Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Wednesday, August 12, 2015

የህወሓት‬ አገዛዝ በላይ አርማጭሆ የጀመረው የትጥቅ ማስፈታት ዘመቻ አሁንም ተጠናክሮ እንደቀጠለ ነው










የአርበኞች ግንቦት 7 ድምጽ እንደዘገበው አርበኞች ግንቦት 7 ጦርነት በከፈተባቸውና አሁንም እየተፋለመባቸው በሚገኙ አካባቢወች የሚኖሩ ደሀ ገበሬዎች ለንብረታቸው መጠበቂያ ጥረው ግረው ጥሪታቸውን በማሟጠጥ በገንዘባቸው ገዝተው በፈቃድ የታጠቁት የጦር መሳሪያ በህወሓት አገዛዝ እየተወሰደባቸው ይገኛል፡፡
ሰሞኑን በታች አርማጭሆ የተጀመረው ትጥቅ የማስፈታት የህወሓት መሰሪይ ተግባር ላይ አርማጭሆንም ጨምሮ ተጠናክሮ ቀጥሏል፡፡
በአጠቃላይ በአርማጭሆ እና በወልቃት ምድር ሰፍሮ የሚገኘው ህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊት በህጋዊ መንገድ የታጠቀውን ገበሬ የጦር መሳሪያ መግፈፍ ዋነኛ ስራው ሁኗል፡፡

ላይ አርማጭሆ ከች ከንፈታ ቀበሌ ፈረስ ማጎሪያ ላይ ሰፍሮ የሚገኘው በህወሓት ቁጥጥር ስር የሚገኘው መከላከያ ሰራዊት ሰበብ አስባብ እየፈለገ የአካባቢውን ገበሬዎች ትጥቅ በመንጠቅ ስራ ላይ ተሰማርቶ ይገኛል፡፡
የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ ዘረኛ ቡድን ይቃወሙኛል ብሎ ከሚሰጋቸው ደሀ ገበሬዎች የሚነጥቀውን የጦር መሳሪያ ደጋፊዎቼ ናቸው ለሚላቸው ግለሰቦች እያስታጠቀ እንደሚገኝ የአርበኞች ግንቦት 7 ድምፅ ሬድዮ ዜና ምንጮች ገልፀዋል፡፡
አርበኞች ግንቦ 7 በጎንደርና አካባቢው በህወሓት መራሹ መከላከያ ሰራዊት ላይ እየፈፀመው የሚገኘውን ጥቃት እና እያገኘ የሚገኘውን ሰፊ የህዝብ ድጋፍ ተከትሎ በሰ/ጎንደር ዞን አስተዳደር የህወሓት አገልጋይ በሆኑት ከፍተኛ ሹማምንቶችና የበታች ካድሬዎች መካከል ከፍተኛ ፍጥጫ ተፈጥሯል፡፡
የላይኞቹ የህወሓት አገልጋዮች ከከፍተኛ የህወሓት ባለስልጣናት የተሰነዘረባቸውን “የጎንደር ህዝብ እኛን ጠልቶ ለምን ከአርበኞች ግንቦት 7 ጎን ተሰለፈ?” የሚል ጥያቄ ለበታቾቻቸው በተለያዩ የግምገማ መድረኮች በማንሳታቸው ምክንያት ነው ፍጥጫው የተከሰተው፡፡

– See more at:http://www.zehabesha.com/amharic/archives/45739#sthash.NJzXitqy.dpuf

No comments:

Post a Comment

wanted officials