ፍትህ ተደብድቦ ኮማ ዉስጥ ገብቷል – Source: Millions of Voices for Freedom - UDJ
የተወሰኑት እስከ ጀነራል ማእረግነት ደርሰዋል። “ብሶት የወለደው የኢሕአዴግ ሰራዊት፣ ለሰፊው ሕዝብ ጥቅም ይሄን ሬዲዮ ጣቢያ ተቆጣጥሮታል” ተብሎ እንደነበረ፣ የኢሕአዴግ አካል በመሆን የደርግን ስርዓት ገረሰሱ። ሆኖም ከደርግ የባሰ ስርዓት ተተካ። በምርጫ ዘጠና ሰባት ህዝብ በይፋ የወያኔን የዘር ፖለቲካ አንገፈገፈኝ አለ። ሆኖም ወያኔዎች ብረት በሕዝቡ ላይ አነሱ።፡ ሰላማዊ ዜጎችን ግንባር፣ ግንባር እየገደሉ ረፈረፉ። በጉልበት ስልጣን ላይ ተንቆናጠው የግፍ አገዛዛቸዉን ቀጠሉ።
የስርዓቱ አካል እንደመሆናቸው፣ የሕወሃት መረን የለቀቀ የግፍ አገዛዝ ለመለወጥ፣ ከኢሕአዴግ ዉስጥ ሆነው መንቀሳቀስ ጀመሩ። በዉሸት ክስ ፣ መፈንቅለ መንግስት ሙክራ አደረጋችሁ ተብለው ታሰሩ። በማእከላዊ እሥር ቤት ምን ያህል አሰቃቂ ቶርቸር እንደሚደረግ የሚታወቅ ነው። በብዙ ድብደባና ቶርቸር፣ ያላደረጉትን አደረግን ብለው በፍርድ ቤት ሳይሆን በቴሌቭዥን እንዲያምኑ ተደረገ። ለውጥን በጠየቁ ፣ አመጸኛ ተብለው ብዙዎቹ የእድሜ ልክ እስራት ተፈረደባቸው።
የተወሰኑ በእስር ቤት ዉስጥ በደረሰባቸው ድብደባና ስቃይ ሕይወታቸው በወህኒ ቤት አልፏል። የቀረትም አሁን ባሉበት ሁኔታ በጣም ከፍተኛ ችግር ላይ ነው ያሉት።
ከሰላሳ ከሚበልጡ እስረኞች መካከል መካከል የሚከተሉት ይገኙበታል
1. ጄነራል ተፈራ ማሞ
2. ጄነራል አሳምነው ጸጌ
3፣ ኮሎኔል ሰለሞን አሻግሬ
4. ኮሎኔል ፋንታሁን ሙ እ ባ
4. አቶ መላኩ ተፈራ
6. ወ/ሮ እማዋይሽ አለሙ..
አንድ ወቅት እንደውም እስረኞቹ በጣም ከፍተኛ ድብደባ ይፈጸምባቸው ስለነበረ፣ ለፍርድ ቤት ብሶት ሊያቀረቡ በጠየቁበት ጊዜ ፍርድ ቤቱ ጉዳያቸውና አቤቱታቸዉን ለመስማት ፍቃደኛ ሳይሆን ይቀራል። በዚህ ወቅት ጀነራል አሳምነው ጽጌ ድምጻቸውን ከፍ አድርገው፣ “የተደበደበው ፍትህ ነው” በማለት የስርዓቱን ፍትህ ችግር ለማሳየት ሞክረው ነበር። ጀነራል አሳምነው ጸጌ እየተደበደበ ነው ያሉት ፍትህ ፣ በአሁኑ ወቅት ድበባው በዝቶበት ኮማ ዉስጥ ገብቷል። ሞቷል ማለት ይቻላል።
እነ ጀነራል ተፈራ፣ እንደነ አባ ዱላ፣ እንደነ ደመቀ መኮንን የህወሃት ጉጅሌ ሆነው ፣ ሃብት አትርፈው፣ ፎቅ አሰርተው መኖር ይችሉ ነበር። ነገር ግን እነርሱ ቢመቻቸውም የሕዝብ ሕመም ተሰማቸው። ሕሊናቸው አልፈቀደላቸውም። ለዉጥ ለማምጣት ሞከሩ። ግን የለወጥ ፣ የዲሞክራሱና የፍትህ ጠላት የሆኑት ወያኔዎች የግፍ በትራቸውን አነሱባቸው። ወያኔዎች ወንጀለኛ ቢሏቸውም ለኢትዮጵያ ህዝብ ግን ጀግኖች ናቸው። እነ ጀነራል ተፈራና ሁሉም የሕሊና እስረኞች እስኪፈቱ ትግሉ ይቀጥላል።
No comments:
Post a Comment