው እንዲቀመጡ ያደረጋቸውን ነገር ማስተካከል ቀዳሚ ሥራ ነው ሊሆን የሚገባው።
ብዙ ኢትዮጵያውይን ትግሉን እንዳይቀላቀሉ፣ ትግሉን በሚመሩ ተቃዋሚዎች ላይ አመኔታ የላቸውም። አንድ ሺህ ተቃዋሚ በየጊዜው እየተፈራረቀ ሰው ምን ብሎ ነው አክቲቭ የሚሆነው? በዉጭ አገር ፣ ዛሬ ግንቦት ሰባት ገንዘብ አምጡ ይላል። ነገ ሸንጎ ገንዘብ አምጡ ይላል። ከነገ ወዲያን ሶሊዳሪቲ ገንዘብ አምጡ ይላል። ሰዉን እኮ በተለያየ አቅጣጫ አሰለቸነው። ! ሰው ደከመው።
በአገር ቤት ደግሞ መኢአድ በዚህ ይሮጣል። እዚያ ጋር ደግሞ ሰማያዊ። ወዲያ ደግሞ መድረክ ...ተቃዋሚውች ተከፋፍለው በተናጥል እየሰሩ፣ ሪሶርስና ኤነርጂ እያባካኑ፣ ከአገርና ከሕዝብ ጥቅም ይልቅ ድርጅትን እና ስልጣንን እያስቀደሙ፣ እንዴት ህዝቡ አመኔታ ኖሮ ከነርሱ ኋላ ሊሰለፍ ይችላል ?
ስለዚህ በዋናነት አገር ዉስጥም ሆነ ከአገር ዉጭ ያሉ ድርጅቶች ልዩነቶቻቸውን እንደያዙ፣ ቀዳሚ በሆነው አገርን ነጻ በማወጣትና የዴሞርካሲ ስርዓት በመገንባቱ ዙሪያ በጋራ መስራት አለባቸው።
ሸንጎ፣ ሽግግር ምክር ቤቱ፣ ግንቦት ሰባት፣ ሶሊዳሪቲ ንቅናቄ፣ ኦዴፍ ...አንድ በዳያስፖራ ትግሉን የሚመራ አማርጭ ኃይል ማቋቋም አለባቸው። በአገር ቤት ደግሞ መድረክ፣ ሰማያዊ፣ መኢአድ፣ አንድነት ....ሁሉም ልዩነቶቻቸውን እንደያዙ፣ ህዝባዊ ሞቢላይዜሽን በማድረግ ሕዝቡን ለማንቀሳቀስ፣ የጋራ ግብረ ኃይል አቋቁመው ሥራ መጀመር አለባቸው።
                         pic from Ethiopians Blog of timret

No comments:

Post a Comment

wanted officials