ታሪካዊና እጅግ በጣም አስደማሚ የሆነ ታላቅ ሰላማዊ ሰልፍ ከ 80 – 100, 000 የሚቆጠሩ የጋሞ ብሔር ተወላጆችና ሌሎች ነዋሪዎች በተገኙበት ዛሬ በውቧ አርባ ምንጭ ከተማ በደማቅ መልክ ተደረገ፡፡ በሰልፉ አያሌ መልዕክቶች ከመሰማታቸውም በላይ ስለ ጋሞ ብሔር ጀግንነትና ከሌሎች የኢትዮጵያ ብሔር ልጆች ጋር ተከባብሮና ተፋቅሮ ስለመኖሩ ተወድሷል፡፡ ስለ አንድነቱም ተዚሟል፡፡ ሕገ መንግስቱ ይከበር፣ ጥገኞችና ሰርጎ ገቦች ታደላ ቱፋና ግብረ አበሮቹን ጨምሮ ስለጋሞ ሕዝብ የመናገር ስብዕናም ሞራልም የላቸውም፣ ቁጫ – ዶርዜ – ምን ምን እያላችሁ አትከፋፍሉንም፣ አንደ ጥንቱ ዛሬም እኛ ጋሞዎች አንድ ነን (ኑኒ ኢሲኖ)፣ ጋሞይ ጊታኮ፣ የመፅሐፉ ፀሐፊና ግብረ አበሮቹ በአስቸኳይ ለፍርድ ይቅረቡ የሚሉና ሌሎች መፈክሮች የተደመጡ ከመሆናቸውም በላይ አርባ ምንጭ የምትወድም ሳትሆን በሕዳሴ ጉዞ ላይ ያለች ከተማ ነች፣ እሷ ሳትሆን አውዳሚዎቿ ራሳቸው ይወድማሉ፣ እናም ታደለ ቱፋና ግብረ አበሮቹ እርማችሁን አውጡ ዓይነት መፈክሮች ከተማዋ ካላት የተፈጥሮ መስህቦች ውዳሴ ጋር ተዳምረው በሰፊው ተስተጋብተዋል፡፡
በመጨረሻም ሰልፉ በከተማ አስተዳደሩ በተጨማሪም በሃገር ባህል ሽማግሌዎችና በሐይማኖት አባቶች፡- በጥገኞች፣ በሟርተኞች፣ በስድብ ደራሲውና በግብረ አበሮቹ ላይ ያቶኮረ ውግዘት ታክሎበት በሰላም ተጠናቋል፡፡
No comments:
Post a Comment