Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Monday, August 10, 2015

ትላንት ምሽት በአዲስ አበባ የ3 ወጣቶች አስክሬን ኩሬ ውስጥ ተገኘ

ትላንት ምሽት በአዲስ አበባ የ3 ወጣቶች አስክሬን ኩሬ ውስጥ ተገኘ…
በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ልዩ ስሙ ላንድሮቨር ማዞሪያ፣ መሳይ ካባ በተባለ ቦታ ነው ወጣቶቹ ህይወታቸው አልፎ የተገኙት ተብሏል፡፡
በአካባቢው ለመንገድ ስራ ድንጋይ ለማውጣት የተቆፈረ ከ7 እስከ 9 ሜትር ርዝመት ያለው ጥልቅት መለስተኛ ሐይቅ ፈጥሯል፡፡
ሁለቱ 20 አንዱ ደግሞ 25 አመታቸው ነው የተባሉ 3 ወጣቶች የገቡበት ምክንያት ባይታወቅም የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋዎች መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን ከአካባቢው ነዋሪ በደረሰው ጥቆማ ትላንት ምሽት 3 ሰዓት ላይ የወጣቶቹን አስክሬን አውጥቷል፡፡
በወጣቶቹ አማማት ዙሪያ ላይ ከዘመዶቻቸው እና በቅርብ ከሚያውቋቸው ጓደኞቻቸው እየተሰጡ ያሉ አስተያየቶች ግድያው በመንግስት ታጣቂዎች እንደተፈጸመ ጥርጣሪያቸውን በመግለጽ ወንጀሉን የፈጸሙትን አካላትም ለፍርድ የማቅረቡን ስራ መንግስት የተለመደውን ድራማ እንደሚሰራ የአካባቢው ነዋሪዎች ስጋታቸውን እየገለጹነው።

No comments:

Post a Comment

wanted officials