Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Saturday, August 8, 2015

የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር ኤፍሬም ማዴቦ እንደነ ዶር ብርሃኑ ነጋ አስመራ ወርደው የትጥቅ ትግሉን ተቀላቀሉ


የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር ኤፍሬም ማዴቦ እንደነ ዶር ብርሃኑ ነጋ አስመራ ወርደው የትጥቅ ትግሉን ተቀላቀሉ
ከአርበኞች ግንቦት 7 ከፍተኛ አመራሮች መካከል አንዱ የሆኑት አቶ ኤፍሬም ማዴቦ አስመራ ሄደው የትጥቅ ትግሉን መቀላቀላቸው ተሰማ::

የአርበኞች ግንቦት 7 መሪ ፕሮፌሰር ብርሃኑ ነጋ እንዲሁም አቶ ነአምን ዘለቀ አስመራ ወርደው ትግሉን ከተቀላቀሉ ሳምንታት የተቆጠረ ሲሆን አቶ ኤፍሬም ማዴቦም ከሐምሌ ወር 2007 ዓም   መጨረሻ ጀምሮ ኤርትራ በረሃ በመውረድ  ትግሉን  ተቀላቅለዋል::

የዛሬ 25 ዓመት ወደ ስደት ገብተው በሰሜን አሜሪካ የተለያዩ ከፍተኛ የትምህርት ተቋማት የተማሩት አቶ ኤፍሬም ከጆርጅ ሜሰን ዩኒቨርሲቲ በማዕረግ የተመረቁ ታዋቂ የፖለቲካ ሰው ናቸው::
ከ አሜሪካው በክኔል ዩኒቨርሲቲ ፕሮፌሰርነትን ያገኙት ታዋቂው ዶር ብርሃኑ ነጋ ፥የአርበኛ አባቱን ፈለግ በመከተል ትግሉን የተቀላቀለው ነዓምን ዘለቀ ና ሌሎችም ለትግል በረሃ ድረስ የገቡት ቀን ጎድሎባቸው ሰራ አጥተው ሳይሆን የተደላደለ የምዕራቡ አለም ቅንጦት   በቃኝ ብለው ይልቁንም ሁሉንም ላጣነው አርአያ ይሆናሉ።በመሆኑም እኛስ መቼ ይሆን ብለን ራሳችንን በመጠየቅ የትግሉን ጎራ በመቀላቀል ነጻነታችንን ማፋጠን አለብን። አሁኑኑ እንወሰን።

ስማቸው ያልተጠቀሱ የአርበኞች ግንቦት ሰባት  አባላት እና አመራሮች ትልቅ ገቢ የሚያስገኝላቸው ሥራቸውን እና ቤተሰቦቻቸውን በመተው   በየጊዜው ወደ አውደዉጊያው እያመሩ እንደሆነም ይታወቃል።



No comments:

Post a Comment

wanted officials