አራቱ ፖለቲከኞች እስከ መስከረም 21 በእስር ላይ እንዲቆዩ ወሰነ
በነገረ ኢትዮጵያ ሪፖርተር
ነሀሴ 14/2007 ዓ.ም የፌደራሉ ከፍተኛው ፍርድ ቤት ከተከሰሱበት የሽብርተኝነት ክስ ነጻ ናችሁ ያላቸው የፖለቲካ አመራሮች የሆኑት አብርሃ ደስታ፣ የሺዋስ አሰፋ፣ ሀብታሙ አያሌው፣ ዳንኤል ሺበሺ እንዲሁም በተመሳሳይ መዝገብ ተከሶ ነጻ የተባለው አብርሃም ሰለሞን ላይ የፌደራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኙን ለማሰማት ለመስከረም 21/2008 ዓ.ም ቀጠሮ ሰጥቶባቸዋል፡፡ ፍርድ ቤት በነጻ እንዲለቀቁ የበየነላቸው የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች በደብዳቤ እግድ ተጥሎባቸው ከእስር እንዳይለቀቁ መደረጋቸውን በትናንትናው ዕለት መዘገባችን የሚታወስ ሲሆን እስከ መስከረም 21/2008 ዓ.ም በእስር ላይ እንደሚቆዩ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ቀጠሮ እንደሰጠባቸውም ታውቋል፡፡
አቃቤ ህግ ይግባኝ እንደጠየቀባቸው የታወቀ ቢሆንም እንደ ህግ ባለሙያዎች ግን የአቃቤ ህግ ይግባኝ ገና ተቀባይነት ባላገኘበት ሁኔታ ከእስር እንዳይለቀቁ እግድ ማድረግ ከህግ ውጭ መሆኑን ለነገረ ኢትዮጵያ አስረድተዋል፡፡
No comments:
Post a Comment