Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, August 12, 2015

ሰበር ዜና – ሪያድ ከተማ በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ፀረ ወያኔ /ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ተቃውሞ ስትናጥ አደረች


ሰበር ዜና – ሪያድ ከተማ በሙስሊም ኢትዮጵያውያን ፀረ ወያኔ /ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ተቃውሞ ስትናጥ አደረች



(ዘ-ሐበሻ) ሰሞኑን የህወሃት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ ፍ/ቤት በሙስሊሙ መፍትሄ አፈላላጊ ኮሚቴ አባላት ላይ የወሰደውን ኢፍተሃዊ ውስኔ በመቃወም ሪያድ ከተማ ውስጥ ትላንት አርብ ኦገስት 7 2015ምሸት ኢትዮጵያዊው ህዝበ ሙስሊም አንድነቱን ጠብቆ ተቃውሞውን አሰምቷል ። ቁጥሩ ከፍተኛ እንደሆነ ህዝብ የተገኘበት ይህ ታላቅ ተቃውሞ የአካባቢውን ድባብ ለውጦት እንደነበር ለማወቅ ተችሏል። የተከሰተው ነገር በራሳችን እንደደረሰ ተሰምቶን በሶስት ቀን ውስጥ በተጠራ የተቃውሞ ጥሪ ይህን ያህል ህዝብ አንድነቱን ጥብቆ ለተቃውሞ በነቂስ መውጣቱየትግሉ አንዱነት ጥንካሬ መገለጫ መሆኑን የገለጹት ሼክ ሲዒድ አህመድ ህዝበ ሙስሊሙ በመንግስት ከባድ ፈተና እንደ ተጋረጠበት አውስተው ይህ ፈተና አዲስ ሆኖብን ሳንደናገጥትግሉን በበሰለና በስለጠነ መንገድ በማጠናከር እስከ ድል መቀጠል እንደሚገባ በቁጣ የወጣውን ህዝብ ሙስሊም በማረጋጋት በአባታዊ ምክራቸውን ገስጸዋል ።

ሼክ ሰዒድ በማስከተል አቡበከር በአንድ ወቅት በመንግስት ፀጥታ ሃይሎች ወህኒቤት ግፍ እይተፈፀመበት « ፍ/ቤቱም የኛ ፤ ፖሊሱም የኛ ፤ አቅቤ ህጉም የኛ ፤ መርማሪውም የኛ ስለሆነየፈለከውን የመከላከያ ምስከር ብታመጣ ብትወጣ ብትወርድ ከፍርድ አታመልጥም እኛ ነን የምንፈርድብህ » ተብሎ በስረአቱ ካድሬዎች በምጸት ከፍርድ ቤቱ ውሳኔ በፊት ተነግሮትየነበረውን በተግባር ማየቱን ሼኩ ለተስብሳቢው በመጥቀስ በመሪዎቻችን ላይ የተፈፀመው ደባ ሊያስደንቀን እንደማይገባ ገልጸው የፍ/ቤቱን ኢፍታሀዊነት ለተሰብሳቢው በተጨባጭ አስረድተዋል። በውቅቱ በቁጣ ገንፍሎ የወጣውን ህዝብ ለማስተናገድ ተይዞ የነበረው ቦታ በመጨናንቁ የነበረውን የሪያድ የአየር ሙቀት በመቋቋም ከ ምሽቱ 1 ስዓት ጀምሮ እስከ ሊሊቱ9 ስዓት ድረስ በዘለቀው በዚህ ፀረ ጭቆና ህዝባዊ ተቃውሞ ላይ አንዳንድ የስብሰባው ተሳታፊዎች ህዝበ ሙስሊሙን በገዛ ሃገሩ መቆሚያ መቀመጫ ያሳጣውን የህወሃት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግስረዓት እንዲያጠፋላቸው እያለቀሱ ለፈጣሪያቸው ፀሎት « ዱአ » አድርሰዋል ። ሰሞኑን የህወሃት/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግ መንግስት ፍ/ቤት በህዝበ ሙስሊም ተወካዮች ላይ ያሳለፈው ውሳኔሰረዓቱ በመላ ኢትዮጵያዊ ሙስሊም ላይ እየፈጸመ ያለው ሃይማኖታዊ ጭቆና ግፍና በድል አንዱ አካል መሆኑን የገለጹት እንዚህ የስብሰባው ተሳታፊዎች ከእንግዲህ ትዕግስታቸውመሞጠጡን ጠቅሰው በዚህ አምባ ገነን ስረዓት ላይ የጀመሩትን ትግል እስከ መጨረሻ አጠናክረው ለመቀጠል በመወሰን የአቋም መግለጫ አውጥተዋል።

በሳውዲ አረቢያ ድምጻችን ይሰማ ደጋፊዎች እያካሄዱ ባለው ሃይማኖታዊ ፀረ ጭቆና ትግል የህወሃትን/ኢ.ህ.አ.ዴ.ግን ስረዓት የቦንድ ሽያጭና መስል የስረአቱን እንቅስቃሴበማሽመድመድ የታወቁ ግንባር ቀደምና ጠንካራ መሆናቸው ይነገራል።

ኢንጂነር መሃመድ አባስ ከሪያድ ሳውዲ አረቢያ

No comments:

Post a Comment

wanted officials