Which one you first choose? በቅድሚያ የሚፈልጉት

Friday, August 14, 2015

ለበጎ አድራጎት መኪናውን በስጦታ የለገሰው አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ መኪና ተሸለመ





‹‹አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ በእግሩ አይሄድም!›› - አቶ ሰለሞን አብርሃም - ኦሎምፒያ ደምበል ጀርባ የሚገኘው (የመኪና ሽያጭ እና ትራንስፖርት ድርጅት ባለቤት እና ማኔጂንግ ዳይሬክተር)

( ‪#‎ቀጥታ‬ ሥርጭት ከሐርመኒ ሆቴል (Live – Harmony Hotel)


ጌጡ ተመስገን ወደ መድረክ ወጣ፡፡ አዘጋጆቹ - የማያውቁትን ሰርፕራይዝ ይዞ መጣ፡፡ አቶ ሰለሞን ‹‹አርቲስት ሰለሞን ቦጋለ በእግሩ አይሄድም!›› በማለት

• የ1971 ዘመናዊ መርሰዲስ ቤንዝ
• ባለ አንድ በር
• 500 ሞዴል
• ይህቺ ቅንጡ መኪና በኢትዮጵያ አንድ ብቻ ናት -
• ግምቱ አንድ ሚሊየን ብር የሆነ መኪና - ለበጎ ሥራው - ይህንን ስጦታ በታላቅ አክብሮት ማበርከታቸውን አስታወቀ፡፡

***
አቶ ሰለሞን አብርሃም እንደተናገሩት ‹‹ሰለሞን ቦጋለ ይህቺንም መኪና ለበጎ አድራጎት መሸጡ አይቀርም፡፡ እኔም እርሱን መኪና መሸለሜን አላቆምም!..›› ብለዋል፡፡

ከአዳራሹ ‹‹ይገባዋል!- ይገባዋል!‹‹ይገባዋል!- ይገባዋል!›› የሚል ድምፅ ተሰማ

***
• የአርቲስት ሰለሞን መኪና በ500 ሺህ ብር ለጨረታ የቀረበች ቢሆንም ዘላለም የመኪና ኪራይ እና አስጎብኚ ድርጅት በ520,000 ለመግዛት ያቀረቡት ዋጋ ተቀባይነት አላገኘም፡፡ ጨረታውም ተሰርዟል፡፡ ይህቺ መኪና በድጋሚ እንደሚጫረት ከመድረክ ተገልጻል፡፡

• ሰለሞን ቦጋለ መኪናውን በሐርመኒ ሆቴል ለአጫራች ኮሚቴው አስረክቧል።

• 2,509,397,16 (ከሁለት ነጥብ አምስት ሚሊየን) ብር በላይ ተሰብስቧል

***
ምንጭ፡ Getu Temesgen - (ጌጡ ተመስገን) 

No comments:

Post a Comment

wanted officials