Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, August 13, 2015

አንዳርጋቸው ጽጌ ቃሊቲ ማራሚያ ቤት ታዬ!


Andargachew Tsige
አርበኞች ግንቦት ሰባትን በ አሸባሪነት በምዕራባዊያን ዘንድ ለማስፈረጅ ያደረገው ከንቱ ውትወታ ያልሰመረለትና በተቃራኒው ጫናው የበረታበት ወያኔ የነጽነት ኮከቡን አንዳርጋቸው ጽጌ ሰውሮ ካስቀመጠበት ያፈና እስር ቤት ወደ ቃሊቲ ተዛውሮ መታየቱ ታወቀ።
ከየመን አየር ማረፊያ ትራንዚት ላይ በወያኔ ደህንነቶች የታፈነው ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ እስከዛሬ በማይታወቅ ቦታ ታስሮ ከፍተኛ ቶርች እየተፈጸመበት ሲሆን ባለፈው ሊጠይቁት የሄዱት የእንግሊዝ አምባሳደር እንዳሉት አንዳርጋቸው ካለሁበት ሁኔታ ይልቅ ሞትን እመርጣለሁ እንዳላቸው የሃገራቸው ጋዜጣ አምባሳደሩን ጠቅሶ ማውጣቱ ይታወሳል፥፥
ከዚህ ቀደም የውጪ ሃይሎች ጫና የበረታበት ወያኔ አቶ አንዳርጋቸውን ወደ ቃሊቲ ለማዘዋወር እስክንድር ነጋ ታስሮበት የነበረበትን ክፍል ሲያድሱ የነበረ ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት እስከዛሬ ሳይዘዋወር ቆይቷል፥፥በዚህ ሰሞን የአሜሪካ የአውሮፓ ሕብረት እና የእንግሊዝ ከፍተኛ የፖለቲካ ባለስልጣናት የጻፉትን ደብዳቤ እና የአልጀዚራን ዘገባ ተከትሎ ዛሬ የወጡ ዘገባዎች እንዳመለከቱት ታጋይ አንዳርጋቸው ጽጌ እነ አንዱአለም አራጌ ያሉበት አከባቢ ሆኖ ለብቻው ከሁለት ሰዎች ጋር ቃሊቲ እስር ቤት ዋይት ሃውስ ተብሎ በሚጠራው ቦታ ላይ መዘዋወሩን የመረጃ ምንጮች ጠቁመዋል፥፥
አፈትላኪ
http://satenaw.com/amharic/archives/9533

















No comments:

Post a Comment

wanted officials