Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Sunday, August 30, 2015

አቶ በረከት ስምኦን በማሌዢያ ፒናንግ ደሴት የንግድ እና መኖሪያ ሕንጻ ቤት እያስገነቡ ነው::





አቶ በረከት ስምኦን በማሌዢያ ፒናንግ ደሴት የንግድ እና መኖሪያ ሕንጻ ቤት እያስገነቡ ነው::
‪#‎Ethiopia‬ ‪#‎Corruption‬ ‪#‎EthiopianOppositionParties‬ ‪#‎EPRDF‬ ‪#‎MinilikSalsawi‬

Minilik Salsawi - የለውጥ ሃይሉ እርስ በእርሱ በፖለቲካ ጥላቻ ሲጠዛጠዝ በሃገር እና ሕዝብ ላይ ዘረፋው ቀጥሏል:-ከጸረ - ሙስና ኮሚሽን ከመዝገብ ቁጥር /203/2007 ከተገኘው መረጃ መሰረት አቶ በረከት ስምኦን በማሌዥያ ፒናንግ ደሴት ጃላን ባሩው 62 በተባለ ቦታ ላይ በሚሊዮኖች ዶላር በወጣ ወጪ ኢትዮጵያ ውስጥ በብረታብረት ስራዎች ላይ ከሚገንኝ አንድ ማሌዢያዊ ጋር በመቀናጀት እጅግ ዘመናዊ የንግድ እና መኖሪያ ሕንጻ በኢንቨስትመት ስም እያስገነቡ መሆኑን ጥቆማ ለኮሚሽኑ ደርሶ በመመዝገብ እያጣራ መሆኑ ምንጮች ለምንሊክ ሳልሳዊ ገልጸዋል::ከሼህ መሃመድ አላሙዲ የሃገሪቱን ሃብት እያሳለፉ እየሰጡ ከፍተኛ ገንዘብ የሚረከቡት ኤርትራዊው አቶ በረከት ስምኦን በግልጽ ከሚታወቀው ከአገር ቤቱ በካፒቴኑ ስም ካስመዘገቡት ሆቴል እና ማደያዎች እንዲሁም የሪያል ስቴቶች በተጨማሪ በዱባይ እና አቡዳቢ መኖሪያቤቶች እና አክሲዮኖች ሲኖሯቸው እንዲሁም በሚላን ጣሊያን መኖሪያ ቤት በሕንድ የሚስማር ፋብሪካ ባለድርሻ ናቸው የሚል ከዚህ ቀደም በጸረ ሙስና ኮሚሽን የተመዘገበ ፋይል አላቸው::


የጸረ ሙስና ኮሚሽን በሕወሓት ባለስልጣናት በተለይ በአቶ ደብረጽዮን እና በጄኔራል? ሳሞራ ልዩ ትእዛዝ የሚመራ ሲሆን በከፍተኛ ባለስልጣናት ላይ የሚመጡ መዝገቦች ከቦታቸው እንዳይንቅሳቀሱ እና ተጣርተው ማረጋገጫ እንደተገኘ ከነማስረጃቸው ታሽገው ቀጥታ ወደ ደህንነት ቢሮ እደሚላኩ ይታወቃል::የአቶ በረከት የመኖሪያ ቤት ግንባታም ጠቅላላ መዝገቡ እንዳለቀ በጥብቅ ምስጢር በሚል ለደህንነት ቢሮ እንደሚላክ ምጮቹ የጠቆሙ ሲሆን የከፍተኛ ባለስልጣናትን ጉዳይ በሚመረምሩ መርማሪያን ላይ ክፍተኛ የሆነ የደህንነት ክትትል እንደሚደረግ ምንጮቹ አክለው ጠቁምዋል::

የደህንነት ቢሮው በቅርቡ ያወጣቸው መረጃዎች እንደሚጠቁሙት ባለስልጣኖች በተለያዩ ሃገራት የሰሯቸው መኖሪያ ሕንጻዎች መታገዳቸው ይታወቃል::የወያኔ ከፍተኛ ባለስልጣናት ኬንያ እና ሱዳንን ጨምሮ በተለያዩ የአፍሪካ ሃገራት መኖሪያ ቤቶች የሰሩ ሲሆን በታንጋኒካ ውስጥ ሃይቅ ዳርቻ ላይ የግል የመዝናኛ ቦታ ለመገንባት ያመለከቱ የሕወሓት ባለስልጣናት ከታንጋኒካ ባለስልጣናት ጋር በቦታ መረጣ እና በጉቦ ገንዘብ አለመግባባት እስካሁን እንዳልተፈቀደላቸው ታውቋል:: ‪#‎ምንሊክሳልሳዊ‬

No comments:

Post a Comment

wanted officials