Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, May 31, 2015

ግለሰቡ በትግራይ ክልል 6 ሰዎችን የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ውስጥ ገደለ


tigrai
 በትግራይ ክልል ከሚሰራበት ባንክ መስሪያ ቤት የተባረረው ግለሰብ በፊት ይሰራበት ባንክ ገብቶ 6 የባንኩን ሠራተኞች መግደሉ ለዘ-ሐበሻ የደረሰው መረጃ አመለከተ:: በትናንትናው ዕለት ግንቦት 21 ቀን 2007 ዓ.ም በሰሜን ምዕራብ ትግራይ በምትገኘው ማይ ፀብሪ በተባለች ከተማ ይኸው ቀድሞ በዘበኝነት ባንኩን ያገለግል የነበረው ግለሰብ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ማይፀብሪ ቅርንጫፍ ስራ አስኪያጅና የወንድ ዘበኛ ጨምሮ 6 የባንኩ ሰራተኞችን ሲገድል አንዲት የባንኩ ሴት ዘበኛም ማቁሰሉን የደረሰን መረጃ አመልክቷል:: እንደ ዜናው ከሆነ ይኸው ማንነቱ ያልታወቀ ግለሰብ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክን ቅርንጫፍ ለተወሰኑ ሰዓታት ተቆጣጥሮት ቆይቶ በመጨረሻም በፖሊስ ቁጥጥር ስር መዋሉን ለዘ-ሐበሻ የመጣው መረጃ ጠቆሟል:: ሰዎቹን የገደለው ይኸው የቀድሞ የባንክ ሠራተኛ ለምን ከሥራው እንደተባረረ የደረሰን መረጃ የለም:: 

No comments:

Post a Comment

wanted officials