Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, August 31, 2015

የሱዳን ወታደሮች 8 ኢትዮጵያውያንን በአሰቃቂ ሁኔታ ገደሉ



የሱዳን ወታደሮች ኢትዮጵያውያንን በአሰቃቂ ሁኔታ ገደሉ
ነኅሴ ፳፭ (ሀያ አምስት) ቀን ፳፻፯ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የሱዳን ባለሀብቶች መተማ ዮሃንስ ከተማ ውስጥ "ትራክተር መንዳት የሚችል 11 ሰዎችን እንፈልጋለን" የሚል ማስታወቂያ መለጠፋቸውን ተከትሎ፣ ውድድሩን ካለፉት መካካል 8ቱ በሱዳን ታጣቂዎች ታርደው ተገድለዋል። ባለሀብቶቹ በርካታ አመልካቾችን ቢያገኙም፣ አስራ አንዱን ብቻ ይዘው ወደ ሱዳን መሄዳቸውን ፣ ይሁን እንጅ ሱዳን ውስጥ ሲገቡ፣ ወታደሮቹ መንገድ ላይ ጠብቀው ከመኪና ላይ በመውጣት ሰዎችን ማረድ ሲጀምሩ፣ የውትድርና ትምህርት የነበራቸው 3 ወጣቶች ከመኪና ላይ በመውረድ ማምለጣቸውን፣ ቀሪዎቹ በአሰቃቂ ሁኔታ መገደላቸውን የአካባቢው ነዋሪዎች ለኢሳት ገልጸዋል። የተወሰኑ አስከሬዎች መቃጠላቸውን፣ የተወሰኑት ደግሞ ወደ ኢትዮጵያ መመለሱን የአካባቢው ነዋሪዎች ተናግረዋል። ኢሳት የወረዳውን አስተዳዳሪ ለማነጋገር ተደጋጋሚ ሙከራ ቢያደርግም ሊሳካለት አልቻለም። ሱዳን ከኢትዮጵያ ጋር ያለው ድንበር እንዲካለል ሰሞኑን በድጋሜ ጠይቃለች። ከዚህ ቀደም እጅግ ሰፊ የሆነ መሬት ከኢትዮጵያ የወሰደችው ሱዳን፣ በአንዳንድ አካባቢዎች ያሉ አወዛጋቢ ቦታዎች እንዲካለሉላት ትፈልጋለች። በኢትዮጵያውያን ላይ የተወሰደውን እርምጃ በተመለከተ የኢህአዴግ መንግስት የውጭ ጉዳይ መስሪያ ቤት እስካሁን ምንም አላለም።

አሰቃቂው ግድያ
----
1ታደለ አበጀ
2 ቴዴ ሸመዴ
3 የሁንሰ አሰናቀው
4 ታከለ አህመድ
5 እሸቱ ዳውድ
6 ባህሩ ቃኝው
7 ሀሰን
8 ታዮ ሙላለም የተባሉ ወጣቶች አካባቢው ይገባናል በሚሉ የሱዳን
ታጣቂዎች ስለ መገደላቸው መረጃዎች ይጠቁማሉ። በረከት በተባለው አካባቢ
አሰቃቂ ግድያ የተፈጸመባቸው ወጣቶች አስከሬን በምስሉ የሚታየው
ነው።የሱዳኑ ትሪቡን ጋዜጣ ባሳለፍነው ሳምንት ሱዳን የድንበር ማካለሉ
ኦፊሻሊ እንዲከናወን መጠየቁ አይዘነጋም።
.

Netsanet Beqalu Mannet's photo.

Netsanet Beqalu Mannet's photo.

No comments:

Post a Comment

wanted officials