በቴክሳስ ዳላስ ከተማ ዛሬ ለአርበኞች ግንቦት 7 ንቅናቄ በተካሄደው ህዝባዊ ስብሰባ ላይ ከ52,000 የአሜሪካን ዶላር መሰብሰቡን ዘገቢያችን ከስፍራው ገለጸ።
ዛሬ ቅዳሜ በቴክሳስ በተካሄደው ሀገርን የማዳን ህዝባዊ የአርበኞች ግንቦት 7 ጥሪ ላይ በርካታ በቴክሳስ የሚገኙ ኢትዮጵያኖች መገኘታቸው ታውቆል። አክቲቪስትና ጋዜጠኛ አበበ ገላው አሁን የተጀመረው የነጻነት ትግል ተጠናክሮ ማህበረሰቡ የሚገባውን ማድረግ ይገባዋል ብለዋል። የቀድሞው ኮሚኒኬሽን ሚንስተር ኤርምያስ ለገሰ በማያያዝ ዛሬ የህወሃት ሰራዊት ይህን ሃይል የሚቆቆምበት ሞራል ያለ አይመስለኝም ምክንያቱም በሰራዊቱ የተፈጠረው አለመግባባትና የማንነት ጥያቄ የጭዋታውን ሜዳ እንደሚቀይረው ተናግረዋል።
በዚሁ ስብሰባ ላይ አንድ ጫራታ $32, ሺ ብር በላይ ተሽጦል።
የቴክሳስ የአርበኞች ግንቦት 7 ተወካይ እንደገለጸው የቴክሳስ ነዋሪ የአንዳርጋቸው ጽጌ ፍሬዎች መሆናቸውን ያሳዩበት እለት ነው። ትግሉ ዳር እስኪደርስ የእኛ ድጋፍ መቼም አይቋረጥም። ይህ መደረግ ከሚገባው ጥቂቱ ነው። ጀግኖች በበርሃ ለሚወዱት ሀገራቸው መሰዋእት ለመሆን መከራን ለመጋፈጥ ሲቆርጡ እኛ እዚህ አንድ ዶላር የማንረዳበት ምንም ምክንያት የለም በለዋል። ነጻነት ውድ ሂዎትን ያስከፍላል እኛ ደግሞ በውጪ ከምናገኘው ትንሽ ያውም ለምንወዳት ኢትዮጵያ ማድረግ ያስደስታል ሲሉ ለአባይ ሚዲያ ተናግረዋል።
የአርበኞች ግንቦት 7 የሀገርን የማዳን ጥሪ የገቢ ማሰባሰቢያ ቀጥሎ እሁድ በዋሽንግተን ዲሲ እና በተመሳሳይ በዋሽንግተን ሲያትል 08/16/2015 የሚደረግ ሲሆን፤ ቀጣይ ስብሰባዎች በለንደን እንዲሁም በኮሎራዶ ዴንቨር በ8/30/2015 ይቀጥላል። ከገቢ አስተባባሪው ያገኘነው መረጃ እንደሚያሳየን በቀጣዩ ወር ሴፕቴምበር 6, 2015 በኦክላንድ ካሊፎርኒያ, በተመሳሳይ ካልጋሪ ካናዳ እና ቶሮንቶ ቀጣይ ስብሰባዎች የሚካሄዱባቸው ናቸው።
ይህ ዘመቻ የሚያሳየው የኢትዮጵያ ህዝብ ለነጻነት የሚደረገውን እልህ አስጨራሽ ትግል ለመደገፍ ቆርጦ መነሳቱን ያረጋግጣል። ለዚህ ደግሞ አርበኞች ግንቦት 7 የጀመረው ስራ ብዙዎችን አነቃቅቶል።

No comments:
Post a Comment