Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Thursday, August 13, 2015

መራዊ ከተማ በእስራት እየማቀቀ ያለ የማትማቲክስ መምህር ስማቸው ምንቺል



ይህ ልጅ ስማቸው ምንቺል ይባላል ከባህርዳር 35 ኪሎ ሚትር እርቃ ከምትገኘው መራዊ ከተማ የሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት ውስጥ የማትማቲክስ መምህር ነው። ከ1997 ዓ.ም ጀምሩ የህዝቡ ስቃይና መከራ ገብቶት የመንግስት ተብየውን እስራት፣አጸያፊ ስድቦች፣የሞራል ኪሳራውን ተቋቁሞ ትክክለኛ ነገር ሲናገር በመኖሩ የወር ደሞዙን ሙሉ በሙሉ ሲያጣ ኑሯል።
.
እውነትና ፍትሕ፣ደግነትና ቅንነት፣ታማኝነትና ልባምነት፣ጉብዝናና ብርታት፣ቸርነትና ለጋስነት እነዚህን የመሳሰሉትን በጎ ስነምግባሮች ሕወሓት ወያኔ በእያንዳንዱ ግለሰብ ውስጥ እንዳይኖሩ ስለሚፈልግ ስማቸው ምንቺልን ከቤቱ አፍነው ከወሰዱት ከአንድ ወር በላይ ሆኖል።
.
ስማቸው ምንቺል ለአካባቢው ተጨቋኝ ህዝብ እውነት ስለተናገር ዛሬ ያለበትን እንኳ ማወቅ አልተቻለም።ይቺ አለም ላድርባዮች፣ለዋላዋዮች፣ለጨካኞች፣ለአጭበርባሪዎች፣ለቀጣፊዎች፣እንዲሁም ለዘራፊዎችና ለሙሰኞች በመሆኗ የዋሆችና ደጎች እየማቀቁ ይገኛሉ።

No comments:

Post a Comment

wanted officials