የኢትዮጵያ ባለስልጣናት በአሁኑ ወቅት የኢትዮጵያን ህዝብ ንብረትና አንጡራ ሀብት በመመዝበር በአለም አቀፍ ደረጃ አሉ በሚባሉ ታላላቅ የንግድ ተቋማትና ባንኮች ላይ ባለድርሻ እየሆኑ ይገኛሉ ለጊዜዉ ስማቸዉን መጥቀስ አስፈላጊ የልሆኑ ከፍተኛ ባለስልጣናት በደቡብ አፍሪካ ዚምባብዌ ኡጋንዳ ቦትሱዋና ዉስጥ ትላላቅ ህንጻዎችን፣ እና የእንግዳ መቀበያ ሆቴሎችን ( gust houses ) ፣ መሬቶችና ሌሎችታላላቅ የንግድ ተቋማት ላይ እግራቸዉን እየተከሉ ይገኛሉ።
ለምሳሌ ያህል ማክሮ ካምፓኒ በደቡብ አፍሪካ እና በዚምባዌ የሚንቀሳቀስ የንግድ ተቋም ሲሆን በደቡብ አፍሪካ ብቻ 19 የንግድ መጋዘኖች አሉት ማክሮ የቤት እቃዎችን የኮምፑዉተርና የመገናኛ እቃዎችን፣እንዲሁም የቢሮ እቃዎችን፣ የጽህፈ…ት መሳሪያዎችን፣ ማንኛዉም አላቂ እቃዎችና መለዋወጫዎችን ( Home Entertainment, Computers and Communication, Office furniture, Stationery supplies and equipment, Large and small appliances, Hardware and DIY, ) በማከፋፈል በደቡብ አፍሪካ በብርቱ የሚታወቅ ታላቅ ድርጅት ነዉ። ዋል ማርት እና ማስማርት መርገር (Walmart and Massmart Merger ) የተባሉ አለም አቀፍ ድርጅቶች የማክሮ 51 % ሼር ባለድርሻ እና ተካፋይ ሲሆኑ የማክሮ ካምፓኒ ከ100 በላይ ሼረ ባለድርሻዎች አሉት ትንሹ የሼር ባለድርሻ ግዢ አንድ ቢሊዮን ራንድ አካባቢ የሚጠጋ ሲሆን በዚህ ድርጅት ዉስጥ በረከት ስሞኦን የተባለዉ የኢትዮጵያ ባለስልጣን ከፍተኛ የሼር ባለድርሻ መሆናቸዉን የደረሰን መረጃ አረጋግጧል። ይህ ባለስልጣን ከ7 አመት በላይ የዚህ ድርጅት ባለድርሻ ሲሆን በየወቅቱ እና በየ ጊዜዉ የሼር ድርሻዉ እያደገና እየጨመረ መምጣቱን በጣም ዉስጥ አዋቂ የሆኑ ምንጮች ገልጸዋል።
በዚህ ባለንበት ወቅት ብቻ ከፍተኛ የሆኑ በተለይም በደቡብ አፍሪካ የሚገኙ የንግድ ቦታዎች ድርጅቶች እና የመሳሰሉት በወያኔ ባለስልጣናት ተወካዮች እየተሸመቱ የሐገራችንን ሐብትና ንብረት ማባከኑ መዝረፉ ማሸሹ ተጧጡፎ ቀጥሏል።
ይህ ሁኔታ እጅግ በመጨመሩና በመበራከቱ ምክንያት በነዚህ በደቡብ አፍሪካ እና አካባቢዉ በሚገኙ ሐገራት ዙሪያ የሚኖሩ ኢትዮጵያዊያንን እያስቆጣ እነደሚገኝ ለማወቅ ተችሏል።
የህዝብ ሐብትን የዘረፉ ሁሉ ለፍርድ ይቀርባሉ ! ! !
ጉድሽ ወያኔ
No comments:
Post a Comment