የዛሬው የፍርድ ቤት ውሎ
በሶልያና ሽመልስ የክስ መዝገብ ሶልያና ሽመልስ (በሌለችበት) በፍቃዱ ኃይሉ፣ ናትናኤል ፈለቀ፣ አጥናፍ ብርሃኔ እና አቤል ዋበላ በዛሬው ዕለት ‹ክሳቸውን መከላከል ያስፈልጋቸዋል ወይስ አያስፈልጋቸውም› በሚል የመጨረሻ ውሳኔውን ለመስማት በፍርድ ቤት ተገኝተው ነበር፡፡
በዕለቱ የተሰየመው ችሎት ‹‹ሰነዱ ሰፊ ነው ብዙ ማንበብ ይጠይቃል በዚህም ምክንያት ችሎቱ የክስ መዝገቡን አይቶ ባለመጨረሱ ለመጪው ሰኞ ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል» በማለት ቀጠሮው መተላለፉ በዳኛው የተነገረ ቢሆንም የፀረ ሽብር ክሶችን የሚያየው 19ኛ ወንጀል ችሎት ነሃሴ 15 ቀን ይዘጋል ተብሎ አስቀድሞ በዳኞች ተነግሮ የነበረ ቢሆንም ግልፅ ባልሆነ ሁኔታ ለነሃሴ 18 የብይን ተለዋጭ ቀጠሮ ተሰጥቷል።
481 ቀናትን በእስር ያሳለፉት ጦማሪያን የሚቀጥለው ቀጠሮአቸው 35ኛው ይሆናል ፡፡ በዕለቱ ከፍተኛ ቁጥር ያላቸው ታሳሪዎች በመገኘታቸው የጦማሪያኑ ቤተሰቦች እና ወዳጆች፣ ጋዜጠኞች እና የዲፕሎማቲክ ኮሚኒቲ አባላት ችሎቱን እንዳይታደሙ ተከልክለዋል፡፡

No comments:
Post a Comment