Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, August 13, 2015

የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች በእያንዳንዳቸው የ15 ሺህ ብር ዋስ ተጠየቀባቸው




በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
ከምርጫው ማግስት ከአማራ ክልል የተለያዩ አካባቢዎች በፖሊስ ተይዘው የታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች እያንዳንዳቸው 15 ሺህ ብር ዋስ ተጠየቀባቸው፡፡ አመራሮቹ ከተያዙበት ጊዜ ጀምሮ አራት ጊዜ ፍርድ ቤት የቀረቡ ሲሆን ፖሊስ በሽብርተኝነት ወንጀል እንደጠረጠራቸው ሲገልጽ ቆይቷል፡፡ ፖሊስ ‹‹ለግንቦት 7 አባላትን እየመለመሉ ይልካሉ፡፡ ኤርትራ ድረስ ሄደው ስልጠና ወስደዋል፡፡›› የሚል ክስ አቅርቦባቸው የነበር ቢሆንም ለክሱ ምንም አይነት ማስረጃ ሳያቀርብ ቀርቷል፡፡ አመራሮቹ በበኩላቸው የታሰሩት በሰላማዊ ትግል ጠንካራ እንቅስቃሴ የሚያደርጉ በመሆናቸው፣ በተለይም በምርጫው ወቅት ፓርቲያቸውን በማስተዋወቅና ህዝብን በማደራጀት ጠንካራ ስራ በመስራታቸው ገዥው ፓርቲ የወሰደባቸው በቀል መሆኑን ሲገልጹ ቆይተዋል፡፡ ከመታሰራቸው በፊት የገዥው ፓርቲ ካድሬዎች ከፖለቲካው እንዲርቁ ሲያስጠነቅቁዋቸው እንደቆዩም አስታውቀዋል፡፡
ፖሊስ ላቀረበው ክስ ማስረጃ ማቅረብ ባለመቻሉ የአማራ ክልል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ሰበር ችሎት ዛሬ ነሃሴ 6/2007 ዓ.ም ከምርጫው ማግስት እየታደኑ ከታሰሩት የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮች መካከል 8ቱ እያንዳንዳቸው የ15 ሺህ ብር ዋስ አቅርበው እንዲፈቱ ወስኗል፡፡ ከምርጫው በኋላ ታስረው በዛሬው ዕለት እያንዳንዳቸው 15 ሺህ ብር ዋስ ከፍለው እንዲወጡ የተጠየቀባቸው፡-
1. ልዑልሰገድ እምባቆም
2. ፋንታሁን ብዙአየሁ
3. መንግስቴ ታዴ
4. አበረ ሙሉ
5. አዳነ አለሙ
6. ሞላ የኑስ
7. ስማቸው ምንይችል
8. አበባው አያሌው ናቸው፡፡
ዛሬ ፍርድ ቤቱ በ15 ሺህ ብር ከፍለው ይውጡ ካላቸው በተጨማሪ በአማራና በደቡብ ክልል በርካታ የሰማያዊ ፓርቲ አመራሮችና አባላት ታስረው እንደሚገኙ ለማወቅ ተችሏል፡፡ በተለይም ከተለያዩ የአማራ ክልል አካባቢዎች ታድነው ከተያዙ በኋላ ባህርዳር ከተማ ውስጥ ታስረው የሚገኙት የፓርቲው አመራሮችና አባላት ከፍተኛ ድብደባ እየተፈፀመባቸው እንደሆነ ለማወቅ ተችሏል፡፡

- See more at: http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45830#sthash.wfgjHgh6.dpuf

No comments:

Post a Comment

wanted officials