Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Tuesday, August 18, 2015

አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በአባታቸው መጎበኘታቸው ተሰማ



የት እንዳሉ ሳይታወቁ ቀርተው የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ በአባታቸው መጎበኘታቸው ተሰማ:: የአርበኞች ግንቦት 7 አመራር የነበሩት አቶ አንዳርጋቸው ጽጌ የመን ላይ ተይዘው ለኢትዮጵያ መንግስት ተላልፈው ከተሰጡ በኋላ አፍቃሪ የመንግስት ድረገጾች በፎቶ ሾፕ አንዳርጋቸው የአዳማን መንገድ ሲጎበኝ በሶሻል ሚድያዎች ለጥፈው ሲዋሹ ነበር::

ከዚህም በተጨማሪ ዶ/ር ቴዎድሮስ አድሃኖም አቶ አንዳርጋቸውን ልማቱን እያስጎበኘነው ነው ሲሉ በአሜሪካ ድምጽ ራድዮ ላይ መናገራቸው ይታወሳል::


የአንዳርጋቸው ጽጌ እህት ብዙአየሁ ጽጌ እንደገለጹት አቶ አንዳርጋቸው በአባታቸው ቢጎበኙም ኢትዮጵያውያን ወደ ለንደን እስኪመለሱና ነፃነታቸውን እስኪያገኙ ድረስ ኢትዮጵያውያን አብረዋቸው እንዲቆሙ ጥሪያቸውን አቅርበዋል::

አቶ አንዳርጋቸው በአባታቸው ሲጎበኙ ጤነነታቸው በደህና ሁኔታ ይገኛል ከመባሉ ውጭ ምን እንደተነጋገሩ የታወቀ ነገር አለመኖሩ ለዘ-ሐበሻ የደረሱ መረጃዎች አመልክተዋል::

Source : Zehabesha

No comments:

Post a Comment

wanted officials