አረ የፈጣሪ ያለህ ሰዎች በድርቅ እያለቁ ነው
እኛ አንሰማም አናይም እንጂ በርካቶች ወገኖቻችን ወንድሞች እህቶች ልጆቻችን በድርቅ ምክንያት እያለቁ ነው በየአከባቢው የሚደርስላቸው አተዋል፡፡ አንድ የመንግስት ባለስልጣን ተብዬ ጀርመን ድምጽ ራድዮ ላይ ጉዳዩን አቅልሎ ‹‹እያጣራን ነው ጥናት እያደረግን ነው ስል ሰምቼዋለሁ፡፡›› ምንም በቀላል ሚታይ ነገር አይደለም አደጋው ከፍ ያለ ነው ፡፡ ከፍትህ ራድዮ ለወገን ደራሹ ወገን ነው ያገኘኋቸውን ምስልች ተመልክታችሁ እራሳችሁ ፍረዱ፡፡ እግዚጎ አንተ አስባቸው፡፡
እነዚሕ ከታች የምትመለከቷቸው በሚሌ ወረዳ በድርቅ ምክንያት አንስሳቶቻቸዉ አልቀው የሚሌ ወረዳ ጤና ፅ/ቤት እና የወረዳዉ አደጋ መከላከል ከየጫካዉ የሠበሰባቸዉ በረሀብ የተጎዱ ወገኖቻችን ናቸዉ።
በመሆኑም አሁን በሚሌ ጤና ጣቢያ መጠለያ የሚገኙ ሲሆን እየተደረገላቸዉ ያለዉ ድጋፍ እጅግ አናሣ ገዉ የፌድራሉ አደጋ መከላከል በእነዚህ ወገኖቻችን ላይ ፊቱን ሊያዞር ይገባል። የአሁን ባሠ በ 77 የነበረዉ ድርቅ አንሥሣቶችን አልጨረሰም እህልም ተወደደ እንጂ አልጠፋም ይህ የተለየ ነዉ አላሕ ይድረስልን።
ምንጭ፤- ፍትህ ራድዮ ለወገን ደራሹ ወገን ነው!
No comments:
Post a Comment