የአባቶች ተጋድሎ
እነዚህ ሁለት ፈርጥ የሐይማኖት አባቶች የዉድ ሐገራችን ኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋህዶና የሙስሊም ሐይማኖት ሊቆች ናቸዉ ሐገራችን በወያኔ እጅ ከወደቀችበት ወቅት አንስቶ ለሐይማኖት መከበርና ለዲሞክራሲ መብት ሲታገሉ በብርቱ ይታወቃሉ የተከበሩ የ 80 አመት አዛዉንት ሼህ ወርቁ ኑሩ እና ብጹእ አቡነ መርቆሪዎስ ይባላሉ ሼህ ወርቁ ኑር በደቡብ አፍሪካ ነዋሪ ሲሆኑ ብጹእ አቡኑ መርቆሪዎስ ደግም በአሜሪካን ይገኛሉ ሁለቱን የሚያመሳስላቸዉ ታላቅ ነገር ቢኖር ሐገር፣ ህዝብ፣ ኢትዮጵያዊነት ነዉ።
ላለፉት 20 አመታት ሁለቱም በሚኖሩበት ሐገር ከፍተኛ ትግል በማድረግ ጉልበታቸዉን ገንዘባቸዉን ጊዜያቸዉን በሰላማዊ የትግል ዘርፍ ወያኔን በመቃወም አዉለዋል። አሁን ግን ነገሩ ተቀየረ! ሰላማዊ ትግሉን አሽቀንጥሮ የደፋዉ ህዝባዊ ወያኔ ሐርነት ትግራይ በአንባገነንነት አሻፈርኝ አለ! እነሆ እነዚህ ምርጥ የክርስትናና የእስልምና እምነት አባቶች ወደ ትግል ሜዳ ወደ ኤርትራ በረሐ በመሄድ እራሳቸዉን መሰዋት ለማድረግ ተዘጋጁ! በርግጥ እጅግ ልብ የሚነካ ነገር ነዉ። እነዚህ አባቶችን ወደ ትግሉ ከመሄድ የሚያግዳቸዉ ነገር የለም። በመሆኑም ግን እነዚህ አባቶች ይህንን የመሄድ ፍላጎታቸዉን ካስታወቁበት ወቅትና ሰአት አንስቶ ብዙሐን ኢትዮጵያዊያን ልባቸዉ ተነክቷል!!! ወደ ትግሉም ከነዚህ አባቶች ቀድመዉ ለመድረስ ጉዞዋቸዉን ጀምረዋል!!! አዎ እነዚህን አባቶች ለታሪክ በማስቀመጥ የህይወት መስዋትነት ሊከፍሉ የተዘጋጁ ወገኖች በፍጹም አትሄዱብንም!!! እኛ እያለን እናንተ ወደሞት አትሄዱም!!! እያሉ ሙግት ገጥመዋል አባት እና ልጅ እራሱን ለትዉልድ መሰዋት አድርጎ ሊከፍል የተዘጋጀበት ወሳኝ ወቅት ላይ ደርሰናል አርበኞች ግንቦት 7ትን ለመቀላቀል ጉዞ የጀመሩና እየተቀላቀሉ የሚገኙ ወገኖች ቁጥር እጅግ በአስገራሚ ሁኔታ በየእለቱ እየጨመረ ነዉ!! ጊዜዉ በሙስሊም ወንድሞቻችን ላይ የደረሰዉን ግፍ በቸልታ የምንቀበልበት ወቅት አይደለም!! ከእንግዲህ እናት ሐገር ወይም ሞት ሐይማኖታችንን ሐገራችንን ሳናስመልስ አንመለስም!!!!!! የሚሉ ሙስሊም ወንድሞች ጓዛቸዉን ጠቅለዉ ወደ ሜዳዉ እየገቡ ነዉ። አርበኞች ግንቦት 7 በበኩሉ ለአንዴና ለመጨረሻ ጊዜ የሚያደርገዉን ወያኔን የማስወገድ ስራ አጠናቋል! ወያኔም በተለያዩ አቅጣጫዎች አለሁ እያለች ብትመጣም የገዛ ሰራዊቷ እየከዳት አየር ሐይሏ እየሟሸሸ ማጠፊያዉ እያጥራት ይገኛል ጀግኖቹ የርበኞች ግምቦት7 ልጆች በቀላሉ የሚመከቱና የሚጤቁ አልሆኑም ድሉ እንደቀጠለ ነዉ።
ከባቶቻችን ቀድመን ለመሰዋትነት ቆመናል!!!
ድል ለኢትዮጵያ ህዝብ
No comments:
Post a Comment